Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥንታውያኑ ቻይናውያን በሰላም መኖር ቢያምራቸው ታላቁን የቻይና ግንብ ገነቡ .............

ጥንታውያኑ ቻይናውያን በሰላም መኖር ቢያምራቸው ታላቁን የቻይና ግንብ ገነቡ፡፡ ቁመቱ ክፍ ያለ ከመሆኑ የተነሳ ማንም አይወጣበትም፣ ማንም አይደርስብንም ብለው አምነዋል፡፡ ነገር ግን...
ግንቡ በተገነባ የመጀመሪያው መቶ አመት ውስጥ ብቻ ቻይና ሶስት ጊዜ ለጠላት ወረራ ተጋለጠች፡፡ በያንዳንዱ ወረራ ጊዜ ግዙፉ ወራሪ ሀይል ታላቁን የቻይና ግንብ መስበርም መንጠላጠልም አላስፈለገውም ነበር፡፡ እናስ? ሰተት ብለው ነበር በበሩ የሚገቡት፡፡ እንዴት አድርገው? ቀላል ነበር፡፡ ለግንቡ በረኞች፣ ለዘበኞቹ ጉቦ ይሰጣሉ፡፡ ከዚያ ነገሩ ሁሉ ያልቃል፡፡
ቻይናውያን በዙሪያቸው ግዙፍ ግንብ በመገንባት ሲጠመዱ ዘበኛ መገንባት ግን ዘንግተዋል፡፡ ስብእናን መገንባት ሌሎች ነገሮችን ከመገንባት የሚቀድም ነገር ነው፡፡ ይሄ ጉዳይ ትኩረት ሊቸረው የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ አንዱ የምስራቁን ታሪክና ትውፊት የሚያጠና ተመራማሪ እንዲህ ይላል፡- “የአንድን ህዝብ ስልጣኔ ማፈራረስ ከፈልግክ ሶስት መንገዶች አሉልህ፡-
1. ቤተሰብን ማፍረስ
2. የትምህርት ስርአቱን ማፍረስ
3. መልካም ምሳሌና አርኣያ የሆኑ ሰዎችን ስብእናቸውን ማጠልሸት
ቤተሰብን ለማፍረስ እናት ሚናዋን እንዳትወጣ አድርጋት፡፡ “የቤት እመቤት” በመባሏ እንድታፍር አድርጋት፡፡
የትምህርት ስርኣቱን ለማፍረስ አስተማሪው ላይ አነጣጥር፡፡ ህብረተሰቡ ጋር ያለውን ቦታ አሳጣው፡፡ ተማሪዎቹ ይንቁት ዘንድ ደረጃውን አውርደው፡፡
አርአያዎችን ለማፍረስ ዓሊሞች ላይ አነጣጥር፡፡ አንቋሻቸው፡፡ ዋጋ አሳጣቸው፡፡ ማንነታቸውን ሰዎች እንዲጠራጠሩ አድርግ፡፡ ያኔ ሰዎች አይሰሟቸውም፡፡ ምሳሌም አያደርጓቸውም፡፡
• አስተዋይ እናት ከጠፋች
• ከልቡ የሚሰራ አስተማሪ ከጠፋ
• ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉት ዋጋ ካጡ
ማነው ትውልዱን በመልካም ስነ-ምግባር የሚያንፀው?
በ “ሀዛ ሚንሀጂ ሰለፊ አሠሪ” ተፅፎ
በኢብኑ ሙነወር ተተረጎመ