Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሴት ልጅ ካለወት ታድለዋል!

ሴት ልጅ ካለወት ታድለዋል!
በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እና ሩህሩህ በሆነው እጀምራለሁ
የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلمእንዲህ ብለዋል የሴት ልጆችን ከባድ ደረጃ በመግለፅ እንክብካቤ እንዲደረግላቸው በማበረታታት ፣(ከእናንተ መካከል በእነዚህ ሴቶች የተሞከረና፣ለእነርሱ መልካምን የዋለ ለእሳት ከለላ ይሆኑታል።)ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
قال النبي صلى الله عليه وسلم (من ابتلي من هذه البنات بشيء فأحسن إليهم كن له ستر من النار)
ሴት ልጅን ማስተማር
ማህበረሰብን ማስተማር ነው ።ሴት ልጅ እናት ነች።ሴት ልጅ የልጆች የመጀመሪያ ትምህርት ቤት ነች።ኢስላማዊም ይሁን የአካዳሚ ትምህርትን ማስተማር አለብን ።ሃላፊነት የሚሰማው ትውልድ ታበረክትልን ዘንድ ።በመልካም ሴት ታንፀው የሚያድጉ ልጆች ለወደፊቱ ማህበረሰብ የጀርባ አጥንት ናቸውና ።
ሴት ልጅ ከተማረች መብትና ግዴታዋን ስለምታውቅ የባልዋን፣የወላጆችዋን ፣የልጆችዋን፣የዘመዶችዋንና፣የጎረቤቶቿን ሃቅ አላህን በሚያስደስት መልኩ ትጠብቃለች ።የራሷንም መብትና ግዴታ ስለምታውቅ ታስከብራለች።
ስለዚህ ለራስዎ፣ለቤተሰብዎ እንዲሁም ለማህበረሰቡ ሲሉ ከጎኗ በመሆን በማረም፣በማድነቅ፣በማስተማር እና በመርዳት ልያግዟት ይገባል።
ውድ አባት ሆይ ልጅዎትን ዲንን በማሳወቅ የተጣለብዎትን ከባድ ሃላፊነት ለመወጣት ከአላህ ከባድ ምንዳ ለማግኘት አሁኑኑ ይንቀሳቀሳሉ ።አላህ ብርታቱን ይስጠወት።