Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሡሉ ሠላሣ ፦ ክፍል ሠባት

ኡሡሉ ሠላሣ ፦ ክፍል ሠባት
የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ
★ ጌታህን በምን አወቅከው??? በተባልክ ግዜ
★ በታአምራቶቹ እና በፍጡራኖቹ በል!!
★ከፍጡራኖቹ መካከል ለሊት ፣ ቀን ፣ ፀሀይ ፣ጨረቃ¹
★ ከፍጡራኖቹ መካከል ሠባት ሠማይ ፣ ሠባት ምድር ፣በነሱም (በሠማይ እና ምድር ስር) ያለው ፣ በነሡም መካከል ያለው ²
ለተአምራቶቹ መረጃ
አላህ እንዲህ ይላል ፦ «ከታአምራቶቹ ለሊት ፣ቀን ፣ ፀሀይ ፣ ጨረቃ። ለፀሀይም ሆነ ለጨረቃ አትስገዱ ። እሡን የምትገዙ ከሆነ እነሡን ለፈጠረ ለሆነው ለአላህ ስገዱ ።»
ለፍጡራኖቹ መረጃ
አላህ እንዲህ ይላል ፦ ጌታችሁ ያ! በስድስት ቀናት ውስጥ ሠማያት እና ምድርን የፈጠረ አላህ ነው ።ከዛም ከአርሽ
በላይ ከፍ አለ። ለሊቱ ቀኑን በፍጥነት የሚፈልገው ሢሆን ይሸፍነዋል ። ፀሀይ ፣ ጨረቃ እና ከዋክብት ለትእዛዙ የተገሩ
ናቸው ።አዋጅ! መፍጠርም ማዘዝም ለሡ ነው ። የአለማቱ ጌታ አላህ ላቀ ።»³ ሡረቱል አእራፍ
ኢብኑ ከሢር አላህ ይዘንላቸው እና እንዲህ ይላሉ «እነዚህን ነገሮች መፍጠር የቻለ አካል ለኢባዳ የተገባ ነው»
―――――――――
አጭር ማብራርያ
―――――――――
¹ የአላህ ተአምራቶች እጅጉኑ. በጣም ብዙ ናቸው ።ቆጥረንም አንዘልቃቸውም ። ለአብነት ያክል ግን የኪታቡ
ፀሀፊ የጠቀሧቸውን እናገኛለን ።አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ የሡን ሀያልነትና ቻይነት እናውቅ ዘንዳ የተለያዩ ተአምራቶቹን
እንድንመለከት ይጋብዘናል ለምሣሌ.
«በምድር ላይ ሒዱ መፍጠርንም እንዴት እንደጀመረ ተመልከቱ ከዚያም አላህ የመጨረሻይቱን ማስነሣት
ያስነሣል አላህ በነገሩ ላይ ሁሉ ቻይ ነውና ።በላቸው» አል አንከቡት
ሌሎችም በዚህ መልኩ የተቀመጡ አናቅፆች በርካታ ናቸው
★ እነዚህን የአላህ ተአምራቶች በአስተነተንን ግዜ የአላህ ሀያልነትን ስለምንገነዘብ ኢማናችን ይጨምራል
ከምንግዜውም በበለጠ የአላህን ፍራቻ ይጨምርልናል
² የአላህን.መኖር አሁንም በመፍጠሩ እናውቀዋለን አንድ ነገር ያለ አንድ አስገኚ ሊገኝ እንደማይችል ከኛ የራቀ ነገር
አይደለም ይህም ሆኖ አንዳንድ ፈላስፋዎች እንኳን የሠማቸውን ሠው የራሳቸውን ጭንቅላት ሊያሣምን
የማይችል ተራ ንግግር ይናገራሉ. « ነገራቶች እራሣቸውን ነው የፈጠሩት» የሚል አንድ ነገር እንዴት እራሡን ሊፈጥር
ይችላል??? በምንም ያልተበከለ ንፁህ ጭንቅላት ሊቀበለው የማይችለው የተራ ሠው ንግግር ነው
³ ከዚህ የቁርአን አያ የተወጣጡ
1 አላሆ ሡብሀነሁ ወተአላ ሠባት ሠማይና ሠባት ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ መፍጠሩ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ
እነዚህን ከባባድ ፍጥረቶች በሁለት ቃል መሀከል. መፍጠር የሚችል ጌታ ከመሆኑም ጋር
አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ እንዲህ ይላል ፦
««የእሡማ ነገሩ አንድን ነገር በፈለገ ግዜ ሁን ይለዋል ይሆናል »»
ይህንን ያደረገበት ምክንያት ስርአትን ለባርያዎቹ ሊያስተምር ነው. ሁሉንን ም ስራቸው ስርአት ባለው መልኩ እንዲያከናውኑ እንዳይቻኮሉ (ረጋ ብለው በትእግስት መስራት እንዳለባቸው ለማስተማር ነው ።
2 የአላህን ከአርሽ በላይ መሆን ፦ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ከፍጡራኖቹ በአጠቃላይ ርቆ ከአርሹ በላይ ነው ያለው ይህን ማመን በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ዋጂብ(ግዴታ) ነው. ይህንን ያላመነ እና ያላረጋገጠ ሙስሊም ሊሆን አይችልም
ይህንን በሚያምንበት ግዜ ሊረሡ የማይገቡ ነገሮች ማብራሪያቸውን በተውሒድ አልአስማ ወሲፋት ላይ
አሣልፈናል እነሡ
1 ሚንገይሪ ተህሪፍ
2 ሚን ገይሪ ተእጢል
3 ሚንገይሪ ተክይፍ
4 ሚንገይሪ ተምሢል ናቸው
አጠቃላይ ከዛሬው ርእስ የምንወስደው ወሣኝ የሆነ ትምህርት
★ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ፣ መፍጠሩን ማብላቱን ሌላም በሠው ልጆች ላይ የዋለላቸውን ፀጋ አስታውሦ ሢጨርስ
ለምን እንደተዋለላቸው ሣይናገር አያልፍ የነዚህ ነገሮች መፈጠር እና የሠው ልጆች እንዲያውቋቸው መደረጉ አላህ በኛ ሀቅ እንዳለው ለማስረዳት ነው
share ማድረጎን እንዳትረሡ