Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስለ ሀይድ ክፍል - 5

‎♦ ስለ ሀይድ  ክፍል - 5 ♦ 

የተንቢሃት ልዩ ሳምንታዊ መልዕክት ቁ•8

የእንስቶች ወርሃዊው ዙር ህግጋት  ```````````````````````````````````````
     የወር አበባ (ሀይድ) ከምን 
         󾀿 ያቅበኛል ? 󾀿 
            """""""""""""""""""""
✅ ሀይድን በተመለከተ የተለያዩ ነጥቦችን መዳሰስ በጀመርነው መሰረት በዛሬው መልዕክታችን ሀይድ ላይ ያለች እንስት ከምን መታቀብ እንደሚገባት እንመለከታለን።

✅ለሀይድ ወደ20 የሚደርሱ አህካሞች ይገኛሉ ከነዚያም መካከል በጣም አሳሳቢውንና ብዙሃን ሊያውቁትና ሊገነዘቡት የሚገባውን በማስቀደም እንጀምራለን።

① ሰላት
    ```````
   የወር አበባ ላይ ላለች እንስት የፍላጎትንም ይሁን የግዴታ ሰላትን መስገዷ ይከለከላል።

󾮜 ከሀይድ በነፃችበት ወቅት የሰላቱ ወቅት አንድ ረከዓ የሚያሰግድ ያህል ካልቀራት በስተቀርም እንድትሰግድ አትገደድም። 

   ይህም የሰላቱ ጅምር ወቅት ላይ ይሁን የመጨረሻው ወቅትም ላይ ቢሆን የደረሰችው ሙሉ አንድ ረከዓ የሚያሰግዳት ግዜ እያለ እሷ ንፁህ ከሆነች ቶሎ መስገድ አለባት።

   ምሳሌ:-

¹•  አንዲት እንስት መግሪብ ከገባ በኋላ ቢያንስ አንድ ረከዓ የሚያሰግድ ያህል ወቅት ከሄደ በኋላ ሀይድ ቢጀምራት ወደፊት ሀይዷን ካበቃችና ከፀዳች በኋላ ያንን የመግሪብ ሰላት ቀዷ ማውጣት ግድ ይሆንባታል፤ ምክንያቱም ንፁህ እያለች ወቅቱ ገብቷል ፤ እሷም ቢያንስ አንድ ረከዓ የመስገድ ዕድል ነበራት።

ለዚህም ምሳሌ:-

•> የመግሪብ ወቅት የሚጀምረው ከምሽቱ 12:00 ቢሆንና ሀይዷ የጀመራት 12:05 ቢሆን ወደፊት ከሀይድ ስትጠራ ያንን መግሪብ ሰግዳ ትተካለች።

󾮜  ነገር ግን መግሪብ እንደገባ በቅፅበት ወዲያው ሀይድ ቢጀምራት እዳ የመክፈል ግደፀታ የለባትም።

²• ከሀይዷ የነፃችው የሰላት ወቅቱ ማብቂያ ከሆነ

ምሳሌ:-

:> ፀሃይ ሳትወጣ አንድ ረከዓ ማሰገድ የሚያስችል ወቅት እያላት ከሀይዷ ከነፃችና ትንሽ ቆይቶም ፀሃይ ቢወጣ በመሰረቱ የፈጅር ወቅት አብቅቷል ነገር ግን ወቅቱ ሳያበቃ ስለነፃች ቀዷ ታወጣለች። ማለትም

   ፀሃይ ብቅ ብላ የፈጅር ወቅት የሚያበቃው ንጋት 12:00 ቢሆንና 11:55 ላይ ከሀይዷ ከነፃች እዳ ኣለባትና ከነጋም ቦኋላ ታጥባ ቀዷ ታወጣለች (ትሰግዳለች)።

󾮜 ነገር ግን ፀሃይ ልትወጣ ስትቀርብ በቅፅበት ወዲያው ከሀይዷ ከጠራች ቀዷ የለባትም።

    ለሁቱም ምሳሌዎች አስረጅ የሚሆነን የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በነገሩን መሰረት ቡኻሪና ሙስሊም ረሂመሁሙላህ የዘገቡት ሀዲስ እነደዲህ ይላል:

” من أدرك ركعة من الصلاة فقد أدرك الصلاة “   متفق عليه

« ከሰላት አንድን ረከዓ የደረሰ ሰላቱ ላይ ደርሷል »

   ማለትም ወቅቱ ሳያልፍ መጨረሻው ላይ አንድ ረከዓ የሚያሰግድ ወቅት አግኝቶ ሰላት የጀመረ ሰው … 
 ምንም እንኳን ሰላቱን ሰግዶ ሲያበቃ የሰላቱ ወቅት ያለፈም ቢሆን እንኳ እንዳለፈበት አይቆጠርበትም። 

    አንዷን ረከዓ የሰገደው ወቅቱ ሳያበቃ ነውና።

   በመሆኑም አንድ ረከዓ የሚያሰግድ ያህል ደቂቃ ሳይኖረው ሰላቱን የሰገደ በወቅቱ እንደሰገደ አይቆጠርለትምም። 
        ~~~``````````~~~

    በሚቀጥለው ርእሳችን ሀይድ ላይ ያለች እንስት ዚክርና ቁርኣንን መቅራት በተመለከተ ሊኖራት የሚገባውን ግንዛቤ እናካፍላችኋለን።

وصلى الله على محمد وعلى آله وصحبه وسلم.
____________
#ተከታዩን-ሊንክ-በመጫን-ፔጁን-ላይክ(Like)-ያድርጉ

www.facebook.com/tenbihat

               إن شاء الله ይቀጥላል
_________
󾔧Abufewzan احمد سيرة
ረቢዕ አልሳኒ 1436    29Jan15
…‎
ስለ ሀይድ ክፍል - 5
የተንቢሃት ልዩ ሳምንታዊ መልዕክት ቁ•8
የእንስቶች ወርሃዊው ዙር ህግጋት ```````````````````````````````````````
የወር አበባ (ሀይድ) ከምን
ያቅበኛል ?
"""""""""""""""""""""
✅ ሀይድን በተመለከተ የተለያዩ ነጥቦችን መዳሰስ በጀመርነው መሰረት በዛሬው መልዕክታችን ሀይድ ላይ ያለች እንስት ከምን መታቀብ እንደሚገባት እንመለከታለን።

✅ለሀይድ ወደ20 የሚደርሱ አህካሞች ይገኛሉ ከነዚያም መካከል በጣም አሳሳቢውንና ብዙሃን ሊያውቁትና ሊገነዘቡት የሚገባውን በማስቀደም እንጀምራለን።
① ሰላት
```````
የወር አበባ ላይ ላለች እንስት የፍላጎትንም ይሁን የግዴታ ሰላትን መስገዷ ይከለከላል።
ከሀይድ በነፃችበት ወቅት የሰላቱ ወቅት አንድ ረከዓ የሚያሰግድ ያህል ካልቀራት በስተቀርም እንድትሰግድ አትገደድም።
ይህም የሰላቱ ጅምር ወቅት ላይ ይሁን የመጨረሻው ወቅትም ላይ ቢሆን የደረሰችው ሙሉ አንድ ረከዓ የሚያሰግዳት ግዜ እያለ እሷ ንፁህ ከሆነች ቶሎ መስገድ አለባት።
ምሳሌ:-
¹• አንዲት እንስት መግሪብ ከገባ በኋላ ቢያንስ አንድ ረከዓ የሚያሰግድ ያህል ወቅት ከሄደ በኋላ ሀይድ ቢጀምራት ወደፊት ሀይዷን ካበቃችና ከፀዳች በኋላ ያንን የመግሪብ ሰላት ቀዷ ማውጣት ግድ ይሆንባታል፤ ምክንያቱም ንፁህ እያለች ወቅቱ ገብቷል ፤ እሷም ቢያንስ አንድ ረከዓ የመስገድ ዕድል ነበራት።
ለዚህም ምሳሌ:-
•> የመግሪብ ወቅት የሚጀምረው ከምሽቱ 12:00 ቢሆንና ሀይዷ የጀመራት 12:05 ቢሆን ወደፊት ከሀይድ ስትጠራ ያንን መግሪብ ሰግዳ ትተካለች።
ነገር ግን መግሪብ እንደገባ በቅፅበት ወዲያው ሀይድ ቢጀምራት እዳ የመክፈል ግደፀታ የለባትም።
²• ከሀይዷ የነፃችው የሰላት ወቅቱ ማብቂያ ከሆነ
ምሳሌ:-
:> ፀሃይ ሳትወጣ አንድ ረከዓ ማሰገድ የሚያስችል ወቅት እያላት ከሀይዷ ከነፃችና ትንሽ ቆይቶም ፀሃይ ቢወጣ በመሰረቱ የፈጅር ወቅት አብቅቷል ነገር ግን ወቅቱ ሳያበቃ ስለነፃች ቀዷ ታወጣለች። ማለትም
ፀሃይ ብቅ ብላ የፈጅር ወቅት የሚያበቃው ንጋት 12:00 ቢሆንና 11:55 ላይ ከሀይዷ ከነፃች እዳ ኣለባትና ከነጋም ቦኋላ ታጥባ ቀዷ ታወጣለች (ትሰግዳለች)።
ነገር ግን ፀሃይ ልትወጣ ስትቀርብ በቅፅበት ወዲያው ከሀይዷ ከጠራች ቀዷ የለባትም።
ለሁቱም ምሳሌዎች አስረጅ የሚሆነን የአላህ መልዕክተኛ ﷺ በነገሩን መሰረት ቡኻሪና ሙስሊም ረሂመሁሙላህ የዘገቡት ሀዲስ እነደዲህ ይላል:
” من أدرك ركعة من الصلاة فقد أدرك الصلاة “ متفق عليه
« ከሰላት አንድን ረከዓ የደረሰ ሰላቱ ላይ ደርሷል »
ማለትም ወቅቱ ሳያልፍ መጨረሻው ላይ አንድ ረከዓ የሚያሰግድ ወቅት አግኝቶ ሰላት የጀመረ ሰው …
ምንም እንኳን ሰላቱን ሰግዶ ሲያበቃ የሰላቱ ወቅት ያለፈም ቢሆን እንኳ እንዳለፈበት አይቆጠርበትም።
አንዷን ረከዓ የሰገደው ወቅቱ ሳያበቃ ነውና።
በመሆኑም አንድ ረከዓ የሚያሰግድ ያህል ደቂቃ ሳይኖረው ሰላቱን የሰገደ በወቅቱ እንደሰገደ አይቆጠርለትምም።
~~~``````````~~~
በሚቀጥለው ርእሳችን ሀይድ ላይ ያለች እንስት ዚክርና ቁርኣንን መቅራት በተመለከተ ሊኖራት የሚገባውን ግንዛቤ እናካፍላችኋለን።
وصلى الله على محمد وعلى آله وصحبه وسلم.
____________
‪#‎ተከታዩን‬-ሊንክ-በመጫን-ፔጁን-ላይክ(Like)-ያድርጉ
www.facebook.com/tenbihat
إن شاء الله ይቀጥላል
_________
Abufewzan احمد سيرة
ረቢዕ አልሳኒ 1436 29Jan15