Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለምንድን ነው አሏሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ለሴቶች ኃዘንን ያልመረጠላቸው?


ለምንድን ነው አሏሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ለሴቶች ኃዘንን ያልመረጠላቸው?

አሏሁ ተዓላ በሱረቱል ቀሰስ ውስጥ (ስለ ሙሳ እናት ልጇን ወደሷ የተመለሰላትን ምክኒያት ሲናገር) እንዲህ ይላል

{አይኗ እንድትረጋ ፣ እንዳታዝንም}

በሱረቱል አህዛብም እንዲህ ብሏል :
{ (የሴቶቹ) አይናቸው ትረጋ ዘንድ፣ እንዳያዝኑም}

ሱረቱል መርየም ውስጥም:
{ከበታቿም ፥ አትዘኚ ሲል ተጣራት}

ሱረቱል ቀሰስ ውስጥም እንዲህ ይላል:
{ አትፍሪም ፣ አትዘኚም}

አንቀፆቹ የሴት ልጅ ሃዘን ፦ ጥልቅ፣ እና ብርቱ ልቧ ሊሸከመው የማይችል ህመም ያለው እንደሆነ ግልፅ አድርገዋል ፤
እርሷም ባዘነች ግዜ ልቧ ይሰበራል

ታድያ እነዚህን ብርጭቆዎች(ብልቃጦች) በልስላሴ መያዝ ያስፈልጋል፤

የእናትህል ልብ በንግግር አልያም ካንተ የፈለገችብህን ነገር በማዘግየት እንዳትሰብር ፤

የእህትህንም ልብ ፡ እሷ ላይ በማላገጥ እና ከክብሯ በማጓደል አታስጨንቅ፤

የሚስትህንም ልብ ፡ እሷን ችላ በማለት እና ወደጎን በመተው አታቁስል፤

ልጅህንም አዳምጣት ፈገግታም ለግሳት ፍላጎቶቿንም አሟላላት ፤

ለእነርሱ ደግም በመዋል ወደ አሏህ ተቃረብ፤
ቀልባቸውንም አታሳዝን

እነርሱን አያከብርም፥ የተከበረ ሰው ቢሆን እንጂ፣ እነርሱንም አያዋርድም፥ የተወቀሰ ሰው ቢሆን እንጂ፤

እነርሱ ልብ ውስጥ ደስታን ባስገባህ ግዜ ያለህን ምንዳ ኮፊ አታውቀውም(እጅጉን የላቀ ነው)

እነርሱ ኮ ከአሏህ ቡኋላ ለሲሳይህ እና ለደስታህ ሰበብ ናቸው።

------------------

لماذا لم يرض الله للنساء الحزن ؟

قال الله تعالى في سورة القصص
" كي تقر عينها ولا تحزن"

وقال في سورة الأحزاب ..
" أن تقر أعينهن ولا يحزن"

وقال في سورة مريم
" فناداها من تحتها ألا تحزني"

وقال في سورة القصص
" ولا تخافي ولا تحزني"

وضحت الآيات أن حزن المرأة عميق،
وذو ألم شديد لا يتحمله قلبها،
فهي إذا حزنت انكسر قلبها فرفقاً
بالقوارير لا تكسر قلب أمك بكلمة
أو تأخير طلبها،
لا تعتصر قلب أختك باستهزاء واستنقاص،
لا تجرح قلب زوجتك بإهمال وتهميش،
استمع لابنتك وابتسم لها ولبي طلبها.
تقرب إلى الله بالإحسان لهن،
ولا تحزن قلوبهن ...
فلا يكرمهن إلا كريم ...ولا يهينهن إلا لئيم ...
فوالله لا تعلم أجر الفرح والسرور
إذا أدخلته عليهن ..
فهن سبباً في رزقك وسعادتك بعد الله ..
ወላሁ አእለም