Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሩቅን ምስጢር

« የሩቅን ምስጢር »
የሩቅ ምስጢር “ገይብ” ማለት ከሰዎች አዕምሮና እይታ የተሰወረ ነገር ሲሆን አሁን ያለ፣ ያለፈ ወይም የወደፊት ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የአላህ መለያ በመሆኑ ከሱሌላ ማንም ሊያውቀው አይችልም
አላህ እንዲህ ይላል፦
ﻗُﻞ ﻟَّﺎ ﻳَﻌْﻠَﻢُ ﻣَﻦ ﻓِﻲ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﻭَﺍﺕِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﺍﻟْﻐَﻴْﺐَ ﺇِﻟَّﺎ ﺍﻟﻠَّﻪ
«በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ምስጢር አያውቅም፡፡ ግን አላህ (ያውቀዋል)፡፡›› (አል ነምል 65)
ﻟَﻪُ ﻏَﻴْﺐُ ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﻭَﺍﺕِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ
«አላህ የቆዩትን ልክ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡ (አል ከህፍ 26)
ﻋَﺎﻟِﻢُ ﺍﻟْﻐَﻴْﺐِ ﻭَﺍﻟﺸَّﻬَﺎﺩَﺓِ ﺍﻟْﻜَﺒِﻴﺮُ ﺍﻟْﻤُﺘَﻌَﺎﻝِ
‹‹ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ታላቅ የላቀ ነው፡፡›› (ረዕድ 9) የሩቅ ምስጢርን ከአላህ በቀር ሌላው ይቅርና የቅርብ መልአክም ሆነ የተላከ ነብይ የሚያውቅ የለም፡፡ አላህ ስለ ኑህ ሲናገር እንዲህ ይላል፦
ﻭَﻟَﺎ ﺃَﻗُﻮﻝُ ﻟَﻜُﻢْ ﻋِﻨﺪِﻱ ﺧَﺰَﺍﺋِﻦُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﻟَﺎ ﺃَﻋْﻠَﻢُ ﺍﻟْﻐَﻴْﺐَ
«ለእናንተም እኔ ዘንድ የአላህ ግምጃ ቤቶች አልሉ ሩቅንም ዐውቃለሁ አልላችሁም (አላቸው)፡፡ ›› (አል ሁድ 31) ስለ ሁድ ሲናገርም እንዲህ ይላል፦
ﻗَﺎﻝَ ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﺍﻟْﻌِﻠْﻢُ ﻋِﻨﺪَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺃُﺑَﻠِّﻐُﻜُﻢ ﻣَّﺎ ﺃُﺭْﺳِﻠْﺖُ ﺑِﻪِ
«ዕውቀቱ አላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ያን በእርሱ የተላክሁበትንም አደርስላችኋለሁ›› አላቸው፡፡ (አል አህቃፍ 23)  አላህ ለነብዩ ሙሐመድም ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብሏል፦
ﻗُﻞ ﻟَّﺎ ﺃَﻗُﻮﻝُ ﻟَﻜُﻢْ ﻋِﻨﺪِﻱ ﺧَﺰَﺍﺋِﻦُ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﻟَﺎ ﺃَﻋْﻠَﻢُ ﺍﻟْﻐَﻴْﺐَ
«ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ ሩቅንም አላውቅም፡፡›› በላቸው፡፡ (አል አንዓም 5ዐ)
ﻭَﻋَﻠَّﻢَ ﺁﺩَﻡَ ﺍﻟْﺄَﺳْﻤَﺎﺀَ ﻛُﻠَّﻬَﺎ ﺛُﻢَّ ﻋَﺮَﺿَﻬُﻢْ ﻋَﻠَﻰ ﺍﻟْﻤَﻠَﺎﺋِﻜَﺔِ
ﻓَﻘَﺎﻝَ ﺃَﻧﺒِﺌُﻮﻧِﻲ ﺑِﺄَﺳْﻤَﺎﺀِ ﻫَﺆُﻟَﺎﺀِ ﺇِﻥ ﻛُﻨﺘُﻢْ ﺻَﺎﺩِﻗِﻴﻦَ
ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﺳُﺒْﺤَﺎﻧَﻚَ ﻟَﺎ ﻋِﻠْﻢَ ﻟَﻨَﺎ ﺇِﻟَّﺎ ﻣَﺎ ﻋَﻠَّﻤْﺘَﻨَﺎ ﺇِﻧَّﻚَ ﺃَﻧﺖَ ﺍﻟْﺤَﻜِﻴﻢُ
ﺍﻟْﻌَﻠِﻴﻢُ
‹‹አደምንም ስሞችን ሁሏንም አስተማረው፡፡ ከዚያም በመላእክት ላይ (ተጠሪዎቹን) አቀረባቸው፡፡ «እውነተኞችም እንደኾናችሁ የነዚህን (ተጠሪዎች) ስሞች ንገሩኝ» «ጥራት ይገባህ፤ ከአስተማርከን ነገር በስተቀር ለኛ ዕውቀት የለንም፡፡ አንተ ዐዋቂው ጥበበኛው አንተ ብቻ ነህና» (አሉ)፡፡ (አል በቀራህ 31-32) ይህ ሆኖ ግን አላህ ለተወሰኑ ፍጡሮች ከስውር ዕውቀቶች የተወሰነ በራዕይ ሊያሳውቂቸው ይችላል፡፡ ለምሳሌ አላህ እንዲህ ብሏል፦
ﻋَﺎﻟِﻢُ ﺍﻟْﻐَﻴْﺐِ ﻓَﻠَﺎ ﻳُﻈْﻬِﺮُ ﻋَﻠَﻰ ﻏَﻴْﺒِﻪِ ﺃَﺣَﺪًﺍ
ﺇِﻟَّﺎ ﻣَﻦِ ﺍﺭْﺗَﻀَﻰ ﻣِﻦ ﺭَّﺳُﻮﻝٍ ﻓَﺈِﻧَّﻪُ ﻳَﺴْﻠُﻚُ ﻣِﻦ ﺑَﻴْﻦِ ﻳَﺪَﻳْﻪِ ﻭَﻣِﻦْ
ﺧَﻠْﻔِﻪِ ﺭَﺻَﺪًﺍ
ﻟِّﻴَﻌْﻠَﻢَ ﺃَﻥ ﻗَﺪْ ﺃَﺑْﻠَﻐُﻮﺍ ﺭِﺳَﺎﻟَﺎﺕِ ﺭَﺑِّﻬِﻢْ ﻭَﺃَﺣَﺎﻁَ ﺑِﻤَﺎ ﻟَﺪَﻳْﻬِﻢْ
ﻭَﺃَﺣْﺼَﻰ ﻛُﻞَّ ﺷَﻲْﺀٍ ﻋَﺪَﺩًﺍ
«(እርሱ) ሩቁን ምስጢር ዐዋቂ ነው፡፡ በምስጢሩም ላይ አንድንም አያሳውቅም፡፡ከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ (ለሌላ አይገልጽም)፡፡ እርሱም ከስተፊቱም ከስተኋላውም ጠባቂዎችን
ያደርግለታል፡፡ እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር ዕውቀቱ የከበበና ነገሩንም ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲኾን የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ መኾናቸውን ያውቅ ዘንድ (ጠባቂ ያደርጋል)፡፡›› (አል ጂን 26-28)
ይህ ግን አንፃራዊ ነው:: ማለትም “ገይብ” ከማያውቁት ሰዎች አንፃር ነው፡፡ በጥቅሉ ገይብ (የሩቅ ምስጢር) ከአላህ ውጭ ማንም ሊያውቀው አይችልም፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ሙስሊም የሩቅ ምስጢር አውቃለው በማለት በሀሰት በማጭበርበር እራሳቸ ጠመው ሌላውን የሚያጠሙ ድግምተኞችንና ኮከብ ቆጣሪ የመሳሰሉ ዋሾዎችን ሊጠነቀቅ ይገባል::

Post a Comment

0 Comments