ሰውተሳሳተ ልቡ ደነዘዘ
በትእቢት በኩራት አይምሮ ፈዘዘ
ጥፋትን ሊሰራ ብእሩን መዘዘ
በመልካም ስብእና በአለሙ እዝነት
በትሁቱ መሪ በሰላሙ አባት
በነፃነትአውራ ፍትህ አስተማሪ
በረሱላችን ላይ በሁሉ አክባሪ
ሀሠት ተደላድሎ ቦታውን ዘነጋ
ነፃነት በማለት ምላሱን ዘረጋ
ከተረዳ በኃላ እውነትነ ጠንቅቆ
ሀሠት ን ቀጠፈ እው ነ ትን አምቆ
ካልገባህ ተረዳ የሱነ ታላቅነት
ህይወቱን ሰውቶ ግፍ በበዛበት
አለምን ያወጣ ከጨቓኝ ባርነት
ስትኖረው ሳለ ዳርክኤጅ በማለት
በቅናት ተይዞ ሀሲድ ቢንጠራራ
ባጢል ቢሰበሰብ ስላንተ ቢያወራ
ቅንጣትን ላይፈፅም ከሰራኸው ስራ
አላህ ይጠብቀን ከመሰሪ ሴራ
ከፍለን ለማያልቅ ለዚህ ውለታህ
ያ! ከሪሚ ጌታ እሱ ይክፈልህ
ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱለላህ