Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዛሬ ሙስሊሞች ለምን ደካማ ሆኑ??? ሸይኸል ኢስላም ኢብን ተይሚያ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ

ዛሬ ሙስሊሞች ለምን ደካማ ሆኑ???
====================
ሸይኸል ኢስላም ኢብን ተይሚያ (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ
‹‹ሙስሊሞች ደካማ ከሆኑ እና ጠላቶቻቸው እነሱ ላይ የበላይ ከሆኑባቸው፤ ይህም (የሰሩት) የወንጀላቸው ውጤት ነው፤ ይህ ውስጣዊ (ትክክለኛ እምነትን መያዝን) እና ውጫዊም (ሰላት፤ ፆም፤ ዘካ እና ሌሎችን አምልኮ ተግባራትን ይመስል) የሆኑ ግዴታ ተግባራትን ችላ በማለታቸው ሰበብ ነው››
መጅሙኡ ፈትዋ 11/645
ይህን የሸይኸል ኢስላም ንግግር ዛሬ አለም ላይ አላህ ካዘነላቸው ባርያዎች ውጭ የሚሰሩትን ተግባር በተጨባጭ ስናየው ለዚህ ውርደት ሰበቡ ሰው የዘራውን ያጭዳል አይነት ሆኗል ነገሩ፡፡
ምን ያህሉ ለአቂዳ ቦታ ይሰጣል? ሙስሊም አገራት ላይ ስንት እና ስንት በዓድ አምልኮ (ሽርክ) ይፈፀማል? ስንት እና ስንት ቢድዓ ይሰራል? ስንት እና ስንት ሃብታም ዘካን ይከለክላል? ስንት እና ስንት ትዳርን ርቆ ዝሙት ይሰራል? ስንት ሰው የአርካኑል ኢስላም መሰረቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን ሃጅ የማይፈፅም አለ? ስንት እና ስንት ወንዶች ጀመዓ ሰላት አይሰግዱም? እና የመሳሰለውን
ሰው የሰራውን ያጭዳል ሆነ እና ነገሮች ሁሉ ተገለባበጡ፡፡
አላህ ሆይ! ጥርት ወዳለችው የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና ሙሉ ዲን መልሰን፡፡