Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስለ ሀይድ መረጃ እናካፍልዎ ክፍል 1

Dec 29 ፖስት ተደርጎ የነበረው ክፍል 1
~°ስለ ሀይድ መረጃ እናካፍልዎ °~
በድጋሚ እነሆ
የተንቢሀት ልዩ ሳምንታዊ መልእክት ቁ.3 /1
①ኛ ጥበብ ከጥበበኛው
`````````````````````````
የእንስቶች ወርሃዊው ዙር
አል ደውረቱ ሻህሪያ
መግቢያ:-
°°°°°°°°°
ሙስሊሟ እንስት የሀይድ ማለትም የወር አበባ ጊዜዋ አብቅቶ ሰላት የምትጀምርበትን ቀን ለማወቅና የሌሎችንም ድንጋጌዎች አህካም ወይም ውሳኔ ለማወቅ እንዲረዳት የወር አበባዋን መጀመርያና ማብቂያ ማወቋ የግድ የሆነ ጉዳይ ነው።
ይህ ቢያንስ ወደ ሃያ ከሚሆኑ ጉዳዮች ጋር የተቆራኘው የወር አበባ የደም ሂደት እንደ ግል ጉዳይ ብቻ ወይም እንደተራ ነገር የሚታይ ሳይሆን በያንዳንዱ ሙስሊም ቤተሰብና ማህበረሰብ ውስጥ ወሳኝ ሚና ያለው የሸሪዓ ክፍል ነው።
ከሰው ልጆች ባጠቃላይ በተለያዩ አቅጣጫዎች የሚወጡ የፈሳሽ አይነቶች ይገኛሉ።
•> ከአይን
•> ከአፍንጫ
•> ከኣፍ
•> ከጆሮ
•> ከቆዳችን
•> ከብልትና ከመቀመጫ የሚወጡ
ሲሆን
መፈጠርና መኖራቸው አስፈላጊ ከመሆኑም ጋር በአስፈላጊው ወቅት ደግሞ ወጥተው መወገዳቸው ተገቢ የሆኑም ናቸው።
ይህም አንዱ የጤናና በህይወት የመኖራችን ምልክትና የፈጣሪያችን የአምላካችን የአፈጣጠር ብቃትና ጥበብን የሚያሳይ የጌትነቱ የሩቡቢያው መገለጫም ነው።
ወደ ርእሳችን ስንገባ ወንዶችን ብቻ የሚገጥሙ የፈሳሽ አይነቶች እንዳሉ ሁሉ ሴቶችንም ብቻ የሚመለከቱና የሚፈሷቸው የፈሳሽ አይነቶች ኣሉ።
እንደሚታወቀውም ሴቶች በተለያዩ ምክንያቶች የተለያዩ የደም ዓይነቶች ይፈሷቸዋል።
ከነዚህም መሀከል
• የሀይድ (የወር አበባ) ደም
• የኢስቲሃዳ ደም
• የኒፋስ (የወሊድ) ደም…
ዋናዎቹ ናቸው
~ ላሁኑ ትምህርታችን የምንመለከተው ሀይድ ስለሚባለው የደም ዓይነት ይሆናል።
ሀይድ ወይም የወር አበባ
`````````````````````````````
ስለ ሀይድ ደም ምን ያህል
ተገንዝበዋል ?
°> የሀይድ ደም (የወር አበባ) በእንስቶች ላይ መኖር እነሱን የሚያነውራቸው አይደለም።
°> የወር አበባ ደም ሴቷን ከወንዱ የሚለይ ቢሆንም ከወንዶች ዝቅ የሚያደርጋቸው ሰበብም አይደለም።
°> አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንስቶችን ሲፈጥር ማህፀን እንዲኖራቸውና በዚያም ማህፀን ውስጥና በዙርያው አስፈላጊው የሆነውን የሆርሞን፣ የጅማት፣ የደምና የደምስርን እንዲሁም የተለያዩ አካላትን ፈጥሮለታል።
°> ከዚህ ደምም ጋር ያለን ግንኙነት ከዚሁ ይጀምራል።
°> በቦታው የሰው ልጅ ሰው ሆኖ ለመወለድ እስኪበቃ የሚያስፈልገውን ቀለብ ሁሉ ከዚያው ከማህፀን ውስጥ በዚሁ ደም አማካኝነት በእምብርት መስመር ነው ሲመገብ የሚያድገው።
°> ከነዚያም መካከል ደም አንዱና በህይወት የመኖሩ ወሳኙ ነገር ነው።
📙የኢስላም ሊቃውንት (ዑለማእ) እንዳብራሩት:
የደሙ መንስኤ:
``````````````````
የሀይድ ደም ማለት ማህፀን የሚያመነጨውና ሴቷ ለአቅመ ሀዋእ ስትደርስ አብዛኛውን ግዜ በየወሩ የሚፈስሳት የደም አይነት ነው።
የቆይታ ግዜው:
`````````````````
የወር አበባ የታወቀ ወቅት ኣለው፤ በመሆኑም በአብዛኛውን ግዜ በአብዛኞች ላይ ለስድስትና ለሰባት ቀናት ወይም እንደሴቷ ተለምዶ ከዚህ ላነሰ ግዜና ለበለጠ ቀናትም ይቆይባቸዋል።
ቀለሙ:
````````
የደሙ ቀለም ጠቆር ያለ ሲሆን ጥሩ ጠረንም የለውም።
ባህሪው:
``````````
ብዙሃኑ እንስቶች የወር አበባ ሲመጣባቸው እንደ ቁርጠት፣ የጀርባ ውጋትና የተለያዩ የሆድ ውስጥ ወይም ያጠቃላይ ሰውነት የመረበሽ ህመም ያስከትልባቸዋል።
በተለይ የመጀመርያቸው ሲሆን በጣም ይብስባቸዋል።
ከነዚህ አይነት ባህሪና ሁኔታ የተለየ ደም ከመጣባት ግን ሀይድ ሳይሆን የኢስቲሃዳ ደም ይሆናል።
°> በእርግዝና ላይ የሌለች ሴትም እንደ ጤናማነቷ እና እንደ እድሜዋ በየወሩ ይህ የሀይድ ደም ይፈሳታል።
°> ለፈጣሪ ጌታችን ለአላህ ምስጋና ይገባውና የወር አበባ ደምን በማህፀን ውስጥ እንዲሚመነጭ አድርጓል።
°> እዚያ መቅረቱም አስፈላጊ ስላልሆነ በየወራቱ ለተወሰኑ ቀናት ወጥቶ እንዲፈስስ አደረገው።
ይህ የሰው ልጆች መፈጠርያ፣ ማደግያና የመጀመርያው የመኖርያ ስፍራችን ከዚህ ደም ጋር የቅርብ ጉድኝት ስላለው እንደማይመለከተን ሆነን ስለ ደሙ ከማወቅ ልንርቅ አይገባም።
°> የወር አበባ ደም መፍሰሱ ጤናማነት እንጂ ጎጂ ጉዳይም አይደለም።
ስለ ሀይድ ደም ይህን ያህል ከተረዳን በቀጣይ :~
① የሚጀምርበትን የእድሜ ዘመንና ተፈጥሯዊነቱን እንዲሁም
②መፍሰስ ከጀመረ በኋላ የሚያደርገውን ቆይታ በተመለከተ በሊቃውንት መሃል ያለውን አስተያየት ብሎም ለሀቅ የቀረበውን አቋም አናያለን።
ኢን ሻአ አላህ… ይቀጥላል…
هذا والله أعلم
وصلى الله على محمد وعلى آله وصحبه وسلم.
‪#‎ተከታዩን‬ ሊንክ በመጫን ፔጁን ላይክ (l­ike) ያድርጉ
-------------------
www.facebook.com/tenbihat
Abufewzan
7ረቢዕ አልአወል1436/ 29Dec14