Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አላህ ሆይ! ወደ ዲናችን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሀባዎች ወደ ነበሩበት መልሰን፡፡

አላህ ሆይ! ወደ ዲናችን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሀባዎች ወደ ነበሩበት መልሰን፡፡
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጠላቶች ሙስሊሞች ላይ እንደሚረባረቡ በተናገሩበት ሃዲስ ውስጥ እንዲህ ሲሉ ጨረሱ
‹‹አላህ ይህን ፈተና አያነሳላችሁም ወደ ዲናችሁ እስካልተመለሳችሁ ድረስ›› አሉ፡፡
ዲናችን የተገነባባቸው መሰረቶች ውስጥ
1) አላህን አንድ አድርጎ መገዛት፤ ከእርሱ ውጭ ያሉትን መራቅ፤ ከአላህ ውጭ ባሉት መካድ፤
2) የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና አጥብቆ መያዝ፤ በዲን ላይ የተጨመሩ ቢድዓዎችን ሁሉ መራቅ፤
3) የሰሃባዎችን እና ሰለፎችን አረዳድ አጥብቆ መያዝ፤ መጤ ፍልስፍናዎችን መራቅ፤
4) እውቀትን መፈለግ፤ ከእውቀት እና ከአዋቂዎች ባይተዋር አለመሆን፤
4) ለቤተሰብ ጥሩ መዋል፤ እነሱን አለመበደል፤
5) ጋብቻን መመስረት፤ ዝሙትን መራቅ፤
እና በጣም ብዙ በዚህች አጭር ፅሁፍ ተጠቅሰው የማያልቁ እውቀትን በመቅሰም በትግስት ሊታወቁ የሚችሉ ብዙ ነገሮችን ይዟል ዲናችን
ስለዚህ ምንም ወዳልጎደለው ሙሉ እስልምና ሃይማኖታችን ጠቅለል ብለን እንግባ፡፡
አላህ ሆይ የዲንን ትክክለኛ አረዳድ አስገንዝበን፡፡

Post a Comment

0 Comments