Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስለ ሀይድ 2ኛው ክፍል

‎~•  ስለ ሀይድ 2ኛው ክፍል  •~   

የተንቢሃት ልዩ ሳምንታዊ መልዕክት ቁ•5

󾀿የእንስቶች ወርሃዊው ዙር󾀿
      ስለ ሀይድ ደም ህግጋት

በክፍል 1 የመግቢያ መልእክት ስለ የወር አበባ ደም ምንነት ኢስላም ያለውን አቋም በተወሰነ መልኩ እንዳካፈልናችሁ ይሰማናል፤  እነሆ ለዛሬ ደግሞ…

•     የወር አበባ (የሀይድ) ደም
       መምጫው፣ ማብቂያውና
               ተፈጥሯዊነቱ

           እንዲሁም
• የወር አበባ ደም መፍሰስ
  ከጀመረ በኋላ የቆይታ የግዜው
       መጠን ላይ የሊቃውንት
  አስተያየትና ትከክለኛው አቋም

የሚሉትን ርእሶች ይዘን ቀርበናል። ያንብቡት

①   የወር አበባ (የሀይድ) ደም
       መምጫው፣ ማብቂያውና
                ተፈጥሯዊነቱ
               `````````````````
~   የሀይድ (የወር አበባ) ደም ባብዛኛው እድሜያቸው ከ12 እስከ 50 ዓመታት ክልል ባሉትና አልፎ ኣልፎ ደግሞ ወደ 9 አመት እድሜ ወዳላቸውና እስከ 50 አመታት ባላቸው እንስቶች ላይ በየወሩ በታወቀ ግዜ የሚከሰትና ከማህፀን ወጥቶ የሚፈስሳቸው የተለመደና ጤናማ የሆነ የደም ዓይነት ነው።

~  የሀይድ ጅምሩም ሆነ የማለቂያው የእድሜ ሁኔታ እንደ ሴቷ አስተዳደግ፣ ጤና፣ የአየር ሁኔታ ና ሌሎች ተፈጥሮዎች ስለሚለያይ ስለ አብዛኞች እንጂ ስለሁሉም መግለፅ ይከብዳል። እንዲሁም ተገድቦ የተነገረን ቁጥር ባለመኖሩ አንዲት እንስት የወር አበባነትን መስፈርት ያሟላ ደም ከታያት ስርኣቱንና ህግጋቱን መጠበቅ ግዴታ ይሆንባታል።

~   ይህ ደም የመፍሰስ ባህሪ ስላለው ሀይድ ማለትም የሚጎርፍ ተባለ።

~   ይህንንም ጥበበኛው አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በሴቶች ላይ በዚህ መልኩ ደነገገ።

     ኢማሙ ቡኻሪና ሙስሊም ረሂመሁሙላህ በዘገቡትና ከዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ በተነገረን መሰረትም የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስለ ሀይድ ደም ለራሷ ለዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ ሲነግሯት:

فيما رواه الإمام البخاري ومسلم من حديث عائشة رضي الله عنها قالت :- لما جئنا سرف حضت فدخل علي النبي صلى الله عليه وسلم وأنا أبكي . فقال : ما يبكيك أنفست ؟ 
قلت : نعم . 
قال " هذا شيء كتبه الله على بنات آدم " 

« ይህ በኣደም ሴት ልጆች ላይ አላህ የፃፈው (የደነገገው) ነው። »
ማለታቸው ተዘግቧል።

~    ከሀይድ ባህሪም አንዱ ህመም ቁርጠት፣ ማቅለሽለሽና የመሳሰሉት እንደየሴቷ ቢለያይም በየደረጃው ይከሰታል በመሆኑም በዚህ ሰበብ ለሚደርስባቸው ሁሉ ሰብር አድርገው የአላህን ጀልለ ጀላሉሁ ውሳኔና ጥበብ ሊወዱት ፣ ኣሚን ብለው ሊቀበሉት ግድ ይላቸዋል።

~   በዚህም እነደ ኒያቸው የአላህን ምንዳ ይቀራመታሉና።

~   የአላህን ውሳኔም ከመውደድና ከመቀበል ያለፈ ልባዊም ሆነ አንደበታዊ ስህተት ውስጥ ሊገቡ አይገባም።

{ وما كان لمؤمن ولا مؤمنة إذا قضى الله أمراً أن يكون لهم الخيرة من أمرهم }

« አማኝ (ሙእሚን) ለሆነም ሆነ ሙእሚን ለሆነች ግለሰብ አላህ በአንድ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ከመቀበል ውጭ ምንም አማራጭ ሊኖራቸው አይገባም። »

~   አላህ አዝዘ ወጀልለ ደግሞ ሁሉን አዋቂ የሆነ ጌታ ነውና ብልሹ ኣድርጎ አልፈጠረም። 

~   የሰውን ልጅ በመልካም ሁኔታ ነው የፈጠረው።

وقال تعالى :
«  لَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ فِي أَحْسَنِ تَقْوِيمٍ  »

« ሰውንም በጣም ባማረ አቋም ላይ ፈጠርነው  »

~   በፈለገው አይነት የመፍጠር ብቃቱም መብቱም የሱ ነውናም የተሰጠንን ኣመስግነን፣ የቸገረንን እንዲያመቻችልን እንጠይቀው።

   በሱረቱል ኢንፊጣር ስምንተኛው አንቀፅ ላይም በፈለገው አይነት ቅርፅና ይዘት ፈጥሮ እንደሚገጣጥመን አስፍሯል።

وقال تعالى { في أي صورة ما شاء ركبك } 
__________

②  የወር አበባ ደም መፍሰስ ከጀመረ በኋላ የቆይታ የግዜው መጠን ላይ የሊቃውንት አስተያየትና ትክክለኛው አቋም
    `````````````````````````````

የመጀመርያው:  አስተያየት

󾮜 አነስተኛው አንድ ቀንና አንዲት ሌሊት ሲሆን ረዥሙ አስራ አምስት ቀን የሚል ነው

    ይህንንም ሃሳብ አብዛኞቹ የኢስላም ሊቃውንት (ፉቀሃእ) ያሉት ሲሆን፣ ይህም  የወር አበባ የቆይታ ግዜ ትንሹ አንድ ቀንና አንድ ሌሊት ሲሆን ረዥሙ ግዜ ደግሞ አስራ አምስት ቀናት ናቸው የሚል ነው።

2ኛው: አስተያየት

󾮜  አጭሩንም ሆነ ረዥሙን የቆይታ ዘመን ቢጠቅሱም ቁጥሩ ላይ ግን መለያየታቸው
       
  ሸይኹል ኢስላም ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ:

“ ከሊቃውንት መሀከል አጭሩን ና ረዥሙን የሀይድ (የወር አበባ) የቆይታ ዘመን የጠቀሱ ቢኖሩም በቀናቱ ቁጥር ላይ ግን ተለያይተዋል።

   አንዳንዶች የአብዛኛውን የቆይታ ግዜ መጠን ሲጠቅሱ አነስተኛ የሆነውን የቆይታ ግዜ ወስነው ወይም ገድበው አልጠቀሱም። ”

3ኛው: አስተያየት

󾮜 የወር አበባ የቆይታ ዘመን ገደብ
              የለውም የሚል ነው
             
=>   ይህ ሶስተኛው የኢስላም ሊቃውንት (ዑለማኡል ኢስላም) አቋም ወደ ትክክለኛነት ያደላ ነው። 

   ይህም 
=>  የሀይድ የቆይታ ዘመን ትንሹ ግዜው ይህን ያህል ነው፣ ረዥሙ ግዜም እስከዚህ ቀን ነው በሚል ገደብ የሌለበት ነው። 

<•> በመሰረቱ ሴት ልጅ ከወር አበባ የመንፃቷ ምልክቱ ወይም ማረጋገጫው የደሙ መቋረጥ ነው። 

<•>  ይህም የግዜ ዘመኑ ወይም የቆይታው ቀናት ለአጭርም ይሁን ለረዥም ግዜ ቢሆን ዋናው ሚታየው የደሙ መቆም ነው።

     ሸይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እንዳሉት    رحمه الله    

°•>  የወር አበባ ቆይታን በተመለከተ አጭርም ሆነ ረዥም የሚባል የተገደበ የግዜ ቀመር የለም።

 °•>   ይልቅ የታወቀው የወር አበባ ደም ምልክቶች እስካሉባት ድረስ ለአጭር ግዜም ይቆይ ለረዘመ ቀናትም ይቆይ የወር አበባዋ ግዜ ያ ነው ብለዋል።

  “ ሀይድን (የወር አበባን) በቁርኣንና በሱና እንደሰፈረው አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ  ከበርካታ አህካሞች (ህግጋት) ጋር አቆራኝቶታል  ። 
    
   አጭሩንም ሆነ ረጅሙን የግዜ ገደብ ደግሞ አላስቀመጠም። ”

ሸይኹል ኢስላም አክለው ሲያስረዱ

“  ስለ ሀይድ ቆይታ ማወቁ ለህብረተሰቡ አስፈላጊና አሳሳቢ ከመሆኑም ጋር የሀይድን የቆይታ ግዜና በሁለቱ የሀይድ ወቅቶች (ባለችበት ወርና በቀጣዩ ወር) መሀል ያለውን የግዜ ክፍተት ወይም የንፅህናዋን የግዜ ቀመር አላስቀመጠም። ”

መጅሙዕ አልፈታዋ 
ጥራዝ 19: ገፅ 237

=>   በዚህም መሰረት ለሀይድ የተገደበ የግዜ ቀመር ካልተቀመጠ ባህሪውና ምልክቶቹ ላይ መመርኮዝ የሀይድን ደም ከኢስቲሃዳ ደም መለየት የተሻለ አማራጭ ነው።

=>   እንደሚታወቀው የያንደንዷ እንስት የወር አበባ ባህሪም ይለያያል።

   ጠቅለል ሲል የወር አበባን የቆይታ ዘመን በግዜ ቀመር ገድቦ መለየት የማይመችና በዚህ መልኩ እንድንለይ የሚያስገድደን ግልፅ መረጃም ባለመኖሩ የሌሎችን ምሁራን አስተያየት በኢጅቲሃድነቱ ከማክበር ጋር … …

    የሀይድ ደም የአጭር ወይም የረዥም ቆይታ ጊዜው የሚወሰነው በደሙ መኖርና ኣለመኖር ላይ ይሆናል የሚሉትን ሊቃውንት አስተያየት እናስቀድማለን።

   በዚህም ለዒባዳዋም ሆነ ተያያዥ ለሆኑት ሙኣመላዎች ራስዋን እንድታዘጋጅ ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላታል።

ተከታዩ ርዕሳችን
① የኢስቲሃዳ ደም
② የወር አበባን ደም ከኢስቲሃዳ
     ደም መለያ 4ቱ ወሳኝ ነጥቦች
ኢን ሻአ አላህ…  ይቀጥላል…

هذا والله أعلم
وصلى الله على محمد وعلى آله وصحبه وسلم.
____________
#ተከታዩን-ሊንክ-በመጫን-ፔጁን-ላይክ(Like)-ያድርጉ

www.facebook.com/tenbihat

14Rabi'e al-awal 1436 
󾔧 05 jan15
.…‎
~• ስለ ሀይድ 2ኛው ክፍል •~
የተንቢሃት ልዩ ሳምንታዊ መልዕክት ቁ•5
የእንስቶች ወርሃዊው ዙር
ስለ ሀይድ ደም ህግጋት
በክፍል 1 የመግቢያ መልእክት ስለ የወር አበባ ደም ምንነት ኢስላም ያለውን አቋም በተወሰነ መልኩ እንዳካፈልናችሁ ይሰማናል፤ እነሆ ለዛሬ ደግሞ…
• የወር አበባ (የሀይድ) ደም
መምጫው፣ ማብቂያውና
ተፈጥሯዊነቱ
እንዲሁም
• የወር አበባ ደም መፍሰስ
ከጀመረ በኋላ የቆይታ የግዜው
መጠን ላይ የሊቃውንት
አስተያየትና ትከክለኛው አቋም
የሚሉትን ርእሶች ይዘን ቀርበናል። ያንብቡት
① የወር አበባ (የሀይድ) ደም
መምጫው፣ ማብቂያውና
ተፈጥሯዊነቱ
`````````````````
~ የሀይድ (የወር አበባ) ደም ባብዛኛው እድሜያቸው ከ12 እስከ 50 ዓመታት ክልል ባሉትና አልፎ ኣልፎ ደግሞ ወደ 9 አመት እድሜ ወዳላቸውና እስከ 50 አመታት ባላቸው እንስቶች ላይ በየወሩ በታወቀ ግዜ የሚከሰትና ከማህፀን ወጥቶ የሚፈስሳቸው የተለመደና ጤናማ የሆነ የደም ዓይነት ነው።
~ የሀይድ ጅምሩም ሆነ የማለቂያው የእድሜ ሁኔታ እንደ ሴቷ አስተዳደግ፣ ጤና፣ የአየር ሁኔታ ና ሌሎች ተፈጥሮዎች ስለሚለያይ ስለ አብዛኞች እንጂ ስለሁሉም መግለፅ ይከብዳል። እንዲሁም ተገድቦ የተነገረን ቁጥር ባለመኖሩ አንዲት እንስት የወር አበባነትን መስፈርት ያሟላ ደም ከታያት ስርኣቱንና ህግጋቱን መጠበቅ ግዴታ ይሆንባታል።
~ ይህ ደም የመፍሰስ ባህሪ ስላለው ሀይድ ማለትም የሚጎርፍ ተባለ።
~ ይህንንም ጥበበኛው አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በሴቶች ላይ በዚህ መልኩ ደነገገ።
ኢማሙ ቡኻሪና ሙስሊም ረሂመሁሙላህ በዘገቡትና ከዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ በተነገረን መሰረትም የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስለ ሀይድ ደም ለራሷ ለዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ ሲነግሯት:
فيما رواه الإمام البخاري ومسلم من حديث عائشة رضي الله عنها قالت :- لما جئنا سرف حضت فدخل علي النبي صلى الله عليه وسلم وأنا أبكي . فقال : ما يبكيك أنفست ؟
قلت : نعم .
قال " هذا شيء كتبه الله على بنات آدم "
« ይህ በኣደም ሴት ልጆች ላይ አላህ የፃፈው (የደነገገው) ነው። »
ማለታቸው ተዘግቧል።
~ ከሀይድ ባህሪም አንዱ ህመም ቁርጠት፣ ማቅለሽለሽና የመሳሰሉት እንደየሴቷ ቢለያይም በየደረጃው ይከሰታል በመሆኑም በዚህ ሰበብ ለሚደርስባቸው ሁሉ ሰብር አድርገው የአላህን ጀልለ ጀላሉሁ ውሳኔና ጥበብ ሊወዱት ፣ ኣሚን ብለው ሊቀበሉት ግድ ይላቸዋል።
~ በዚህም እነደ ኒያቸው የአላህን ምንዳ ይቀራመታሉና።
~ የአላህን ውሳኔም ከመውደድና ከመቀበል ያለፈ ልባዊም ሆነ አንደበታዊ ስህተት ውስጥ ሊገቡ አይገባም።
{ وما كان لمؤمن ولا مؤمنة إذا قضى الله أمراً أن يكون لهم الخيرة من أمرهم }
« አማኝ (ሙእሚን) ለሆነም ሆነ ሙእሚን ለሆነች ግለሰብ አላህ በአንድ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ከሰጠ በኋላ ከመቀበል ውጭ ምንም አማራጭ ሊኖራቸው አይገባም። »
~ አላህ አዝዘ ወጀልለ ደግሞ ሁሉን አዋቂ የሆነ ጌታ ነውና ብልሹ ኣድርጎ አልፈጠረም።
~ የሰውን ልጅ በመልካም ሁኔታ ነው የፈጠረው።
وقال تعالى :
« لَقَدْ خَلَقْنَا الْإِنسَانَ فِي أَحْسَنِ تَقْوِيمٍ »
« ሰውንም በጣም ባማረ አቋም ላይ ፈጠርነው »
~ በፈለገው አይነት የመፍጠር ብቃቱም መብቱም የሱ ነውናም የተሰጠንን ኣመስግነን፣ የቸገረንን እንዲያመቻችልን እንጠይቀው።
በሱረቱል ኢንፊጣር ስምንተኛው አንቀፅ ላይም በፈለገው አይነት ቅርፅና ይዘት ፈጥሮ እንደሚገጣጥመን አስፍሯል።
وقال تعالى { في أي صورة ما شاء ركبك }
__________
② የወር አበባ ደም መፍሰስ ከጀመረ በኋላ የቆይታ የግዜው መጠን ላይ የሊቃውንት አስተያየትና ትክክለኛው አቋም
`````````````````````````````
የመጀመርያው: አስተያየት
አነስተኛው አንድ ቀንና አንዲት ሌሊት ሲሆን ረዥሙ አስራ አምስት ቀን የሚል ነው
ይህንንም ሃሳብ አብዛኞቹ የኢስላም ሊቃውንት (ፉቀሃእ) ያሉት ሲሆን፣ ይህም የወር አበባ የቆይታ ግዜ ትንሹ አንድ ቀንና አንድ ሌሊት ሲሆን ረዥሙ ግዜ ደግሞ አስራ አምስት ቀናት ናቸው የሚል ነው።
2ኛው: አስተያየት
አጭሩንም ሆነ ረዥሙን የቆይታ ዘመን ቢጠቅሱም ቁጥሩ ላይ ግን መለያየታቸው
ሸይኹል ኢስላም ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ:
“ ከሊቃውንት መሀከል አጭሩን ና ረዥሙን የሀይድ (የወር አበባ) የቆይታ ዘመን የጠቀሱ ቢኖሩም በቀናቱ ቁጥር ላይ ግን ተለያይተዋል።
አንዳንዶች የአብዛኛውን የቆይታ ግዜ መጠን ሲጠቅሱ አነስተኛ የሆነውን የቆይታ ግዜ ወስነው ወይም ገድበው አልጠቀሱም። ”
3ኛው: አስተያየት
የወር አበባ የቆይታ ዘመን ገደብ
የለውም የሚል ነው
=> ይህ ሶስተኛው የኢስላም ሊቃውንት (ዑለማኡል ኢስላም) አቋም ወደ ትክክለኛነት ያደላ ነው።
ይህም
=> የሀይድ የቆይታ ዘመን ትንሹ ግዜው ይህን ያህል ነው፣ ረዥሙ ግዜም እስከዚህ ቀን ነው በሚል ገደብ የሌለበት ነው።
<•> በመሰረቱ ሴት ልጅ ከወር አበባ የመንፃቷ ምልክቱ ወይም ማረጋገጫው የደሙ መቋረጥ ነው።
<•> ይህም የግዜ ዘመኑ ወይም የቆይታው ቀናት ለአጭርም ይሁን ለረዥም ግዜ ቢሆን ዋናው ሚታየው የደሙ መቆም ነው።
ሸይኩል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እንዳሉት رحمه الله
°•> የወር አበባ ቆይታን በተመለከተ አጭርም ሆነ ረዥም የሚባል የተገደበ የግዜ ቀመር የለም።
°•> ይልቅ የታወቀው የወር አበባ ደም ምልክቶች እስካሉባት ድረስ ለአጭር ግዜም ይቆይ ለረዘመ ቀናትም ይቆይ የወር አበባዋ ግዜ ያ ነው ብለዋል።
“ ሀይድን (የወር አበባን) በቁርኣንና በሱና እንደሰፈረው አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ከበርካታ አህካሞች (ህግጋት) ጋር አቆራኝቶታል ።
አጭሩንም ሆነ ረጅሙን የግዜ ገደብ ደግሞ አላስቀመጠም። ”
ሸይኹል ኢስላም አክለው ሲያስረዱ
“ ስለ ሀይድ ቆይታ ማወቁ ለህብረተሰቡ አስፈላጊና አሳሳቢ ከመሆኑም ጋር የሀይድን የቆይታ ግዜና በሁለቱ የሀይድ ወቅቶች (ባለችበት ወርና በቀጣዩ ወር) መሀል ያለውን የግዜ ክፍተት ወይም የንፅህናዋን የግዜ ቀመር አላስቀመጠም። ”
መጅሙዕ አልፈታዋ
ጥራዝ 19: ገፅ 237
=> በዚህም መሰረት ለሀይድ የተገደበ የግዜ ቀመር ካልተቀመጠ ባህሪውና ምልክቶቹ ላይ መመርኮዝ የሀይድን ደም ከኢስቲሃዳ ደም መለየት የተሻለ አማራጭ ነው።
=> እንደሚታወቀው የያንደንዷ እንስት የወር አበባ ባህሪም ይለያያል።
ጠቅለል ሲል የወር አበባን የቆይታ ዘመን በግዜ ቀመር ገድቦ መለየት የማይመችና በዚህ መልኩ እንድንለይ የሚያስገድደን ግልፅ መረጃም ባለመኖሩ የሌሎችን ምሁራን አስተያየት በኢጅቲሃድነቱ ከማክበር ጋር … …
የሀይድ ደም የአጭር ወይም የረዥም ቆይታ ጊዜው የሚወሰነው በደሙ መኖርና ኣለመኖር ላይ ይሆናል የሚሉትን ሊቃውንት አስተያየት እናስቀድማለን።
በዚህም ለዒባዳዋም ሆነ ተያያዥ ለሆኑት ሙኣመላዎች ራስዋን እንድታዘጋጅ ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላታል።
ተከታዩ ርዕሳችን
① የኢስቲሃዳ ደም
② የወር አበባን ደም ከኢስቲሃዳ
ደም መለያ 4ቱ ወሳኝ ነጥቦች
ኢን ሻአ አላህ… ይቀጥላል…
هذا والله أعلم
وصلى الله على محمد وعلى آله وصحبه وسلم.
____________
‪#‎ተከታዩን‬-ሊንክ-በመጫን-ፔጁን-ላይክ(Like)-ያድርጉ
www.facebook.com/tenbihat
14Rabi'e al-awal 1436
05 jan15
.…