Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስራን ሁሉ የሚያስተካክለው ተውሂድ ነው፤ ስራን ሁሉ የሚያበላሸው ሽርክ ነው፡፡ ሸይኽ ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ)

ስራን ሁሉ የሚያስተካክለው ተውሂድ ነው፤ ስራን ሁሉ የሚያበላሸው ሽርክ ነው፡፡
=============================================
ሸይኽ ፈውዛን (ሀፊዘሁላህ)
ጠያቂ፡- የተከበሩ ሸይኻችን
የእርሱ ሃሳብ ምንድን ነው?
አንዳንድ ሰዎች ህዝቡን ወደ ተውሂድ አይጠሩም ነገር ግን አብዛኛው ትምህርቶቻቸውና ኹጥባዎቻቸው ላይ ስለ ኹስነል ኹሉቅ (ጥሩ ስነ ምግባር) ብቻ ያስተምራሉ፤ ስለ ተውሂድ ቢያስተምሩም እንኳን…..
(ሸኹ አቋረጡ)
ሸኹ፡- ይሄ ዳዕዋ ምንም ፋይዳ የሌለው ነው፡፡ ይሄ ዳዕዋ ልክ እንደ ራስ (አናት) እንደሌለው የሞተ በድን ነው፡፡ አንድ አካል ጭንቅላቱ ከተቆረጠ ምንም አይፈይድም፡፡
ሰዎች ጥሩ ፀባይ እንዲኖራቸው፤ ሃቀኛ እንዲሆኑ፤ ብዛት ሰላት እንዲሰግዱ፤ ሰደቃ እንዲሰጡ እንፈልጋለን ነገር ግን ሽርክ ከገባበት ሁሉም ስራ ይጠፋል፤ ተቀባይነት አይኖረውም፤ ሁሉም ስራ ተቀባይነት አይኖረውም፤ ስራን ሁሉ የሚያስተካክለው ተውሂድ ነው፤ ስራን ሁሉ የሚያበላሸው ሽርክ ነው፡፡ ስለዚህ ትኩረት ሊሰጠው ግዴታ ነው፡፡
ተውሂድ የሌለው ዳዕዋ እንደሌለ ነው፤ እንደውም ተውሂድ የሌለው ዳዕዋ ከሚኖር ባይኖር ይሻላል ምክንያቱም ሰውን ያጠፋል፤ ሰዎች ሃቅ ነው ብለው ያስባሉ፤
(ጠያቂ..)
ሸኹ፡- ሩሱሎች (መልክተኞች) ዳእዋቸውን የጀመሩት በተውሂድ ነው፡፡ ታድያ ሩሱሎችን ልትፃረር ነውን???
ከነሱ መንሃጅ (አካሄድ) ውጭ ልትሄድ ነውን???
=============================================
አላህ የመልክተኞችን ፋና ዱካ በዱካ ከሚከተሉት ያድርገን፡፡