Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

"የወንድሞቻቸውን ምክር አይቀበሉም"

"የወንድሞቻቸውን ምክር አይቀበሉም"
*********************
ይህች አጭር መልክት አንዳንድ ወንድሞች እና እህቶች ባለንበት ወቅት ከማንኛውም የቢድዐ ቡድን እና ማንኛውም መጤ አካሄዶችን የማይቀበሉ ብሎም የሚያስጠነቅቁ የሆኑ ወንድሞችን እና እህቶችን "ድንበር ያለፉ፣ ሂክማ የሌላቸው፣ ••••• ናቸው" በማለት ስም ሲያጠፉ ይታያል።
እስቲ ምንን ይሆን ምክር አይቀበሉም ብለው የሚጠሩት???
አንድ ምሳሌ ላንሳ
አንድ ወንድም ልምከርህ አለኝ
እሺ አልኩት
እንዲህም አለኝ
"ስለ ኳስ የፃፍከውን አየሁት ጥሩ ነው፣ ግን ከወቅቱ ጉዳይ ጋር አታያይዘው"

ሱብሃነላህ
ምን ፅፌ ይሆን "ከወቅቱ ጉዳይ ጋር አታያይዘው" ያለኝ?
የኢትዬጵያ ሙስሊም እንደሚታወቀው ፊትና ላይ ነው። በዲኑ የተፈተነ ደግሞ አላህን ያመልካል እንጂ ሽርክ የተደባለቀበት መንዙማ በመስማት፣ ቢድዓ፣ ኳስ፣ ድራማ፣ ፊልም እያለ አላህን አያምፅም፣ ግዜውንም አያባክንም። ሙስሊሞች አደለም በፈተና ጊዜ በሰላሙም አላህን ሊያምፁት አይገባም።
ስለ ኳስ ፖስት ያደረግኩት ላይ ጀመዐ ሰላት አለመምጣት የኒፋቅ ምልክት እንደሆነ የአብደላህ ኢብን መስዑድን (ረድየላሁ አንሁ) ንግግር ጠቅሼ ከዛም እንዲህ ፅፌ ጨረስኩ
"በዚህ ሁኔታ ካለህበት ፈተና መውጣት ፈለግክን?"
እንዲህ አይነቱን ነው እንግዲህ ከወቅቱ ጋር አታያይዘው የሚሉት።
ስለዚህ "ምክር አይቀበሉም እና ሌላም" እየተባለ ያለው ስሜታቸውን የማይገጥም ነገር ሲነገር፣ ቢድዓው ሲጋለጥበት መሆኑ መታወቅ አለበት። ብሎም ይህ ማደናበሪያ እኛን ዝም ለማስባል የተሞከረ ነው።
አሁንም ቢሆን አስረግጠን እንናገራለን ከሽርክ፣ ከቢድዓ፣ ኢስላማዊ እያሉ ሰውን ከቁርዓን፣ ከሱና፣ ከኢልም፣ ከትክክለኛው ግንዛቤ ኡማውን አርቀው ወደ ጥመት የሚጣሩ ቡድኖች እና ግለሰቦችን ዝም በማለት፣ እነሱን ባለማስጠንቀቅ መፍትሄ አይገኝም። ስናስጠነቅቅ ደግሞ የጥመት ደረጃቸው ቢለያይም ሁሉንም እንጂ አህባሽን ብቻ መሆን የለበትም።
አንድ ሰው ወንድሙን መምከር ሲፈልግ በማስረጃ ሊሆን ይገባዋል። ለምሳሌ አገራችን ላይ ያለ ሽርክ ሲጋለጥ የቢድዐ አራማጆች ተነስተው "በታተኑን፣ አንድነታችንን አፈረሱት" ብለው ያን የውሸት ክሳቸውን በአደባባይ ቢነዙት፣ ሱና ተከታይ የሆነ ሰው ወንድሙን ልምከር ብሎ ሲመጣ የነዚህን ሰዎች "የአዞ እማባ" ሰምቶ ሳይሆን ሊመክር የሚገባው የሚከተሉትን ጥያቄዎች እራሱን በመጠየቅ ሊሆን ይገባል
1) ወንድሜ መልክተኞች ከነበሩበት መንገድ የወጣ ምን አዲስ ነገር ይዞ ተነስቷል???
2) የሰለፉነ ሷሊሂንን አረዳድ ተቃርኗልን???
እና የመሳሰለውን
እዚህ ላይ ችግር ካላገኘበት ወንድሙን ሊያግዘው አብሮት ሊሆን ነው የሚገባው። ምክንያቱም አላህ ከእውነተኞች ጋር ሁኑ ነው ያለው።
የቢድዐ ሰዎች የበዙትን ያህል ቢበዙ እንዳያታሉህ። የነሱን የበዛ ውሸት ይዘህ የሱና ወንድሞችህን ያለ ማስረጃ ለመተቸት እና ስማቸውን ለማጥፋት አትሞክር። ያለ ማስረጃ የወንድሞችህን ስም ብታጠፋ ኪሳራው በራስህ ላይ ነው።
በአላህ ፈቃድ ማንኛውንም የጥመት አካሄድ በአላህ እገዛ እናጋልጣለን።
አላህ ፅናቱን ይስጠን። አላህ ፍትሃዊነቱን ያላብሰን።

Post a Comment

0 Comments