Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጀነት የሙተቆች ንብረት

አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏህ
ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ አሏህ ይሁን ሰላትና ሰላምም የነቢያት መደምደሚያና ለዓለም እዝነት ተደርገው በተላኩት ነቢያችን ሙሐመድ ላይ ይስፈን
=== ጀነት የሙተቆች ንብረት===
ጀነት ሲባል ውስጡ ደስታ የማይሰማውና የማይጓጓ ሙስሊም የለም:: ካለም ኢማኑን መፈተሽ ይጠበቅበታል ምክንያቱም ሰው ሆኑ ሀገሩን የማይናፍቅ የለም:: የሙእሚኖች ሃገር ጀነት ናት ወደ ዱኒያ የመጣነው ስራ ሰርተን ለመመለስ ነው:: የመጣለትን ዋና ዓላማ የዘነጋና የሚኖርበትን ሃገር ምንነት የማያውቅ ሰው በግዜው በሚያገኛቸው ወቅታዊ መደሰቻዎች ሊብቃቃና ሊረካ ይችላል:: ሙእሚን ግን ቁርጠኛ ነው ወኔውም ትልቅ ነው አላማውንም አይዘነጋም:: በሁለቱም ዓለም እንደፈለጉ ሆኖ መኖር እንደማይቻል ያውቃል:: አሏህ በተከበረው ንግግሩ "" ባሪያዬ ላይ ሁለት ስቃዬን አልሰበስብም፣ ሁለት ሰላምም አልሰጠውም፥ አዱኒያ ላይ ከፈራኝና ህጌን ካከበረ ከሞት በኋላ ባለው ህይወቱ ሰላምን እሰጠዋለሁ ዱኒያ ላይ ህጌን ከጣሰና ካልፈራኝ ከሞት በኋላ ስጋትና መከራ እንዲፈራረቅበት አደርገዋለሁ“” ማለቱን ሁሌም ያስታውሳል::
እነሆ ዱኒያ ላይ አሏህን ፈርቶ ወንጀለ የተወ፣ ስሜቱን ያሸነፈ አኼራ ላይ እነደሻው ይኖራል
ዱኒያ ላይ እንደፈለጉ እየሆኑና አሏህንም እያስቀየሙ ኖረው፥ ከሞት በኋላ ጀነትና ጸጋዎቿን መመኘት ትልቅ ሞኝነትና በዱኒያ ላይ ብዙ ነፍሳቸው የምትፈልጋቸው ነገሮችን ለአሏህ ብለው ትተው የኖሩ ሰዎችንና የሻቸውን ስያድበሰብሱ የኖሩትንም አሏህ አንዳይነት ደረጃና ማዕረግ ይሰጣቸዋል ብሎ ማሰብ በመሆኑ አሏህ ሰዎችን ይበድላል ማለትም ጭምር ነው::
ጀነት አሏህ ለመልካም ሰሪ ባሪያዎቹ የሚሸልማት መቼም የማትጠፋ ውድ ንብረት ናት:: ይሄን ታላቅ ሽልማት ለማግኘት አስፈላጊዉን ነገር ማሟለት የግድ ነው::
እያንዳንዱ ሰው አሏህ ዘንድ ጀነትን ሊያስሸልመኝ የሚችል ስራ ምን አልኝ እያለ እራሱን ሊፈትሽ ይገባዋል:: ጀነት የሚገባው በአሏህ ረህመት ቢሆንም ከገቡ በኋላ ደረጃዎች የሚመደቡት ይሰሩት በነበረው መልካምስራ መሰረት ነው:: ጀነት አፈሯ ለም የሆነች ባዶ መሬት ናት ባሪያው ከተውሂድ ጋር ዱኒያ ላይ መልካምን ስራ በሰራና ከወንጀል በታቀበ ቁጥር የጀነት ባዶ መሬቱ ላይ መላይኮች ይዘሩለታል ይተክሉለታል የአኼራን የተሟላ ደስታና እረፍት የፈለገ በሙሉ ዱኒያ ላይ ላለ ማረፍ መወሰን ይጠበቅበታል ካልሆነ ግን ሁሉን ወዶ የለም!
# አሕመድ ኣደም
ረቢ ኢግፊር ሊ ወሊዋሊደየ ያከሪም