Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ካለ ወሊይ ፍቃድ ኒካህ ተቀባይነት የለውም!

ካለ ወሊይ ፍቃድ ኒካህ ተቀባይነት የለውም!
قال النبي صلى الله عليه وسلم : (لا نكاح إلا بولي) رواه أبو داود (2085 ) والترمذي (1101 ) وابن ماجه (1881) من حديث أبي موسى الأشعري ، وصححه الألباني في صحيح الترمذي.
አቡ ሙሳ ባስተላለፉት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «ያለ ሴቷ ቅርብ ሀላፊ ዘመድ (ወልይ) ፈቃድና ይሁንታ ጋብቻ አይፈፀምም።» አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚ፣ ኢብን ማጃህ ዘግበውታል አልባኒም ሰሂህ ብለውታል።
በሌላም ሀዲስ ተመሳሳይ መልእክት እናገኛለን፤
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : ( أيما امرأة نكحت بغير إذن وليها فنكاحها باطل ، فنكاحها باطل ، فنكاحها باطل ) رواه أحمد ( 24417) وأبو داود (2083) والترمذي (1102) وصححه الألباني في صحيح الجامع برقم 2709 .
«ያለ ቅርብ ዘመዷ (ወሊይ) ፈቃድ ጋብቻ የፈፀመች ሴት ጋብቻዋ ውድቅ ነው!!» ይህን ቃል ሦስት ጊዜ ደጋግመውታል
አል ኢማም አህመድ አቡዳውድና ቲርሚዚ ዘግበውታል፤ አልባኒም ሰሂሁልጃሚእ ላይ በቁጥር 2709 ሰሂህነቱን አረጋግጠዋል።