Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሡሉ ሠላሣ ከአጭር ማብራሪያ ጋር ክፍል 4

‎የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ
አላህ እሡን ለመታዘዝ ያመላክትህ እና ከጥመት ወደ ሀቅ የዘነበለችው መንገድ
የኢብራሒም መንገድ ናት። እሦም ለአላህ ሀይማኖትን ጥርት ያደረክ ስትሆን ልትገዛው ነው ።በዚህም ነገር (ሀይማኖትን ለአላህ ጥርት በማድረግ) ሁሉንም ሠዎች አዟል ለዚህም አላማ ፈጥሯቸዋል። አላህ እንዲህ ይላል
« ጋኔንም ሆነ የሠውን ልጅ እኔን ሊገዙኝ ቢሆን እንጂ አልፈጠርኳቸውም» (አዛሪያት 56) 
ሊገዙኝ. ፦ (በብቸኝነት ሊያመልኩኝ)

☞ ትልቁ አላህ.ልንተገብረው ያዘዘው ነገር. ፦ ተውሒድ ነው. እሡም አላህን
በአምልኮ መነጠል ማለት ነው ¹
____________
አጭር ማብራሪያ
____________
በትላንትናው ርእስ የኢባዳን ትርጓሜ በአጭሩ አይተን ነበር. የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ

በአምልኮ መነጠል ማለት ነው
ከዚህ ንግግር

★ተውሒድ. ፦ ማለት የዚህ ኪታብ ፀሀፊ ተውሒድን ኢባዳ በኢባዳ መነጠል
ሢሉ ተርጉመውታል. ይህም ማለታቸው አላህን በብቸኝነት. ልታመልከው ነው ፣
በሡም ምንንም ላታጋራ. ነው ለመላኢካም ፣ለነብይንም ፣ለሦሊህ ሠውም
፣ለቀብርም. በአጠቃላይ ከአላህ ውጪ ላሉ አካላት የኢባዳ አይነቶችን አሣልፎ
አለመስጠት ማለታቸው ነው በዚህ ንግግራቸው የፈለጉበት መልዕክተኞች ሁላ የተላኩበትን የተውሒድ ክፍል ለመጠቆም ነው ሙሉ የሆነው የተውሒድ ትርጓሜ ይህን ይመስላል አላህ ሡብሀነሁ ወተአላን በሦስቱም የተውሒድ ክፍሎች መነጠል ሦስቱ የተውሒድ ክፍሎች አነማን ናቸው??

1 ተውሒድ አሩቡቢያ ፦

ተውሂዱ ሩቡቢያ ማለት፡- አላህ ብቸኛ ፈጣሪ ተቆጣጣሪና ንጉስ መሆኑን ህያው
አድራጊ ገዳይ ሲሣይ ለጋሽ እሱ ብቻ እንደሆነና ባጠቃላይ በሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ ብቸኛ እንደሆነና አጋር እንደሌለው ማመን ማለት ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
‹‹ሰማያትን ያለምታዩዋት አዕማድ (ምሰሶዎች) ፈጠረ፡፡ በምድርም ውስጥ
በእናንተ እንዳታረገርግ ተራራዎችን ጣለ፡፡ በእርሷም ላይ ከተንቀሳቃሽ ሁሉ በተነ፡፡
ከሰማይም ውሃን አወረድን፡፡ በእርሷም ውስጥ ከመልካም ዓይነት ሁሉ አበቀልን፡፡ ይህ የአላህ ፍጡር ነው፡፡ እነዚያ ከእርሱ ሌላ ያሉት ምንን እንደፈጠሩ እስኪ አሳዩኝ፡፡ በእውነቱ በዳዮቹ በግልጽ
ጥመት ውስጥ ናቸው፡፡ (ሉቅማን 1ዐ-11)
“ከአላህ ሌላ የምትግገዟቸውን አያችሁን? ከምድር ምንን እንደፈጠሩ አሳዩኝ፤
ወይም በሰማያት ለነሱ (ከአላህ ጋር) መጋራት አላቸውን?” (አል አህቃፍ 4)
ይህ የተውሂድ ክፍል ከእምነት ክፍል ውስጥ አንዱ ቢሆንም አንድ ሰው ይህንን
ብቻ በማመኑ በአላህ አመነ አይባልም እንዲያውም በነብዩ ላይ ጦርነት የከፈቱ
አጋሪዎች በዚህኛው የተውሂድ ክፍል ያምኑ እንደነበር አላህ በብዙ የቁርዓን አንቀፆች ገልጿል፡፡

አላህ እንዲህ ይላል፡-

‹‹ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ፀሐይንና ጨረቃንም የገራ ማን እንደኾነ
ብትጠይቃቸው በእርግጥ አላህ ነው ይሉሃል፡፡ ታድያ እንዴት ይመለሳሉ፡፡ (አንከቡት 61)

‹‹ከሰማይም ውሃን ያወረደና በእርሱም ምድርን ከሞተች በኋላ ሕያው ያደረጋት
ማን እንደኾነ ብትጠይቃቸው «አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ምስጋና ለአላህ ነው»
በላቸው፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡ (አንከቡት 63)

‹‹ማን እንደፈጠራቸውም ብትጠይቃቸው «በእርግጥ አላህ ነው» ይላሉ፡፡ ታዲያ
(ከእምነት) ወዴት ይዞራሉ፡፡ (ዙኽሩፍ 87)

«ምድርና በውስጥዋ ያለው ሁሉ የማን ነው? የምታውቁ ብትኾኑ (ንገሩኝ)»
በላቸው፡፡ በእርግጥ ‹‹የአላህ ነው» ይሉሃል፡፡ታዲያ አትገሰጹም ፡፡ የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው? «በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ እንግዲያ አትፈሩትምን፡፡ የነገሩ
ሁሉ ግዛት በእጁ የኾነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው?
የምታውቁ እንደኾናችሁ (መልሱልኝ)» በላቸው፡፡ በእርግጥ አላህ ነው» ይሉሃል፡፡ «ታዲያ እንዴት ትታለላላችሁ?» በላቸው፡፡ (አል ሙእሚኑን 84-89)

ከዚህ የምንረዳው በተውሂዱ ሩቡቢያህ ማመን ብቻ አንድን ሰው ከቅጣት
እንደማያድነው እና ሙስሊምም እንደማያሰኘው ነው፡፡ ስለዚህ በአላህ አማኝ ሙስሊም ለመሆን አምልኮን ለአላህ ብቻ በማድረግ በአምልኮው ላይ ከማጋራት መጠንቀቅ ግዴታ ነው::(በሀይደር ከድር)

2 ተውሒድ አል ኡሉህያ
ኡሉሒያ” (አምላክነት) “ኢላህ” (አምላክ) ከሚለው ስም የተወሰደ ሲሆን
የሚመለክና ትዕዛዙ ሊፈፀም የሚገባ ማለት ነው፡፡ “ኢላህ” (አምላክ) ከአላህ
ውብ ስሞች አንዱ ሲሆን “ኡሉሂያ” (አምላክነት) ደግሞ ከታላቅ ባህሪያቱ አንዱ ነው፡፡ አላህ ልቦች ሊያመልኩት፣ ሊዋረዱለትና ትዕዛዙን ሊፈፅሙ የሚገባ አምላክ ነው፡፡ ምክንያቱም ፍጥረተ ዓለምን የፈጠረ፣ ጉዳዮችን የሚያስተናብር፣ በተሟሉ
ባህሪዎች ሁሉ የተገለፀ፣ ከጉድለቶች ሁሉ የተጥራራ ትልቅ ጌታ ነው፡፡ መዋረድና መተናነስ ለርሱ እንጂ ለማንም አይገባም፡፡ በመፍጠር በማስገኘትና እንደነበር በመመለስ ብቸኛና ማንም ማይጋራው ስለሆነ በአምልኮም ማንም ሊጋራው
ማይገባ ብቸኛ መሆኑ የግድ ነው፡፡

“ተውሂዱል ኡሉሂያ” አላህን በአምልኮ ብቸኛ ማድረግ ሲሆን ይህም የሚሆነው
አንድ ባሪያ በትክክል መመለክ የሚገባው አላህ ብቻ መሆኑን እርግጠኛ ሆኖ ሲያውቅ ነው፡፡

የመመለክ ባህሪ ከአላህ ሌላ ለማንኛውም ፍጡር እንደሌለ ሲያውቅ ውስጣዊና ውጫዊ በሆኑ የአምኮ ዘርፎች በሙሉ አላህን ብቸኛ በማድረግ እንደ ሰላት፣ ዘካ፣ ፆም፣ ሀጅ፣ በመልካም ማዘዝ፣ ከመጥፎ መከልከል፣ ወላጆችን መታዘዝ፣
ዝምድናን መቀጠልና የመሳሰሉትን አካላዊ አምልኮዎችንና እንደ በአላህ ማመን፣
በመላኢኮች፣ በመፅሐፎች፣ በመልዕክተኞች፣ በመጨረሻው ቀንና በቀድር ማመን በመሳሰሉት
ልባዊ እምነቶች አላህን ብቸኛ በማድረግ የአላህን ውዴታና የርሱን ምንዳ ብቻ
በመከጀል ያመልከዋል፡፡

# ማስረጃዎቹ
አላህን በብቸኝነት ማምለክ ግዴታ ስለመሆኑ ብዙና የተለየዩ ማሰረጃዎች አሉ፡-

1. አንዳንዴ በትዕዛዝ መልኩ ይቀርባል::
አላህ እንዲህ ይላል፦

‹‹ ሰዎች ሆይ! የፈጠራችሁን እነዚያንም ከናንተ በፊት የነበሩትን (የፈጠረውን)
ጌታችሁን ተገዙ፤ (ቅጣትን) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና፡፡ (አል በቀራህ 21)

‹‹አላህንም ተገዙ፡፡ በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡(አል ኒሳህ 36)

‹‹ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፡- እርሱን እንጂ ሌላን አትገዙ፡፡ (ኢስራህ 23)

ይህን የመሳሰሉ አንቀፆች ሌሎችም አሉ፡፡

2. አንዳንዴ ሰዎች ጋኔኖችና ሌሎችም ፍጥረታት የተገኙለት ዋነኛ ዓላማ ተደርጎ
ይገለፃል:: አላህ እንዲህ ይላል፦

‹‹ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ (ዛሪያት 56)

3. አንዳንዴ ይህ የመልክተኞች መላክ አላማ ተደረጐ ይገለፃል፡፡ ለምሳሌ አላህ
አንዲህ ይላል-

‹‹በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ «አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ» በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡፡ (ነህል 36)

‹‹ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ
የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ (አንቢያ 25)
(ምንጭ ሀይደር ከድር)

3 ተውሒድ አል አስማ ወሢፋት ፦
ተውሒድ አልአስማ ወሢፋት ማለት፦ አላህ ለራሡ ያፀደቀውን ወይ ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም. ሠሒህ በሆኑ ሀዲሦች ያፀደቁትን እነሡ ባፀደቁት መልኩ ማፅደቅ ነው ከአላህ
ያራቁትን ከማራቅ ጋር ይህንን በሚያምንበት ግዜ

1. ሚንገይሪ ተህሪፍ ፦ ተህሪፍ ማለት አንድን ነገር መጀመርያ ከነበረው ፊት ማዞር ይህ በሁለት አይነት መንገድ ሊከሠት ይችላል

1.1. ቃሉን በመለወጥ ፦ በቃሉ ላይ በመጨመር ፣በመቀነስ ፣እና የቃሉን ሀረካ
(አናቢዎች) በመለዋወጥ የሚደረግ ለውጥ ነው

ለምሣሌ አላህ በቁርአኑ

ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦُ ﻋَﻠَﻯﺍﻟْﻌَﺮْﺵِ ﺍﺳْﺘَﻮَﻯ } [ ﻃﻪ : 5 ] ( ﻃﻪ : 5 )
( አረህማን ከአርሽ በላይ ከፍአለ) (ጠሀ 5 )
ﺇﻟﻰ ﺍﺳﺘﻮﻟﻰ
ወደ (አረህማን ከአርሽ በላይተሾመ) ወደሚል.

ሁለተኛው ትርጉም ከነብዩም ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ፣ከሠሀቦችም ፣ ከታብዕዬችም በአጠቃላይ ከሠለፎች አልተገኘም ስለዚህ ውድቅ ነው

1.2. ትርጉሙን በመለወጥ ፦ አላህ እና. መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም
ያልፈለጉበትን ትርጉም በመተርጎም
.ምሣሌ " ﺍﻟﻴﺪ " እጅ አላህ በቁርአን ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም በሠሒህ ሀዲስ አላህ እጅ እንዳለው አስፍረዋል " ﺍﻟﻴﺪ " እጅ የሚለውን በ ሀይል ወይ ፀጋ በሚል የተረጎመ ከቀደምቶች አንድም የለም ስለዚህ ይህ አተረጓጎም ስህተት ነው

2 ሚንገይሪ ተዕጢል(ማራቆት) ፦ አላህን ባህሪ አልባ አለማድረግ ። አንዳንድ የጠመሙ አንጃዎች እንደሚሉት "አላህ ባህሪ የለውም "

∴ተህሪፍ (ማዛነፍ) እና ተእጢል (ማራቆት)የሚለያዩት.

ተህሪፍ. ፦ በሌላ ሸሪአው ባልደነገገውን አዲስ ቃል.ወይም ትርጉም መለወጥ ማለት ነው.ምሣሌው ላይ እንዳለፈው
ተእጢል ፦ ቃሉን ያለምንም መለወጫ ቃል ትርጉም አልባ ማድረግ.

3 ሚን ገይሪ ተክይፍ.( ሁኔታን ሣንገልፅ) ፦ የአላህን ባህሪዎች ሁኔታቸውን መግለፅ
አንዳንድ አፈንጋጮች እንደሚሠሩት ምሣሌ የአላህ እጅ እንዲህ ነው ቡሎ መናገር ይህ በጣም ትልቅ ስህተት ነው!! የአላህን ዛት ማንም ሠው አላየም ማንም ሠው ያላየውን መናገር አይችልም ከተናገረም ይሣሣታል ።ይህም እውቀት ከሠው ልጆች ግንዛቤ እጅጉኑ
የራቀ ነው! የሠው ልጅ እንኳን ስለ ጌታው ስለራሡ አፈጣጠር ጠንቅቆ የማያቅ ደካማ ፍጥረት ስለሆነ ስለ አላህ ባህሪዎች ሁኔታ ከመናገር ሊቆጠብ ይገባል ።

4 ሚን ገይሪ ተምሢል ፦ አላህ ከሌላ ፍጥረት ጋር ማመሣሠል ምሣሌ አላህ ሠሚ እንደሆነ ተናግሯል ይህን ንግግሩን አዎ በልቅናው የሚገባው መስማትን ይሠማል ብሎ ማመን ሢገባው እንደ እንትን… ነው የሚሠማው ብሎ አላህ አምሣያ የሌለው ሀሊቅ ሆኖ
ሣለ ለአላህ አምሣያን ማበጀት ነው

☞ በአስማ ወሢፋት ዙርያ እነዚህን ሦስት እምነቶች ያረጋገጠ በአላህ ፍቃድ ከውዥንብር ፈጣሪዎች ነፃ ይሆናል

1 አላህ እና መልዕክተኛው የገለፁልንን ባህሪ በአጠቃላይ ማመን ።

2 አላህ ሡብሀነሁ ወተአላን የሡን በሀሪ ከፍጡር ጋር አለማመሣሠል።

3 የአላህን የባህሪዎች ሁኔታቸውን በፍፁም ሊያውቅ ስለማይችል ለማወቅ አለመሞከር ።

በመጨረሻም በ አንድ ጥያቄ የዛሬውን ርእስ እዚህጋር አበቃለው በአላህ ፍቃድ
ይቀጥላል!!

ጥያቄ ፦ ሦስቱንም የተውሒድ ክፍሎች በአንድ ላይ ያቀፈች አንቀፅ. ምን ሡራ ውስጥ ትገኛለች? አንቀፅ ቁጥሯስ?‎
የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ

ጥያቄ ፦ ሦስቱንም የተውሒድ ክፍሎች በአንድ ላይ ያቀፈች አንቀፅ. ምን ሡራ ውስጥ ትገኛለች? አንቀፅ ቁጥሯስ?