Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የተበላሸው ሚዛን

የተበላሸው ሚዛን
***************
አንድ ሰው ስለ አብደላህ ሀረሬ እንዲህ ቢል "አብደላህ ሀረሬ አላህ ከአርሽ በላይ መሆኑን አይቀበልም" ቢል ብዙዎች ማሻ አላህ፣ ጀዛከላህ፣ በርታ ይሉታል።
አሁንም ይህ ግለሰብ "ሰይድ ቁጡብ አላህ ከአርሽ በላይ መሆኑን አይቀበልም" ቢል ብዙዎች የሚከተለውን ይሉታል
*) አንተ የኡለማ ስም ስታነሳ ትንሽ አይከብድህም?
*) የዩሁዳ ተላላኪ
*) ኡማውን በታታኝ
*) እና የመሳሰሉት

አሁንም አንድ ግለሰብ "አህባሾች የአላህ ስም እና ባህሪያትን አህለ ሱና ወል ጀመዐ በሚያፀድቁበት መንገድ አያፀድቁም" ብሎ ቢያጋልጥ ብዙዎች "ማሻ አላህ፣ ጀዛከላህ" ይሉታል
ያው ግለሰብ "ሱፍዬች የአላህ ስም እና ባህሪያትን አህለ ሱና ወል ጀመዐ በሚያፀድቁበት መንገድ አያፀድቁም" ብሎ ቢያጋልጥ ብዙዎች የሚከተለውን ይሉታል
*) "1 ነን እኛ ማንም አይለየን"
*) "ካድሬው"
*) "ሙናፊቁ"
*) "ቅጥረኛው" እና የመሳሰለውን
አሁንም አንድ ግለሰብ ወደ ሽርክ፣ ወደ ቢድዐ፣ ወደ ስሜት መከተል የሚጣሩ ሰዎችን እና ግብረ አበሮቻቸውን ሲያጋልጥ
"የሰው አይብ፣ የወንድምህን አይብ ለምን ታጋልጣለህ?" ብለው ይጠይቁታል።
ሱብሃነላህ ይሄ ሁላ ሀቅን በባጢል ለመሸፈን መሞከር ነው። በአደባባይ የሚሰራጭን ቢድዐ፣ ብሎም "ከአህባሽ ጋር የአቂዳ (የእምነት) ልዩነት የለንም" የሚልን የቢድዐ አራማጅ ለምን ተጋለጠ ብሎ ጥብቅና መቆም ለዲኔ ዘብ ቆሚያለሁ ከሚል የአላህ ባርያ አይጠበቅም።
አብደላህ ሀረሬን ለኩፍሩ እና ለጥመቱ ሲል የእውነት የጠላ ሰይድ ቁጡብ ልክ እንደ አብደላህ ሀረሬ የአላህን ከአርሽ በላይ መሆን አይቀበልም ሲባል ለምን የሰይድ ቁጡብን ስህተት መቀበል ያንገሸግሸዋል?????
አህባሾች ያለባቸው ችግር ሱፍዬችም ላይ አለ ሲባል ያውም በማስረጃ ሲጋለጥ ለምን የሱፍዬች ችግር ሲነሳ ይከፋቸዋል??? ለሱፍዬች አዝነው ነው???
የማይመስል ነገር እንደሚባለው ሱፍዬች አህባሾች እሚያምኑበትን ሽርክ እያመኑ እና እየተገበሩ ከሞቱ እጣ ፈንታቸው ምን ይሆን??? በአላህ ላይ እያጋራ የሞተ የእሳት ነው ብለዋል ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)።
ታድያ ወደ እሳት በሚወስዳቸው ጉዳይ ዝም ያላቸው እውነት ያስብላቸዋል???
አላህን እንፍራ ሚዛናችንን እናስተካክል። ቢድዐ አራማጅ ሲጋለጥ ለኡማው አንድነት ታላቅ ሚና አለው። ለቢድዐ ከለላ የሚሰጥ መዳረሻው አያምርም።
አላህ ሆይ! ሀቅን በሀቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን። ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን።