Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ውሎኣችንን እንገምግም !

‎تنبيهات على أحكام تختص بالمؤمنات    ተንቢሀት - ሙስሊም ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት‎'s photo.
‎تنبيهات على أحكام تختص بالمؤمنات    ተንቢሀት - ሙስሊም ሴቶችን የተመለከቱ ህግጋት‎'s photo.
ውሎኣችንን እንገምግም !
በየ እለቱ ፌስቡክና መሰሎቹን መጎብኘትዎ አይጠረጠርም።
የጌታዎ የአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ቃል የሆነውን ቁርኣንን ለማንበብና ለማስተዋል ግን ምን ያህል ግዜ እንደሰጡት ራስዎን ያውቁታል።
ሙስሊሞች ሆይ ቁርኣንን አናኩርፍ !
ቁርኣን የአምላካችን ቅዱስ ቃል ነው
በማንበባችን፣ በማስተዋላችን፣ በማስተንተናችንና በመተግበራችን የምንመነዳበት የምንከበርበት ታላቅ በረከት ነውና እንበርታ።
ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ ባወሩልን መሰረት የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዳሉት
عن ابن مسعود قال : قال رسول الله صلى الله عليه وسلم
{ : من قرأ حرفا من كتاب الله فله حسنة والحسنة بعشر أمثالها ، لا أقول الم حرف ، ولكن ألف حرف ، ولام حرف ، وميم حرف } . رواه الترمذي .
« ከአላህ ኪታብ አንዲትን ቃል ያነበበ ለሱ መልካም ምንዳ ኣለው። እያንዳንዷም መልካም ምንዳ በአስር አምሳያዋ ትባዛለች። "አሊፍ ላም ሚም" የሚለውንም አንድ ቃል ነው አልልም። ነገር ግን "አሊፍ" ቃል ነው "ላም" ቃል ነው "ሚም" የሚለውም (ራሱን የቻለ) ቃል ነው። »
ቱርሙዚይ ዘግበውታል።
በየእለቱ እንደ አቅማችን አላህ ያገራልንን ያህል በሰላት ላይ፣ እንዲሁም ያለ ሰላትም እናንብብ።
” فَاقْرَءُوا مَا تَيَسَّرَ مِنْهُ ۚ “
المزمل: 20
« ከቁርኣን የተቻላችሁን አንብቡ »
አል ሙዘሚል: 20
ያለ ምንም ገደብ ሌሊት በመነሳት በለይል ሰላት ላይም የገራላችሁን ያህል አንብቡ።
__________
ابو فوزان
19 rabi'e al sani 1436
08Feb 15

Post a Comment

0 Comments