Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሰው አይን (ቡዳ) የበላው ሰው እንዴት ይፈወሳል?

የሰው አይን (ቡዳ) የበላው ሰው እንዴት ይፈወሳል?
የሰው አይን (ቡዳ) ያለና የሚያጋጥም ነው። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፤ (الْعَيْنُ حَقٌّ) «በአይን (መጎዳት) ያለ እውነታ ነው» ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።
ይህ ሰው የሚታወቅ ከሆነና ፍቃደኛ ከሆነ ውዱእ እንዲያደርግ ወይም ገላውን እንዲታጠብ ተደርጎ ውሀውን ለፈውስ መጠቀም ይቻላል። ማንኛውም ሰው እይታው የጎዳውን ሰው ካወቀ ወይም ከጠረጠረ ውዱእ እንዲያደርግለት የመጠየቅ መብት አለው።
ሸይኽ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፤ «የሰው አይን ለጉዳት የዳረገው ሰው ሊወስድ የሚገባውን እርምጃ ምንድነው? ቁርአን በመቅራት ይታከማል፤ በእይታው የጎዳው ሰው ከታወቀ ውዱእ እንዲያደርግ ይጠየቅና ውዱእ ሲያደርግ የተንጠባጠበውን ውሀ ለበሽተኛው ይሰጣል። ጀርባውና ራሱ ላይ ይደፋበታል። እንዲጠጣም ይደረጋል። በአላህ ፍቃድ በዚህ ይፈወሳል።
ለኪታቡ ተውሂድ በሰጡት ማብራሪያ ላይም እንዲህ ብለዋል፤ «ሌላም መንገድ አለ እሱንም ከመጠቀም ምንም የሚከለክል ነገር የለም። እሱም፤ እንደ ኮፍያ ከነቴራና የውስጥ ሱሪ ያሉ ከሰውነት ጋር የሚነካኩ የውስጥ ልብሶችን ወይም በባዶ እግሩ የሄደበትን ንፁህ አፈር ተወስዶ ዉሀ ይነከርና በዛ ውሀ የታመመው ሰው ላይ ይረጫል ወይም ይጠጣዋል፤ ይህም የተሞከረ ነው።» መጅሙእ ሙአለፋት ኢብኑ ኡሰይሚን 9/88
ይህ የመጨረሻው መፍትሄ ይበልጥ ጠቃሚ የሚሆነው ይህ ሰው ውዱእ ለማድረግ ወይም ለመታጠብ ዝግጁ ካልሆነ ወይም ካፊር ከሆነ ወይም ደግሞ ከዚህ ሰው ጋር ያለንን ግንኙነት የሚያበላሽ መስሎ ከተሰማን ሰውየው በማያውቅበት መልኩ መፈፀም ስለሚችል ጥሩ አማራጭ ነው።
ماذا يفعل من أصيب بالعين؟
العين يقع ويدلّ عليه عموم قول النبي صلى الله عليه وسلم : ( الْعَيْنُ حَقٌّ ) رواه البخاري (5740) ومسلم (2187).
إذا عُرف العائن أمر بالاغتسال أو الوضوء ، وأخذ ماؤه وصب على المعيون .
قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله : "ولكن من أصيب بالعين فماذا يصنع؟ يعالج بالقراءة وإذا علم عائنه فإنه يطلب منه أن يتوضأ، ويؤخذ ما يتساقط من ماء وضوئه ثم يعطى للعائن يصب على رأسه وظهره ويسقى منه، وبهذا يشفى بإذن الله" انتهى من فتاوى نور على الدرب
وقال رحمه الله في شرح كتاب التوحيد : "وهناك طريقة أخرى ، ولا مانع منها أيضا ، وهي أن يؤخذ شيء من شِعاره ، أي: ما يلي جسمه من الثياب ؛ كالثوب ، والطاقية ، والسروال ، وغيرها ، أو التراب إذا مشى عليه وهو رطب ، ويصب على ذلك ماء يرش به المصاب أو يشربه ، وهو مجرب " انتهى من "مجموع مؤلفات ابن عثيمين" (9/ 88).
ቁርአናዊ ፈውስ ፔጅ
www.fb.com/nosihr