Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

“መውሊድ” gtm

“መውሊድ”
መርያችን አልሰሩት ሱሓባ አልነካካው
በሱና አልጸደቀ የስራ በረካው
ሰለፍ ልብ አልሰጠው መቃረብያ ብሎ
አልበላ አልዘለለ ያን ቀን ዳሱን ጥሎ
ሰብስቦ አልደገሰ መውሊዳችን ብሎ።
የኋላኋላ ‘ንጂ የጥመቶች ፊርቃ
ሱና ላይ ደንዝዞ በቢድዓ የነቃ
ያልነበረን መውሊድ ፈጣጥሮት ሲያበቃ
በነብዩ ሱና ያደበላለቀው
ቁርአንና ሱና ከቶውም አያውቀው


በሙሓመድ ሲራጅ