Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዓቂዳዊ ጥያቄና ምላሽ ከአላህ በስተቀር በሀቅ ሊመለክ የሚገባው አምላክ የለም፤ ሙሀመድ የአላህ መልእክተኛ ናቸው ማለትም [ላ ኢላሃ ኢለላህ፣ ሙሀመደን ረሱሉላህ] የሚለው የምስክርነት ቃል ትርጉሙ ምንድነው? ማስረጃውንም ይጥቀሱልን።

③ ክፍል

🌐ዓቂዳዊ ጥያቄና ምላሽ
ـ الأسئلة والأجوبة في التوحيد

https://drive.google.com/file/d/0B5pFljkYQDdsZlNhYl9sUzd5dlk

በሸይኽ ሷሊህ ቢን ዐብዱረህማን ቢን ዐብደላህ አል አጥረም [ረሂመሁላህ]

بسم الله الرحمن الرحيم
الحمد لله، والصلاة والسلام على رسول الله وعلى آله وصحبه ومن اهتدى بهداه. وبعد:

7/ ما معنى شهادة أن لا إله إلا الله وأن محمداً رسول الله؟ مع ذكر الدليل.
ከአላህ በስተቀር በሀቅ ሊመለክ የሚገባው አምላክ የለም፤ ሙሀመድ የአላህ መልእክተኛ ናቸው ማለትም [ላ ኢላሃ ኢለላህ፣ ሙሀመደን ረሱሉላህ] የሚለው የምስክርነት ቃል ትርጉሙ ምንድነው? ማስረጃውንም ይጥቀሱልን።

الجواب: ምላሻቸው
معنى لا إله إلا الله: لا معبود بحق إلا الله، والإله معناه المعبود المتأله إليه.
ففيها نفي جميع المعبودات من وثن أو قبر أو شجر أو حجر أو ولي أو هوى، وفي قوله إلا الله إثبات العبادة لله وحده

"ላ ኢላሃ ኢለላህ" ማለት ትርጉሙ ከአላህ በስተቀር በሀቅ ሊመለክ የሚገባው አምላክ የለም ማለት ነው።

" አል ኢላህ الإله" የሚለው ቃል ትርጉሙ የሚገዝዙት፣ ወደሱ አምልኮትን የሚያደርሱለት፣ የሚያመልኩት ማለት ሲሆን ባጭሩ አምላክ ማለት ነው።

በዚህም የምስክርነት ቃል ውስጥ ጣዖታትን፣ መቃብሮችን፣ ዛፎችን፣ ድንጋዮችን፣ ወይም ወሊይን ሆነ ስሜትን ባጠቃላይ የሰው ልጅ ተሳስቶ የሚያመልካቸውን ሁሉንም ተመላኪ ነገሮችን የሚያስወግድ፣ አምልኮ እንደማይገባቸው የሚፃረር መልእክት አለበት።

"ኢለልላህ إلا الله" የሚለው ቃል ደግሞ አምልኮት የተባለ ሁሉ ለብቸኛው አምላክ ለአላህ ብቻ የሚገባው መሆኑን ያፀናል።
ومن عبده وحده اقتضى ذلك طاعة الله في جميع أوامره واجتناب منهياته، وهناك النصوص العديدة التي تفسرها من الكتاب والسنة: فمن الكتاب ،

ስለሆነም አላህን በብቸኝነቱ ያለ ምንም አጋር የሚያመልከው ሰው ማንኛውንም የአላህ ትእዛዛት ለመፈፀምና ክልከላዎቹንም ለመራቅ ይገደዳል። በዚህም ላኢላሀ ኢለላህ የሚለውን ቃል የሚተረጉምልን የሚያብራሩልን ከቁርኣንና ከሀዲስ በርካታ ማስረጃዎች ተገልፀዋል።

በአላህ ኪታብ ከተጠቀሱት ማስረጃዎች መካከል:-
قوله ـ تعالى ـ: {شَهِدَ اللَّهُ أَنَّهُ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ وَالْمَلَائِكَةُ وَأُولُو الْعِلْمِ قَائِمًا بِالْقِسْطِ لَا إِلَهَ إِلَّا هُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ}
آل عمران: 18

«አላህ በማስተካከል የቆመ (አስተናባሪ) ሲኾን ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የሌለ መኾኑን መሰከረ፡፡ መላእክቶችና የዕውቀት ባለቤቶችም (እንደዚሁ መሰከሩ)፡፡ ከእርሱ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ እሱ አሸናፊውና ጥበበኛው ነው፡፡» ይላል።
(ኣሊ ኢምራን:18)

እንዲሁም
{وَإِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ لِأَبِيهِ وَقَوْمِهِ إِنَّنِي بَرَاءٌ مِمَّا تَعْبُدُونَ *إِلَّا الَّذِي فَطَرَنِي فَإِنَّهُ سَيَهْدِينِ}.
الزخرف: 18
«ኢብራሂምም ለአባቱና ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ «እኔ ከምትግገዙት ሁሉ ንጹሕ ነኝ፡፡» «ከዚያ ከፈጠረኝ በስተቀር (አልግገዛም)፡፡ እርሱ በእርግጥ ይመራኛልና፡፡» ይላል።
(አል ዙኽሩፍ: 27)

ከዚሁ ጋር በተያያዘ
وأدلة شهادة أن محمداً رسول الله قوله ـ تعالى ـ:{لَقَدْ جَاءَكُمْ رَسُولٌ مِنْ أَنْفُسِكُمْ عَزِيزٌ عَلَيْهِ مَا عَنِتُّمْ حَرِيصٌ عَلَيْكُمْ بِالْمُؤْمِنِينَ رَءُوفٌ رَحِيمٌ}.
التوبه: 18
(ሙሀመደን ረሱሉላህ) ማለትም ሙሀመድ የአላህ መልእክተኛ ነው ለሚለው የምስክርነት ቃል ደግሞ ማስረጃው

«ከጎሳችሁ የሆነ ችግራችሁ በእርሱ ላይ ጽኑ የሆነ፣ በእናንተ (እምነት) ላይ የሚጓጓ፣ በምእምናን (ላይ) ርኅሩኅ አዛኝ የኾነ መልክተኛ በእርግጥ መጣላችሁ፡፡» የሚለው የአላህ ቃል አንዱ ማስረጃ ነው።
(አትተውባህ: 128)

ومعنى شهادة أن محمداً رسول الله طاعته فيما أمر وتصديقه فيما أخبر، واجتناب ما نهى عنه وزجر وأن لا يعبد الله إلا بما شرع، فهذا مقتضى الشهادة بالرسالة وهذا مقتضى تواطؤ اللسان مع القلب.

ሙሀመደን ረሱሉላህ محمد رسول الله) የሚለው የምስክርነት ቃል ያቀፈው ትርጉም ያዘዙትን መታዘዝ፣ የተናገሩትን እውነት ነው ብሎ ማመን፣ የከለከሉትንና ያስጠነቀቁትን ደግሞ መራቅ፣ እሳቸው በደነገጉት መመርያ እንጂ አላህን ኣለመገዛት፣ የአምልኮ ተግባርን ኣለመፈፀም። ይህ እንግዲህ በሳቸው መልእክተኝነት መመስከር ያቀፈው መልእክት ነው። እንዲሁም የአንደበትና የልብ መጣመርን የሚያሳየውም ይህ ነው።

8/ ما المقصود بتوحيد الربوبية؟
ተውሂድ አርሩቡቢያ "توحيد الربوبية" ሲባል ምን ለማለት ነው ?

الجواب: ምላሽ
المقصود بتوحيد الربوبية: الاعتقاد والاعتراف والإقرار الجازم بأن الله هو الخالق الرازق المحيي المميت المدبر لجميع الكائنات
ተውሂድ አርሩቡቢያ ማለትም በጌትነቱ ብቸኛ መሆኑ ሲባል የተፈለገበት መልእክት እሱ አላህ … ፈጣሪ፣ ሲሳይ ለጋሽ፣ ህያው አድራጊ፣ ህይወትን ወሳጅ ባጠቃላይ የሁሉም ነገሮች አስተናባሪ መሆኑን በማፅናት ቁርጥ ባለ ሁኔታ ማመን መቀበል ማለት ነው።

قال ـ تعالى ـ:
{وَمِنْ آيَاتِهِ خَلْقُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ وَاخْتِلَافُ أَلْسِنَتِكُمْ وَأَلْوَانِكُمْ ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِّلْعَالِمِينَ.}
الروم﴿٢٢﴾
«ሰማያትንና ምድርንም መፍጠሩ፣ የቋንቋዎቻችሁና የመልኮቻችሁም መለያየት፣ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለዐዋቂዎች ተዓምራቶች አልሉበት፡፡» ይላል።
አልሩም:(22)
እንዲሁም
وقال ـ سبحانه ـ:
{وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّـهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ} الفصلت: ﴿٣٧﴾
«ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ አትስገዱ፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአላህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምትግገዙ እንደ ኾናችሁ (ለሌላ አትስገዱ)፡፡»
አልፉስሲለት: (37)

فهو المالك المتصرف، وهذا يستلزم قبول أمره واجتناب نهيه
አላህ እሱ የሁሉም ነገር ባለቤት፣ ንጉስና አስተናባሪ የሆነ አምላክ ነው። ይህ ሀያልነቱ ደግሞ ትእዛዛቱን እንድቀበልና ክክከላዎቹን እንድንርቅ ያስገድደናል።

{أَلَا لَهُ الْخَلْقُ وَالْأَمْرُ تَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ} الأعراف: ﴿٥٤﴾
والنصوص في هذا كثيرة.
«ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ (ክብሩ) ላቀ፡፡» በማለት ሃያልነቱን ያስገነዝበናል።
አልአዕራፍ: (54)

ባጠቃላይ በዚህ ርእስ ላይ የተወረዱ ማስረጃዎችም እጅግ በጣም በርካታ ናቸው።

9/ ما المراد بالخلق؟
መፍጠር [ኸልቅ "خلق"] ሲባል ምን ለማለት ነው ?

الجواب: ምላሽ
المقصود بالخلق: إيجاد الأشياء بعد أن لم تكن موجودة ، وبدعها على ما لم يسبق لها نظير

መፍጠር [ኸልቅ "خلق"] ማለት ያልነበረን ነገር ማስገኘት ማለት ነው። ቀድሞ አምሳያ የሌለውን አዲስ ነገር መፍጠርም ማለት ነው።

{ بَدِيعُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَإِذَا قَضَىٰ أَمْرًا فَإِنَّمَا يَقُولُ لَهُ كُن فَيَكُونُ.}
البقرة: ﴿١١٧}
«ሰማያትንና ምድርን ያለብጤ ፈጣሪ ነው፤ ነገርንም (ማስገኘት) በሻ ጊዜ ለርሱ የሚለው፡- «ሁን ነው፤» ወዲያውም ይኾናል፡፡» ይላል።
አልበቀራ: 117

በሌላ አንቀፅም
{الْحَمْدُ لِلَّـهِ فَاطِرِ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ جَاعِلِ الْمَلَائِكَةِ رُسُلًا أُولِي أَجْنِحَةٍ مَّثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۚ يَزِيدُ فِي الْخَلْقِ مَا يَشَاءُ ۚ إِنَّ اللَّـهَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ .} فاطر: ﴿١﴾

«ምስጋና ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ፣ መላእክትን ባለ ሁለት ሁለት፣ ባለ ሶስት ሶስትም፣ ባለ አራት አራትም ክንፎች የኾኑ መልክተኞች አድራጊ ለኾነው አላህ ይገባው፡፡ በፍጥረቱ ውስጥ የሚሻውን ይጨምራል፡፡ አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነውና።»
ፋጢር: (1)

{فَاطِرُ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ جَعَلَ لَكُمْ مِنْ أَنْفُسِكُمْ أَزْوَاجًا وَمِنَ الْأَنْعَامِ أَزْوَاجًا يَذْرَؤُكُمْ فِيهِ لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ} الشورى: 11
«ሰማያትንና ምድርን ፈጣሪ ነው፡፡
ከነፍሶቻችሁ ሴቶችን ከቤት እንስሳዎችም ዓይነቶችን (ወንዶችና ሴቶችን) ለእናንተ አደረገላችሁ፡፡ በእርሱ ያበዛችኋል፡፡ የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡ እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው፡፡»
አሽሹራ: (11)

وكل شيء خلقه الله فهو مبتدئه على غير مثال سبق إليه
አምላካችን አላህ ለፈጠራቸው ነገሮች በሙሉ ቀድሞ ምንም ብጤ ሳይኖረው የጀመረው የፈጠረው እሱው ራሱ ነው።

{أَلَا لَهُ الْخَلْقُ وَالْأَمْرُ تَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ} الأعراف: 54
ويأتي الخلق بمعنى التقدير، ومنه
« ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ (ክብሩ) ላቀ፡፡» ይላልና።
አል-አዕራፍ: (54)

ኸልቅ خلق የሚለው ቃል በግምት መነሻ መቅጠፍ፣ መሳል፣ መቅረፅ የሚል ትርጉምም አለው። ለምሳሌ
قوله ـ تعالى ـ: {تَبَارَكَ اللَّهُ أَحْسَنُ الْخَالِقِينَ} أي المقدرين،
«ከሰዓሊዎችም (ከቀራፂያን) ሁሉ በላጭ የሆነው አላህ ላቀ፡፡»
አልሙእሚኑን: (14)

وقوله ـ تعالى ـ {وَتَخْلُقُونَ إِفْكًا} أي تقدرون كذباً.
«ውሸትንም ትቀጣጥፋላችሁ።» ማለትም በግምታዊ መነሻ ስለሚቀባጥሩ ውሸትን ትቀጥፋላችሁ ይላቸዋል።

10/ ما المراد بالملك؟
ሙልክ الملك ሲባል ምን ለማለት ነው

الجواب: ምላሽ
المراد بالملك: السلطان والعز والعظمة، فالرب هو المالك
ሙልክ ማለት ስልጣን፣ ሃያልነት፣ የበላይነት እንደማለትም ነው።
ጌታም الرب ራሱ ተቆጣጣሪ ንጉሦ፣ ባለቤት ነውና።

አላህም
قال ـ تعالى ـ: {مَالِكِ يَوْمِ الدِّينِ}
«የፍርዱ ቀን ባለቤት» ይላል።

{ قُلِ اللَّـهُمَّ مَالِكَ الْمُلْكِ تُؤْتِي الْمُلْكَ مَن تَشَاءُ وَتَنزِعُ الْمُلْكَ مِمَّن تَشَاءُ
وَتُعِزُّ مَن تَشَاءُ وَتُذِلُّ مَن تَشَاءُ ۖ
بِيَدِكَ الْخَيْرُ ۖ إِنَّكَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ }
آل عمران ﴿٢٦﴾
«ሙሐመድ ሆይ!) በል፡- «የንግስና ባለቤት የኾንክ አላህ ሆይ! ለምትሻው ሰው ንግሥናን ትሰጣለህ፡፡ ከምትሻውም ሰው ንግሥናን ትገፍፋለህ፡፡
የምትሻውንም ሰው ታልቃለህ፡፡ የምትሻውንም ሰው ታዋርዳለህ፡፡
መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ (በችሎታህ) ነው፤ አንተ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነህና፡፡»
ኣሊ-ዒምራን: (26)

وأما قوله :
{قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ النَّاسِ ﴿١﴾ مَلِكِ النَّاسِ ﴿٢﴾ إِلَـٰهِ النَّاسِ ﴿٣﴾ }
«በል “በሰዎች ጌታ እጠበቃለሁ፡፡የሰዎች ሁሉ ንጉሥ በኾነው፣ የሰዎች አምላክ በኾነው፡፡»
አንናስ: 1-3

ይህም
أي أفضل الملوك وأقواهم وأعزهم وأشملهم ملكاً.
አላህ ንጉስ ነው ሲባል ምድር ላይ ንጉስ ተብለው ከሚጠሩት ፍጡራን ሁሉ በላጩ፣ ሃያሉ የሆነው፣ ንግስናን ሁሉ አጠቃልሎ የተቆጣጠረው ንጉስ ማለት ነው።

فالملك من الناس ملكاً نسبياً، ووصف الرب بالملك ملكاً مطلقاً تاماً فهو ملك الملوك.
የሰው ልጅ ንግስና አንፃራዊ ሲሆን የአላህ ንግስና ግን አጠቃላይና የተሟላ ንግስና ነው። እሱም ንጉሠ ነገሥት ነው።

11/ ما المقصود بالتدبير؟
ማስተናበር ማለትም "ተድቢር التدبير" ማለት ምን ማለት ነው ?

ምላሽ
الجواب: المقصود بالتدبير إنفاذ الأمر وإبرامه فهو يعلم عواقب الأمور وما تؤول إليه،
ማስተናበር ማለት የአንድን ነገር ሂደትም ሆነ መጨረሻ ውጤቱን ሙሉ በሙሉ አውቆ መምራት፣ ማካሄድ እንደማለት ነው።
قال ـ تعالى ـ:
{يُدَبِّرُ الْأَمْرَ يُفَصِّلُ الْآيَاتِ لَعَلَّكُم بِلِقَاءِ رَبِّكُمْ تُوقِنُونَ } الرعد: ﴿٢﴾
« ነገሩን ሁሉ ያስተናብራል፡፡ በጌታችሁ መገናኘት ታረጋግጡ ዘንድ ተዓምራቶችን ይዘረዝራል፡፡»
አርረዕድ: (2)

---------------※ --------------
www.fb.com/tenbihat
05ሰፈር 1437/ 22Dec15
ከተንቢሃት የዋትሳፕ ግሩፕ
https/telegram.me/tenbihat