Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሡሉ ሠላሣ ክፍል አስራ አምስት

'‎አሠላሙ አለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካቱ

ኡሡሉ ሠላሣ ክፍል አስራ አምስት

የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ ይላል

ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም. ብሎ የመመስከር መረጃ

አላህ እንዲህ ይላል

« አላህ በማስተካከል የቆመ (አስተናባሪ) ሲሆን ከእርሡ በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ መሰከረ መላእክቶች እና
የእውቀት ባለቤቶችም እንጀዚሁ መሠከሩ ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የለም አሸናፊ እና ጥበበኛ ነው » አል ኢምራን

የላኢላሀ ኢለላህ ትርጉም ፧ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም. ( ﻻ ﺇﻟﻪ ) ከአላህ ውጪ የሚመለኩ አማልክትን በአጠቃላይ ይሽራ. ( ( ﺇﻻ ﺍﻟﻠﻪ
ኢባዳን በአጠቃላይ ለአላህ ያፀድቃል ፡ በመፈጠሩ ላይ አጋር እንደሌለው በአምልኮውም ላይ አጋር አይኖረውም
የላኢላሀ ኢለላህን ትርጓሜ ግልፅ ሚያደርጉ መረጃዎች ውስጥ

አላህ እንዲህ ይላል «« ኢብራሒም ለህዝቦቹ እና ለአባቱ እኔ ከናንተ እና ከምትገዟቸው የጠራሁ ነኝ (26)) ያ!
የፈጠረኝ ሢቀር እሡም. ይመራኛል (27) ንግግሯን ሠዎች ይመለሡ ዘንዳ በዘሮቹ ስር ቀሪ አደረጋት» ዙህሩፍ

አላህ እንዲህ ይላል « እናንተ የመፀሀፍ ባልተቤቶች ሆይ በኛና በእናንተ መካከል እኩኩል ወደ ምታደርግ ቃል . አላህ ውጪ ሌላን ላመልክ በሡም ምንም ላናጋራ
ከፊላችን ከፊሉን ከአላህ ውጤ ቢጤ አድርጎ ላይ ኑ! በላቸው―» አል ኢምራን

------**---------------
አጭር ማብራርያ

★ ላኢላሀ ኢለላህ

ትርጉም ፦ 

★ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ማለት ነው

★አንዳንድ የተሣሣቱ ሠዎች ላኢላሀ ኢለላህ የምትለው ቃል ሩቡብያን ታመላክታለች ሢሉ ያስተምራሉ እውን እነሡ እንደሚሉት ላኢላሀ ኢለላህ ሩቡብያን ነው የምታመለክተው??  

✔ እነሡ እኔደሚሉት ቢሆን ኖሮ ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ከመካ ሙሽሪኮች ጋር ባልተጋጩ ነበር ምክንያቱም የመካ ሙሽሪኮች በሩቡብያው ያምኑ ነበርና  

ላኢላሀ ኢለላህ ስምንት ሸርጥ እና ሁለት አርካን አላት እነሡም

የላኢላሀ ኢለላህ መስፈርቶች 

1. የመሀይምነት ተፃራሪ የሆነው
ይህም ማለት የዚህ ቃል መልዕክት እና ቃሉ ዉድቅ የሚያደርጋቸዉንና እና
የሚያፀድቃቸውን ነገሮች ማወቅ ማለት ነው፡፡ ማለትም አላህ በእውነት
ሊያመልኩት የሚገባ እና ብቻውን የሚመለክ አምላክ መሆኑን ከእርሱ
ውጭ ያሉ ሁሉ አምልኮ
የማይገባቸው ባጢል አማልክት መሆናቸውን ማወቅ ሲሆን ካለ እዉቀት
የሚሰጥ ምስክርነት ተቀባይነት የለዉም። ለዚህም ማስረጃው ቀጣዩ የአላህ ቃል ነው፡፡

(እነዚያም ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸዉ እነሱ የሚያውቁ ሆነው በእውነት
ከመሰከሩት በስተቀር ምልጃን አይችሉም) (አል-ዙኸሩፍ 86)

2. የጥርጥር ተፃራሪ የሆነው እርግጠኝነት
ይህ መስፈርት የሚያመለክተው (ላ ኢላሀ ኢለላህ) የሚለውን ምስክርነት ከልቡ
በመቀበል አላህ ብቻውን የሚመለክ አምላክ መሆኑን እና ከእርሱ ውጭ ያሉ
አማልክት በሙሉ ከንቱ መሆናቸውን በአንደበት እንደሚናገረው ሁሉ
በልቡም ማረጋገጥ እንዳለበት ነው። እርግጥኝነት ከሌለ ጥርጥር ዉስጥ ነዉና
እምነቱ ከመናፍቃን እምነት
አይለይም። 
አላህ እንዲህ ይላል፡-

({እዉነተኞቹ} ምእመናን እነዚያ በአላህና በመልእክተኛዉ ያመኑት ከዚያም
ያልተጠረጠሩት ናቸው) (አል-ሑጁራት 15)

3. የማጋራት ተፃራሪ የሆነው ማጥራት (ኢኽላስ)
የላኢላሀ ኢለላህን የምስክርነት ቃል የሰጠ ሰው ስራውን ከሽርክ ማጥራት
አለበት፣ የሚያከናውናቸውን ተግባራቶችም ሆነ የሚናገራቸውን
ንግግሮች በሙሉ ለአላህ ብቻ
ብሎ መፈጸም አለበት። በዚህ የምስክርነት ቃል የዱንያ ጥቅማጥቅሞችንና
ዝናን ከመከጀል ለይዩልኝ እና ይስሙልኝ ከመስራት መጥራት አለበት፡፡ ለዝና
ወይም ለዱንያዊ ጥቅም ተብሎ የሚፈፀም ተግባር ከአላህ ጋር ሌሎችን በአምልኮ ማጋራት በመሆኑ ምንዳን አያስገኝም።የሚያስከትለውም ቅጣት
ብርቱ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ( ﷺ ) እንዲህ ብለዋል 
‹‹የቂያማ ዕለት የኔን ምልጃ በማግኘት
ዕድለኛ የሚሆነው ከልቡ ጥርት አድርጎ ላ ኢላሀ ኢለላህ ያለ ሰው ነው፡፡››
ቡኻሪ ዘግበዉታል፡፡

4. የውሸት ተፃራሪ የሆነው እውነተኛነት
ላ ኢላሀ ኢለላህ ብሎ የሚመሰክረው ግለሰብ በልቡ የሚያምንበት
እምነትም ሆነ በአንደበቱ የሚናገረው ንግግር እውነትን የተላበሰ መሆን
አለበት።  ካልሆነ ውሸትን
የሚያራምድ አታላይ እንጂ እዉነተኛ መስካሪ አይሆንም። የአላህ መልእክተኛ( ﷺ ) እንዲህ ይላሉ

‹‹ማንኛውም ከልቡ በእውነተኛነት በአላህ ብቸኛ አምላክነትና በሙሐመድ ( ﷺ) 
መልዕክተኝነት የሚመሰክር ሰው አላህ ከእሳት እርምይለዋል››  (ቡኻሪ ዘግበዉታል)

5. የመጥላት ተፃራሪ የሆነው መውደድ
ላ ኢላሀ ኢለላህ ብሎ የሚመሰክረው ግለሰብ ይህ ምስክርነቱ ግዴታ
የሚያደርጋ ቸውን ነገሮች ሁሉ መውደድ ይገባዋል። ወዶ እና ፈቅዶ ካልመሰከረ ተገዶ ነዉና ምስክርነቱ ተቀባይነት የለዉም። ላኢላሀ ኢለላህ የሚለውን
የምስክርነት ቃል ፣ አላህን እንዲሁም አላህን በብቸኝነት የሚያመልኩትን የተውሂድ ሰዎችን መውደድ
ነው፡፡ አላህ እንዲህ ይላል 

(ከሰዎችም አላህን እንደሚወዱ የሚወዷቸው ሆነው ከአላህ ሌላ
ባለንጣዎችን የሚይዙ አሉ፡፡ እነዚያ ያመኑትም አላህን በመውደድ
(ከነርሱ) ይበልጥ
የበረቱ ናቸው) 
አል በቀራህ 165

6. የመተው ተፃራሪ የሆነው መታዘዝ
ይህ ማለት ‹‹ላ ኢላሀ ኢለላህ›› የሚለው የምስክርነት ቃልለሚያመላክታቸው
ትዕዛዛትና ክልከላዎች ሙሉ ታዛዥ ተከታይና ተናናሽ መሆን ነው፡፡ አላህ
 እንዲህ ይላል፡-

(እርሱ መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን (በመታዘዝና በመተናነስ)
ወደ አላህየሚሰጥ ሰው
ጠንካራን ገመድ በእርግጥ ጨበጠ...) ሉቅማን 22

7. የተቃውሞ ተፃራሪ የሆነው መቀበል
ላ ኢላሀ ኢለላህ ብሎ የሚመሰክረው ሰው ቃሉ ግዴታ የሚያደርጋቸዉን ነገሮች
በሙሉ (አላህን በብቸኝነት ማምለክን እና ለሌላ ለፍጡራን የሚከናወኑ አምልኮቶችን
መተው) ከልቡ አምኖ በአንደበቱ መስክሮ መቀበል አለበት። ይህንን መስፈርት ያላሟላ እምቢተኛ ነዉና መሰከረ አይባልም።አላህ ኩራተኛነታቸውን
እና አለመቀበላቸውን እንዲህ በማለት ከገለፃቸው ሙሽሪኮች ይሆናል፡፡ (እነርሱ፤ ከአላህ ሌላ አምልኮ የሚገባው ሆኖ የሚመለክ አምላክ የለም› በተባሉ ጊዜ ይኮሩ ነበር፡፡ እኛ ለእብድ ባለቅኔ ብለን
አማልክቶቻችንን የምንተው ነን
ይሉም ነበር፡፡) (አልሷፋት 35-36)

8. ከአላህ ውጪ የሚመለኩ አማልክትን መካድ (ማስተባበል) ናቸው።

ከላይ እንደተመለከትነው ከአላህ ሌላ አምልኮ የሚገባው እንደሌለ የምናረጋግጥበት ቃለ ተውሂድ ይህንን መስፈርት በዉስጡ ያካትታል። 

 ከባዕድ አምልኮ ያልተላቀቀ ሰው በአላህ አላመነም!!! 
የላኢላሀ ኢለላህ አርካኖች
① ( ﻻ ﺇﻟﻪ )
ከአላህ ውጪ የሚመለኩልአማልክትን በአጠቃላይ ይሽራል.
②( ( ﺇﻻ ﺍﻟﻠﻪ

በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

share ማድረጎን እንዳይረሡ‎'
አሠላሙ አለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካቱ

share ማድረጎን እንዳይረሡ