Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የኢትዬጵያ ሙስሊም ድጋሚ አንሸወድ ብልህ ከስህተቱ የሚማር ነው፡፡

የኢትዬጵያ ሙስሊም ድጋሚ አንሸወድ ብልህ ከስህተቱ የሚማር ነው፡፡
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹‹ሙዕሚን ካንድ ጉድጓድ ሁለት ግዜ በእባብ አይነደፍም›› ቡኻሪ እና ሙስሊም
ኢስላም ለማንኛውም አምልኮ ጉዳይ አቅም መቻልን አፅኖት ሰጥቶ አስቀምጦታል፡፡ አላህ አንድን ነፍስ ከአቅሟ በላይ አያስገድዳትም፡፡
ሌላው Online, Dubai, Saudi, Europe, America እና ሌላ ቦታዎች ላይ ተቀምጠው ሂድ፤ ውጣ፤ ለዲንህ ታገል እያሉ ለሚሰብኩህ ሰዎች ይችን ጥያቄ ጠይቃቸው
‹‹ለዲን መታገል ኢኽላሱን እና ሱናውን አሟልቶ ለሰራው ጀነት ያስገባል›› ታድያ እናንተ አዛችሁ ቦታው ላይ ምነው ጠፋችሁ?
እውነት እናንተም ይችኑ እኛን የምትሰብኩባትን ጀነት ነው የምትፈልጓት ወይንስ ሌላ አጀንዳ አላችሁ?
ጀግንነት ማለት ሰዎችን የማይችሉት ፈተና ውስጥ ገፋፍቶ ከቶ እራስን ከቦታው አርቆ ችግሩ ከደረሰ በኋላ የሀዘን መግለጫ እና የዜና ማጣፈጫ ማሰማት አይደለም፡፡
ሲጀምር ሸህ ጠሃ ተከትለውት የሚሰግዱት ሰው አይደለም፡፡ በጁዐችን አንቀልድ፡፡ ሸህ ጠሃ በዲን ላይ የሚያሾፍ፤ ወደ ሽርክ የሚጣራ ሰው ነው፡፡
አላህን ፍሩ ሰዎችን ወደዚህ ፈተና የምትቀሰቅሱ በተለይ ውጭ አገር ተቀምጣችሁ፡፡ ሀገር አቀፍ ብለህ አገር ውስጥ ከሌለህ ምን ያደርጋል???
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለምንድን ነው የማትሰሩትን የምትናገሩት ተብሎ የተኮነነው እንዲህ አይነቱን ሰው አይደለምን?

የሙስሊም ደም ከባድ ነው፤ ለአንድ የሙስሊም ደም መፍሰስ ሰበብ መሆን በኋላ ብዙ ያስከፍላል፡፡
አላህ ሆይ!
لَا يُكَلِّفُ ٱللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا ۚ لَهَا مَا كَسَبَتْ وَعَلَيْهَا مَا ٱكْتَسَبَتْ ۗ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَآ إِن نَّسِينَآ أَوْ أَخْطَأْنَا ۚ رَبَّنَا وَلَا تَحْمِلْ عَلَيْنَآ إِصْرًا كَمَا حَمَلْتَهُۥ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِنَا ۚ رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلْنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِۦ ۖ وَٱعْفُ عَنَّا وَٱغْفِرْ لَنَا وَٱرْحَمْنَآ ۚ أَنتَ مَوْلَىٰنَا فَٱنصُرْنَا عَلَى ٱلْقَوْمِ ٱلْكَٰفِرِينَ
አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡ ለርስዋ የሠራችው አላት፡፡ በርስዋም ላይ ያፈራችው (ኀጢአት) አለባት፡፡ (በሉ)፡- ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንስት አትያዘን፤ (አትቅጣን)፡፡ ጌታችን ሆይ! ከባድ ሸክምን ከእኛ በፊት በነበሩት ላይ እንደጫንከው በእኛ ላይ አትጫንብን፡፡ ጌታችን ሆይ! ለኛም በርሱ ችሎታ የሌለንን ነገር አታሸክመን፡፡ ከእኛም ይቅርታ አድርግ ለእኛም ምሕረት አድርግ፡፡ እዘንልንም፤ ዋቢያችን አንተ ነህና፡፡ በከሓዲዎች ሕዝቦች ላይም እርዳን፡፡
አላህን እንፍራ፤ አላህን እንፍራ፤ አላህን እንፍራ፡፡
እስቲ ከእኛ በፊት የነበሩት ደጋጎች በዲናቸው ላይ ፈተና ሲመጣ እንዴት ነበር ፈተናውን ያስተናገዱት? በስሜት ወይንስ መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎች የሄዱበትን መንገድ በመጓዝ?
ማንም ሰው አንድን ስራ ከመስራቱ በፊት የሚሰራው ስራ ከሸሪዓ ጋር ይሄዳል ወይንስ አይሄድም የሚለውን ጠንቅቆ ማረጋገጥ አለበት፡፡
ዛሬ በኢንተርኔት የሚያዙት የማያውቃቸው ሰዎች ቢያውቃቸውም ሸሪዓን የሚጋጭ ነገር ቢያዙት እና ቢፈፅም ነገ አላህ ፊት አያስጥሉትም እንዲያውም ይከዱታል፡፡
አላህ ሆይ! ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንከተለውም አድርገን፤ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡