Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለምን ይሁን ዉዱ ነቢያችን ላይ የሚያሾፉት?!

አሰላሙ ዐለይኩም
===ለምን ይሁን ዉዱ ነቢያችን ላይ የሚያሾፉት?!===
ምዕራባዊያን ባለንበት ጊዜ ከመቼውም በላይ የማንነታቸው ጉዳይ እያሰጋቸው ነው ዛሬ እንዲህ ከሆነን ነገ ምን ልንሆን ነው ? እያሉ ነው ለዚህ ጥያቄ መልስ ለማግኘት ከራሳቸው ጋር ፍጅት ላይ ናቸው የማህበረ ሰባቸው ስነምግባር መበላሸት፣ አብዛኛ ነዋሪዎች ለእምነታቸው ግዴለሽ መሆናቸው እንቅልፍ እየነሳቸው ነው
ፓሪስ፣ ለንደን፣ ፐርሊን፣ ወዘተ ከተሞቻቸው ላይ የነበሩ የአምልኮ ስፍራዎች/ቤተ-ክህነቶች/ የሚጎበኛቸው ጠፍቶ በርካሽ ዋጋ ለልማት ስራ እየተቸበቸቡ ይገኛል
እስከ ዛሬ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ መልኩ ህዝቦች ወደ ኢስላም እየገሰገሱ ነው ይህም ከተራው ማህበረ ሰብ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ፥እስፖርተኞችን፣ ጸሃፊዎችን፣ፖለቲከኞችን፣ የፊልም አክተሮችን፣የሀይማኖት መሪዎችን ወዘተ ያካተተ ነው ከዚህም አልፎ ኢስላምን ለማጥፋትና ስሙንም ለማንቋሻሽ በይፋ በተለያየ መልኩ ይንቀሳቀሱ የነበሩትም ጭምር ባልታሰበ መልኩ ወደ ኢስላም መግባታቸው የሀገራቱን መሪዎችና አበሮቻቸውን ጭንቅ ውስጥ ጥሏል ብዙም አነጋግሯል
ከነሱው ሀገር የወጡ የጥናት መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ከአመታት በኋላ አብዛኞች የኢሮፕ ሀገራት ኢስልምና እምነት ተከታዮች ቁጥር በእጅጉ እንደሚጨምር ነው አሁንም በየጊዜው ወደ ኢስላም የሚጎርፉ ሰዎች (በተለይም ሴቶች) ቁጥር በጣም አስገራሚ ነው ከነዚህ ሀገራት ውስጥም ሀገሩ በክርስትና እምነት የሚታወቅ ከመሆኑ ጋር በአንድ ዓመት ብቻ 30 ሺህ ንጹህ የሀገሪቱ ተወላጅ የሆኑ ( በስደት የገቡ ሳይሆን) ኢስላምን መቀበላቸው ይታወቃል
ፈረንሳይ ላይ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ 10 ቤተ ክርስቲያኖች ብቻ የተገነቡ ሲሆን 60 ቤተ ክርስቲያኖች ደግሞ የሚጎበኛቸው ጠፍቶች ፈርሰዋል! ልብ በሉ ይህ የሚሆነው ያውም ቤተ ክርስቲያን የሚመጡ ሰዎች እንዳይደብራቸውና ዘና እንዲሉ ተብሎ የተለያዩ የመዝናኛ ስፍራዎችና የሙዚቃ አይነቶች ተዘጋጅተው እሽሽሽሽ እሮሮ የሚባሉ ከመሆናቸውም ጋር ነው!
ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ እዛው ሀገር ውስጥ ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ ብቻ 2000 /ሁለት ሺህ/ መስጂዶች የተሰሩ ሲሆን ገና 150 መስጂዶች ግንባታ ላይ ይገኛሉ በቀጣይ ዓመታትም የመስጂዶችን ቁጥር 4000 ለማሳደግ እቅድ ወጥቷል
ከዓመታት በኋላ ከፈረንሳይ ዜጎች ሩቡ ሙስሊሞች ሊሆኑ እንደሚችሉ ከሀገሪቱ የወጡ መረጃዎች ይናገራሉ!
አሜሪካን ውስጥ በየዓመቱ በቀላሉ 20,000/ሃያ ሺህ/ ሰዎች ወደ ኢስላም ይገባሉ
ከቅብር ዓመታት ወዲህ የሆላንድ ዜጎች አብዛኞቹ የቁርኣንን ትርጉም በመግዛት እያነቡቡ ይገኛል
ጀርመንና እንግልትራ ላይ ከቤተ ክርስቲያን ጎብኚዎች ይልቅ የመስጂድ ጎብኚዎች ቁጥር እንደሚበልጥ መረጃዎች የሚያሳዩ ወጥተዋል
በ2008 ላይ በቫቲካኑ ሊቀ-ጳጳስ አንደበት እንደተገለጽው "የኢስልምና እምነት ተከታዮች ከክርስትና እምነት ተከታዮች በቁጥር በላጭ ነበሩ" ይህ የዛሬ 10 ዓመት የነበረው ሲሆን ዛሬ የትና የት ደርሷል
ይህ እንዳለ ከላይ የተጠቀሱ ሀገራት ህዝቦች በህይወታቸው ሰላምን አጥተዋል፣ ኢኮኖሚያቸው ተቃውሷል፣ እርሰበርሳቸው መባላት ይዘዋል፣ በሙስናና አስካሪ መጠጦች ሳቢያ ትልቅ ውርደት ገጥሟቸዋል ሀገራቱ ላይ ብልግና ከመጠን በላይ በመስፋፋቱ
በህገ ወጥ መንገድ የተወለዱ ህጻናት ቁጥር፥ ስዊዲን ውስጥ %50 እንግልትራ %33 ፈረንሳይ %33 ደርሷል
በዚህና በትዳር ህይወታቸው ላይ ሰላምና መረጋጋትን በማጣታቸው ምክንያት የሀገራቱ ህዝቦች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል አሜሪካን ውስጥ ያለ አባት ከናቶቻቸው ጋር የሚኖሩ የቤተ ሰበ አባላት ቁጥር፥ %34 ደርሷል
የሀገራቱ ነዋሪዎች(ሙስሊም ያልሆኑት)እጅግ በጣም በሚያስፈራ መልኩ አደንዛዥ እጽና አስካሪ መጠጦችን ያዘወትራሉ ከእንግልትራ ወጣቶች ውስጥ %50 የአስካሪ መጠጥ ሱሰኞች ናቸው አሜሪካ ውስጥ የተለያዩ ሀላፊነት ቦታዎች ላይ ከተቀመጡ ሰዎች ውስጥ %32 ልዩ ልዩ አደንዛዥ እጾችን ተጠቃሚዎች ናቸው!
እኛ ሚዲያ ላይ የምናየውና እነሱ በተጨባጭ የሚኖሩት እጅጉን የተለያየ ነው አብዛኞች ከላይ ከተጠቀሱ ችግሮች መውጫ መንገድ ኢስላም መሆኑን በማወቅ በየእለቱ ወደ ኢስላም እየጎረፉ ነው ከጥቂት ዓመታት በኋላ የዓለም ህዝቦች እስላም ውስጥ ይገባሉ ነስርም ይመጣል ሙስሊሞችም የበላይ ይሆናሉ ወከባውም ይቆማል ግፍም ያበቃል|

ታዲያ ይህ ሁሉ ሲሆን ፈረንሳይ ዝም ብላ ማየት አላስቻላትም የሰው ልጆች ሁሉ ምርጥ የሆኑትን፣ ማንንም ሰድበው አንቋሸው የማያውቁትን ነቢያችን ላይ አሾፉ…ተሳለቁ…ቀለዱ…. በዚህም እኩይ ተግባራቸው እራሳቸውን የበለጠ አረከሱ ተዋረዱ የበለጠም ወደ ማለቂያቸው ተቃረቡ
አዑዙ ቢላሂ ሚነሸይጣኒረጂም በአሏህ ስም እጅግ በጣም መሃሪና እዝነቱ ሰፊ ለሁሉም ደራሽ በሆነው፥ (ሙሐመድ ሆይ እኛ ብዙ መልካምን ነገር ሰጥተንሃል ለጌታህ ብቻ ስገድ ለሱም ብቻ እረድ አንተን የሚጠላ ዘሩ (መጨረሻው) የተቆረጠ ነው )ሱረቱል ከውሠር
## አሕመድ ኣደም##
በዐብዱል ዓዚዝ አልሁወይጣን በዓረብኛ የቀረበውን ጽሁፍ መሰረት በማድረ የተዘጋጀ==