Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሲሕር (ድግምት ) እና አደገኝነቱ

بسم الله الرحمن الرحيم
ሲሕር (ድግምት ) እና አደገኝነቱ
ሲሕር የተለያዩ ነገሮችን በመቋጠርና እሱ ላይም "እትፍ" በማለት በብዙ መልኩ የሚሰራ ልብና ዉጫዊ የሰውነት አካላት ላይ (በአሏህ ፈቃድ ) ተጽኖ ሊያሳድር የሚችል ሸይጣናዊ ተግባር ነው::
ሲሕር (ድግምት) በምርመራ የማይገኝ በሽታ፣ ሞት፣ ባልና ሚስትን ማለያየት ወዘተ ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል::
ሁሉም የሲሕር አይነቶች በዲናችን ሐራምና የተከለከሉ ናቸው ሲሕር ከከበባድ ወንጀሎች መካከልም አንዱ ነው
ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል
( اجتنبوا السبع الموبقات قالوا: يارسول الله وما هن؟ قال: الإشراك بالله ..... والسحر....) متفق عليه
" የሰው ልጅን ለጥፋት ( አደጋ) የሚዳርጉ ሰባት ወንጀሎችን ራቁ አሉ፥ ሰሓቦችም እነማን ናቸው አንቱ የአሏህ መልእክተኛ? ብለው ጠየቋቸው: እሳቸውም ፥ በአሏህ ማጋራት፣ ድግምት እና….." ወዘተ ሁሉንም ዘረዘሩላቸ ው
ድግምትን አስመልክቶ አሏህ የሚከተለውን ብሏል
[[ وما يعلمان من أحد حتى يقولا إنما نحن فتنة فلا تكفر فيتعلمون منهما ما يفرقون به بين المرء وزوجه وما هم بضآرين به من أحد إلا بإذن الله ]] البقرة 102
" ሃሩትና ማሩት፥ እኛ መፈተኛ ነን ድግምትን በመማር ኩፍር (ክህደት) ላይ አትውደቅ ብለው ሳያስጠነቅቁ ማንንም አያስተምሩም:: ከነሱም ባልና ሚስትን የሚያፋቱበትን ሲሕር ይማራሉ በድግምታቸውም ያለ አሏህ ፈቃድ ማንንም አይጎዱም " ሱረቱል በቀረህ 102
ድግምትን መስራትና መማር ከባድ ወንጀል እንደሆነው ሁሉ ድግምተኛን ሄዶ መጠየቅም እንደዚሁ ከባድ ወንጀል ነው:: ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ይሄን አስመልክተው የሚከተለውን ብለዋል፥
" ድግምተኛ ወይም ጠንቋይን የጠየቀና የሚለውንም አምኖ የተቀበለ በነቢዩ ሙሐመድ ላይ በወረደው (ሸሪዓና ቁርኣን) ክዷል (ከፍሯል) ብለዋል
የሚናገረውን አምነው ባይቀበሉ እንኳ እንዲሁ ለሙከራ ወይም ለማጣራት ወዘተ… ብሎ የሄደ እንደሆነ፥ የአርባ ቀናት ሰላቱን አሏህ እንደማይቀበለው ተናግረዋል::
ሲሕር የተሰራበት ሰው ምን ማድረግ ይጠበቅበታል??
በመጀመሪያ ደረጃ አሏህ ያመጣው ፈተና መሆኑን አውቆ መታገስ ይጠበቅበታል:: በመቀጠልም በአሏህ መመካትና ዱዓ ማብዛት፣ እራስን በቁርኣን ለመፈወስ መሞከር ካልተቻለም ከሸሪዓ በማይጋጭ መልኩ የሚቀሩ ሰዎችን ፈልጎ ሩቃ ማስደረግ፣ዚክር ላይ መበርታት በተለይ ደግሞ የጠዋትና ማታ ዚክሮችን ማዘውተር እና በተቻለ ያክል ዲን ላይ ጠንከር ማለት ይጠበቅበታል
ይህ በእንዲህ እንዳለ ብዙ ሰዎች ድግምትን በድግምት ማክሸፍ፣ ባልና ሚስት እንዲፋቀሩ ተብሎ የሚሰራን ድግምት ወዘተ በተመሳሳይ ነጥቦች ዙሪያ ጥያቄዎችን ያነሳሉ?
የመጀመሪያን በተመለከተ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል
" ድግምትን በድግምት ማክሽፍ ሰይጣናዊ ተግባር ነው" ብለዋል
ሁለተኛውም በሸሪዓችን አይቻልም ከላይ ከተጠቀሰው ሲሕር የሚመደብ ነው

ሙስሊሞች ሆይ፥ እምነታችሁን ጠብቁ አካላችሁን ለማከም ብላችሁ ዋናውና ትልቁን ልባችሁን (ዲናችሁን) እንዳታበላሹ!
ወሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏህ
"አሕመድ ኣደም"
www.fb.com/nosihr