Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሡሉ ሠላሣ ፦ ክፍል ስምንት

ኡሡሉ ሠላሣ ፦ ክፍል ስምንት
የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ
★ እነዛ አላህ ያዘዘባቸው የኢባዳ አይነቶች¹ ለምሣሌ ፦ ኢስላም ፣ ኢማን (እምነት) እና ኢህሣን (ማሣመር) ከነሡ
ውስጥ ዱአ ፣ ሀውፍ (ፍራቻ) ፣ ረጃእ (ክጃሎት) ፣ ተወኩል (መመካት.) ፣ ረግባ (መከጀል) ፣ ወረህበቱ (መፍራት) ፣
ሁሹዕ (መተናነስ) ፣ሀሺያ (መፍራት) ፣ ኢናባ መመለስ ፣ ኢስቲአና (መታገዝ) ፣ ኢስቲአዛ (መጠበቅ) ፣ኢስቲጋሣ (የይድረሱልኝ ጥሪ) ፣ዘብህ (እርድ) ፣ ነዝር (ስለት) ከዚህም ውጪ ያሉ አላህ ያዘዘባቸው የኢባዳ አይነቶች በአጠቃላይ ((እነዚህን ነገሮች ላስገኘ አካል ነው))
መረጃ
አላህ እንዲህ ይላል
«« መስገጃ ስፍራዎች በአጠቃላይ ለአላህ ናቸው ከአላህ ጋር አንድንም ትለምኑ» » ሡረቱል ጂን
★ ከኢባዳ አይነቶች አንዱን ከአላህ ውጫ ላለ አካል አሣልፎ የሠጠ እሡ ሙሽሪክ(አጋሪ) ፣ካፊር (ከሀዲ) ነው ²
መረጃ
አላህ እንዲህ ይላል ፦ «ከአላህ ውጪ ሌላን አምላክ የሚለምን ሠው ለሡ መረጃ የለውም የሡም ምርማሬ ጌታው ዘንድ ነው እነሆ ካሀዲያን አይድኑም » አል.
ሙእሚን
________
አጭር ማብራርያ
=======
★ከዚህ ቀደም ባለፈው ርእስ ላይ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ተአምራቶቹን እና ፍጡራኖቹን ከነገረን ቡሀላ ይህን አስታኮ
እሡን በብቸኝነት.ማምለክ እንዳለብን እንደሚነግረን ለመጠቆም ተሞክሮ ነበር
¹ ኢባዳ እና አይነቶቹ
★ ኢባዳ የሚለውን ቃል የተለያዩ የኢስላም ሊቃውንት በሀሣብ አንድ የሆነና በተለያየ ቃል ትርጉሙን አስቀምጠዋል ከነዛ ውስጥ በጣም ውስን በሆኑ ቃላቶች
እና እጅግ በጣም ሠፊ የሆነ ሀሣብ የሚያስተላልፈው የሼህ ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ አተረጓጎም. ይህንን ይመስላል
« ከንግግር ፣ ከስራ ፣ በላይኛው የሠውነት ክፍል እና በውስጠኛው የሠውነት ክፍል የምንሠራቸው አላህ የሚወዳቸውን ነገሮች አጠቃላ የያዘች ስምነች»
ይህች ኢባዳ በአጠቃላይ አይነቶቹ ሦስት ሲሆኑ ሦስት አርካን እና ሦስት ሸርጦች አሏት እነሡም
★ የኢባዳ አይነቶች
1 በምላስ የሚሠሩ የኢባዳ አይነቶች ፦ ቁርዐን መቅራት ፣ አዝካር ፣ በአጠቃላይ ጠቃሚ የሆነ ንግግር እዚህ የኢባዳ
አይነቶች ውስጥ ይገባሉ ።
2 በላይኛው የሠውነት ክፍል የምንሠራቸው የኢባዳ አይነቶች ውስጥ ፦ ሠላት ፣ ሀጅ ፣ ዘካ. ፣… እና እነዚህን
የመሣሠሉ የሠው ልጆች ሊያዩዋቸው የሚችሉ ኢባዳዎች ናቸው
3 በውስጥ የሠውነት ክፍል የሚሠሩ የኢባዳ አይነቶች ውስጥ ፦ ፍራቻ ፣ ክጃሎት ፣ ውዴታ … እና የመሣሠሉ
ከአላህ ውጪ ማንም ሊያውቃቸው የማይችሉ በልብ የሚሠሩ. ስራዎችን ያካትታል
★የኢባዳ አርካኖች
1 ውዴታ ፦ አንድን ኢባዳ በምንተገብርበት ግዜ ኢባዳውን ለምናደርገው አካልም. ሆነ ኢባዳውን ልንወድ የግድ ነው ።
እየተሠላቸን ወይም ግዴታነቱን ከኛላይ ለማውረድ ብቻ ታስቦ የተሠራ ኢባዳ ኢባዳ ነው ሊባል አይችልም ።
2 ፍራቻ ፦ አሁንም ኢባዳውን በሚያደርግበት ግዜ ኢባዳው ለሚደረግለት አካል ፍራቻ ሊኖር የግድ ነው የምንፈራውም እሡ ዘንድ ያለውን ቅጣት ነው
3 ክጃሎት ፦ አንድን ኢባዳ በምንተገብርበት ወቅት አላህ
ዘንድ ያለውን ቅጣት እንደፈራነው ሁሉ እሡ ዘንድ ያለውንም የድሎት ሀገር መከጀል እና መመኘት የግድ ነው
★እነዚህ ሦስት አርካኖች አንድ ኢባዳ ከሚሠራ ሠው ሊነጠሉ የማይገቡ አርካኖች ናቸው ። በመሠረቱ አርካን
ካልተገኘ አርካን የተደረገለት ነገር አይገኝም እና ሠላት የሚሠግድ ሠው ከሠላት አርካኖች አንዱን ካጎደለ ሠላቱ
ውድቅ እንደሚሆነው ከእነዚህም የኢባዳ አርካኖች አንዱን ካጎደለ ኢባዳው ውድቅ ይሆናል
★ የኢባዳ ሸርጦች
1 በአላህ ማመን ፦ አንድ ሠው በአላሆ ፈጣሪነት ፣ ተመላኪነት እና በስሞቹ እና በባህሪያቶቹ ሣያምን ማንኛውንም አይነት ኢባዳ ቢሠራ ስራው ፋይዳ ቢስ እንደሆ
አላህ እንዲህ ሢል ነግሮናል
« ከስራ ወደሚሠሩት ስራ አሰብን የተበተነ አብዋራ አደረግነው» ሊያዝ ሊጨበጥ የማይችል ነገር ማለት ።
2 ኢህላስ (ፍፁማዊነት) ፦ ኢህላስ የሚባለው ነገር ለአንድ.ኢባዳ ወሣኝ የሆነ ነገር ነው ። አብዘሀኛው አቢድ
፣ዳኢ ፣ኡስታዝ ሌሎችም በኢስላም ስር እየተጉ ያሉ ግለሠቦች የተፈተኑበት በጣም ከባድ እና ከረታነው (ካሸነፍነው) ደግሞ ለድል የምንበቃበት ትልቅ ነገር ነው ።
ፍፁማዊነት ማለት ስራችንን በአጠቃላይ ሠዎች አይተው እንዲያደንቁን ፣ እንዲያሞግሡን ፣ ወይ ደግሞ በአኼራ ስራ የዱንያ ጥቅምን ፈልገን ሣይሆን የአላህን ፊት ብቻ ፈልጎ መተግበር ማለት ነው ። እነዲዚህ ሣይሆን ቀርቶ ለይዩልኝ
እና ለይስሙልኝ የተሠራ. ስራ አጅር ሊያስገኝ ይቅር እና በሠሪው ላይ የሽርክ መዘዝ ነው ይዞበት የሚመጣው
የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዲህ ይላሉ ፥ ((ከምፈራላችሁ ነገር ይበልጥ የምፈራላቹ ትንሹን ሽርክ ነው) አሉ ትንሹ ሽርክ ምንድነው ተብለው ሢጠየቁ እዩልኝ ነው በማለት መለሡ
አላህ ስራችንን በአጠቃላይ የሡ ፊት የተፈለገበት ያደርገው ዘንዳ እማፀነዋለው!!
3 ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለምን መከተል ፦ አንድ ኢባዳ ኢባዳ ለመባል ተግባሩን ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም በንግግር ፣ በተግባር. እንዲሁም ማረጋገጫ በመስጠት ያመላከቱት መሆን አለበት ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ያልተናገሩት ፣ ያልሠሩት ፣ ማረጋገጫም
ያልሠጡት ተግባር ቢድአ በመባል ይታወቃል ይህ ስራ (ቢድአ) ተቀባይነት እንደሌለው የአላህ መልእክተኛ ሠለላሁ
አለይሒ ወሠለም እንዲህ ይላሉ «« የኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሠራ ስራው ወደራሡ ተመላሽ ነው»
★ ከእነዚህ ሸርጦች መካከል አንዱ የጎደለ ከሆነ ኢባዳው ተቀባይነት አይኖረውም ። ኡዱእ ሣይኖረን ሠላት
እንደማንሠግደው ሁሉ እነዚህን ነገሮች ሣናሟላ ኢባዳ ማድረግ የለብንም!!
² እነዚህን አርካን እና ሸርጥ በተገቢው መልኩ ያሟላ አንድም የኣባዳ አይነት ከአላህ ውጪ ላለ አካል መስጠት
ተገቢ አይደለም ከሠጠም ሠውዬው ሙሽሪክ (አጋሪ)፣ ካፊር (ከሀዲ) ይሆናል በእሳት ውስጥም ይዘወትራል።
Share ማድረጎን እንዳይዘነጉ!!