Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

‹‹ ለእህትህ ‘‘አትጨነቅም’’ ›› አሉኝ እነማ? ‪#‎እነሱ‬! ለምን? ሰልፍ እንዳትወጪ ያ አረመኔ ፖሊስ በያዘው ቆመጥ ይመታሻል ስላልኩኝ!

‹‹ ለእህትህ ‘‘አትጨነቅም’’ ›› አሉኝ
እነማ? ‪#‎እነሱ‬!
ለምን? ሰልፍ እንዳትወጪ ያ አረመኔ ፖሊስ በያዘው ቆመጥ ይመታሻል ስላልኩኝ!
‹‹ለእህትህ ‘‘አትጨነቅም’’›› አሉኝ
ለምን? የፖለቲካ ጋጋታውን ጋብ አድርጊው ትድርሺበታለሽ አሁን ግን ስለተፈጠርሽበት ዓላማ ተውሒድ ተማሪ ስላልኩኝ!
‹‹ለእህትህ ‘‘አትጨነቅም’’›› አሉኝ
ለምን? ሜካፕ ምናምን ተቀባብተሽ ከወንዶች ጋር አትጋፊ ይሄ ከሸሪዓ ይጋጫል ስላልኩኝ!
‹‹ለእህትህ ‘‘አትጨነቅም’’›› አሉኝ
ለምን? ከነሺዳና መንዙማ ብሎም ከፊልም ራቂ በቁርኣን ልብሽን አርጥቢ ስላልኩኝ!
‹‹ለእህትህ ‘‘አትጨነቅም’’›› አሉኝ
ለምን?በየፌስቡኩ በየዋትሳፑ ፎቶሽን አትለጥፊ ይቅርብሽ ስላልኩኝ!
እነሱማ ........ ‘‘ይጨነቁላታል’’ !!
- ‘‘ሰልፍ ወጥተሽ ተደብደቢ’’ ይሏታል !
- እነሱማ.. ’’ በድምፅሽ ግጥም ገጥመሽ ላኪልን’’ ይሏታል !
- እነሱማ.. ሰው ሃገር ለፍታ ያካበተችውን ሳንቲም ’’ ለትግል ነው አዋጪ’’ እያሉ ይብዘብዟታል!
- እነሱማ.. በየግሩፖቻቸው አስገብተው ’’ ተውሒድ እንማር የሚሉሽን ተጠንቀቂያቸው’’ ይሏታል!
- እነሱማ.. በየሲኒማ ቤቱ ’’ ፊልም ይመረቃልና እንዳትቀሪ’’ ይሏታል!
- እነሱማ.. በግሩፕ በግሩፕ ሰብስበዋት ’’ይሄን የፖለቲካ ወሬ ፖስት በየቦታው በትኚ ትግል ነው’’ ይሏታል!
- እነሱማ.. ይጨነቁላታል ሱናን አያስተምሯትም ቢድዓን ያሰጠኗታል!
- እነሱማ.. ይጨነቁላታል ሽርክን አያስጠነቅቋተም ሽርክ የሚያስጠነቅቀውን ግን ያስጠነቅቋታል!
- እነሱማ ይጨነቁላታል .............!
_______________
ስሚኝ እሕትዋ....!
’መጨነቅ’ እንደነሱ ከሆነማ...
ዓላማሽን ስተሽ በውድቀትሽ መሳለቄ ?
’መጨነቅ’ እንደሱ ከሆነማ...
በጅሕልና ፅልመት ተውጠሽ
በቢድዓ ማዕበል ታጥረሽ
ከሱና ርቀሽ ጀርባ ሰጥተሽ
ሳይሽ መሳቄ ከሆነማ ?
’መጨነቅ’ እንደሱ ከሆነማ ....
እወቂልኝ ከአሁን በህዋላ ...!
ይቅርብኝ ላንቺ ማሰቡ
’መጨነቅ’ መሳቀቅ በእሮሮ
ስለዚህ እወቂልኝ አሁንም ...
ላንቺ ለውዷ ፈርጧ እሕቴ
’አ...ል....ጨ....ነ....ቅ....ም’ - ከቶ!!!!