Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አንድ ሰው የነብዩን (ﷺ) ሱና ተቃርኖ ‹‹የዘመናችን ምርጥ ሰው አላህ ይጠብቅህ እንወድሃለን!›› ይባላልን???

‎አንድ ሰው የነብዩን (ﷺ) 
ሱና ተቃርኖ 
‹‹የዘመናችን ምርጥ ሰው አላህ ይጠብቅህ እንወድሃለን!››
 ይባላልን???

ከኢማን ስራ ሁሉ በላጭ ለአላህ ብሎ መውደድ ለአላህ ብሎ መጥላት ነው፡፡ አንድ ሙስሊም አንድ ሙስሊምን ሲወድ ለአላህ ብሎ መሆን አለበት፡፡ እውነት ለአላህ ብለው የወደዱትን ሰው ደግሞ የአላህ እና የመልክተኛውን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ትዕዛዝ በተቃረነው እና በጣሰው ልክ ለአላህ ተብሎ ይጠላል፡፡ ምክንያቱም መጀመሪያስ ቢሆን ለአላህ ብሎ ከተወደደ መስፈርቱ ለዚህ ውዴታ ያበቃው የአላህን እና የመልክተኛውን ትዕዛዝ መፈፀሙ ብቻ እና ብቻ ከነበር ከዚሁ ትዕዛዝ ሲያፈነግጥ ባፈነገጠው ልክ ለአላህ ሲባል ይጠላል፡፡

ዛሬ በተገላቢጦሹ የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና ትቶ ‹‹ነብያት የተጣሩለትን ጥሪ የማይጣራ፤ ፂሙን የሚላጨውም፤ ሱሪውን መሬት ላይ የሚጎትተውም እና ሌሎች አመፆችን የሚሰራውን›› ‹‹ለአላህ ብዬ እወድሀለሁ›› ብለው ብዙዎች ለአላህ ብሎ መውደድ ምን መስፈርት እንዳለው ሳያውቁ ቃሉን ይጠቀሙታል፡፡

የአላህ ባርያዎች ሆይ! ለአላህ ብዬ እወድሃለሁ የሚለውን ቃል አላህ እና መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያዘዙትን ለሚተገብር እንጂ ሱናን ጥሶ ፋሽን እና ቢድዓን ለሚከተል አይደለም፡፡

ዛሬ አርቲስቱንም ድራማ ሰሪውንም ‹‹የዘመናችን ምርጥ ሰው›› ብሎ መጥራት ተገቢ አይደለም፡፡ ይህንን አባባል የሚሉ ሰዎች የእስልምና እውቀት የሌላቸው ለመሆናቸው ተግባራቸው ይናገራል፡፡

የዘመኑ ምርጥ ሰው ሊባል የሚገባው ሰዎች የረሱልን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና በተው ግዜ አጥብቆ የሚይዝ እንጂ የሳቸውን ሱና የሚቃረነው አይደለም፡፡

ሀቅ በሰዎች አትለካም፤ ሰዎች በሃቅ ይለካሉ እንጂ፡፡‎
አንድ ሰው የነብዩን (ﷺ)

ሀቅ በሰዎች አትለካም፤ ሰዎች በሃቅ ይለካሉ እንጂ፡፡
Like · ·