Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ማንን ነው የወደድነው የአንፀባራቂው ታሪክ ባለቤት ከመነሻ እስከ መድረሻ ክፍል - 3

‎°° ማንን ነው የወደድነው❓°°

     󾀽 ሙሐመድ ﷺ󾀽
  የአንፀባራቂው ታሪክ ባለቤት
      ከመነሻ እስከ መድረሻ
                ክፍል - 3

              󾁇󾁇󾁇

•> ባሳለፍናቸው ክፍል አንድና ሁለት መልዕክቶች: -

• የመልእክተኛው ﷺ መነሻ ታሪክ ላይ የነቢዩ ኢብራሂም ﷺ ትውልድ ሀገርና ነቢይ ተደርገው የተላኩባት ኢራቅ መሆኗን፤

• ከሀገራቸው ከኢራቅ ወደ ሻም ምድር ( ያሁኖቹ ሶሪያ፣ ዮርዳኖስ፣ ሊባኖስና ፍልስጢን በሚል ወደ ተከፋፈሏት ምድር ) መሰደዳቸውን፤

• መስር (ግብፅ ሀገር)  ገብተው ቆይታ ማድረጋቸውን፤

• በግብፅ ንጉስ ፈተና ገጥሟቸው ለባለቤታቸው ለሳራ ክብር ሃጀር የምትባል የቤተመንግስቱ ምርጥ እንስት እንድትካድማት መሰጠቱን፤

• ከግብፅ ወደ ፍልስጢን መመለሳቸውን ፤

• ከሀገር ሀገር የሚሰደዱት ተውሂድን ለማስተማርና ራሳቸውንም ከጨካኝ ገዢዎች ሴራ ለማዳን ወደ ተሻለና ወደ ተረጋጋ ስፍራ መሄዳቸውን ፤

• ከኢራቅ ሲሰደዱ ከነቢዩ ሉጥ ﷺ እና ከባለቤታቸው ከሳራ ጋር መሆኑን፤ 
• ሳራ ያጎታቸው ልጅና ባለቤታቸው መሆንዋን ፤

• እመት ሃጀርን የግብፅ ንጉስ ለሳራ በስጦታ እንደሸለማት ሁሉ እመቤት ሳራም ልጅ በማጣት ረጅም እድሜ ከባሏ ጋር በማሳለፏና ባለቤቷም የሚተካውን ልጅ ፈልጎ እንደጓጓ ስለምታውቅ ሃጀርን አሳልፋ ለውዱ ባለቤቷ መስጠቷን ፤

• ኢብራሂም ﷺ ስጦታውን ተቀብለው ከሃጀር ልጅ ማፍራታቸውን፤

• የኢብራሂም ﷺ የመጀመርያው ልጅ ኢስማዒል መሆኑን፤

• በኢስማዒል መወለድ ባለውለታዋ ሳራ መልሳ መቅናቷንና ከእይታዋ እንዲርቁ ማሰቧን፤

• ነቢዩ ኢብራሂም ﷺ መልእክተኛ ነቢይ በመሆናቸው የሚሰሩት በሙሉ በአላህ ትእዛዝ መሆኑን ተመልክተናል።

            󾁀󾁀󾁀󾁀󾁀

  በዚህም መሰረት የሀይማኖታችን መሰረታዊ ነጥቦችን እንደሚከተለው እናስተውላለን።

①• ኢብራሂም ﷺ የአላህ መልእክተኛ ነቢይ ናቸው።

° በዚህ ማእረግ ያለ ሰው የሚተገብረው በሙሉ ከፈጣሪው የታዘዘው መልእክት በመሆኑ ለማንም የግል ራእይ ቦታ የለውም።

②• ፈጣሪያችን አላህ ኢብራሂምን ﷺ የላከው የሰው ልጆች ፈጣሪ ጌታቸውን ብቸኛውን አምላካቸውን አላህን ያለ ምንም አጋር እንዲያመልኩ ነው።

③• ኢብራሂም ﷺበህይወት እያሉ አይሁዳነት፣ ክርስትና የሚባሉ እምነቶች አልነበሩም። 

• ወደ ፊት እንደምንደርስበት ሁሉ አይሁዳ የሚባለው እምነት የተፈጠረው ከኢብራሂም ﷺየልጅ ልጅ በኋላ ነው።

• ክርስትናም የተፈጠረው ከበርካታ ዘመናት በኋላ ከነቢዩ ዒሳ ﷺእርገት በኋላ ነው።

ፈጣሪያችን አላህም እንዲህ ይለናል

{ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ لِمَ تُحَاجُّونَ فِي إِبْرَاهِيمَ وَمَا أُنْزِلَتِ التَّوْرَاةُ وَالْإِنْجِيلُ إِلَّا مِنْ بَعْدِهِ أَفَلَا تَعْقِلُونَ }.
آل عمران/65

« እናንተ የመልሐፉ ሰዎች ሆይ  !
በኢብራሂም (ጉዳይ) ለምን ትከራከራላችሁ ? ተውራትና ኢንጂልም ከሱ በኋላ እንጂ አልተወረዱም። ልብ አታደርጉምን በላቸው። »
ኣሊ ዒምራን: 65

• ኢብራሂም ﷺ ይሁዲም ክርስቲያንም አልነበረም። ነገር ግን ከባዕድ አምልኮ ጥርት ያለ ፈጣሪ ጌታውን ብቻ የሚታዘዝ ነቢይ ነበር።

 { مَا كَانَ إِبْرَاهِيم يَهُودِيًّا وَلَا نَصْرَانِيًّا وَلَكِنْ كَانَ حَنِيفًا مُسْلِمًا وَمَا كَانَ مِنْ الْمُشْرِكِينَ } 
آل عمران/67

« ኢብራሂም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም። ግን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበረ። ከአጋሪዎችም አልነበረም። »
ኣሊ ዒምራን: 67

• ለፈጣሪ ጌታችን ለአምላካችን ለአላህ እጅ ሰጥቶ በመታዘዝ ባእድ አምልኮን በመራቅ እሱን ብቻ ማምለክ ማለት ባጭሩ ኢስላም ይባላል። ነቢዩ ኢብራሂምም የአላህ መልእክተኛ፣ የነቢያት አባት ፣ የሙስሊሞች መሪ ናቸው።

4• የኢብራሂም ﷺ የበኩር ልጅ ማለትም የመጀመሪያ ልጁ ኢስማዒል ነው።

• በመሆኑም በነቢዩ ኢብራሂም ﷺ ማንነትና በበኩር ልጁ ማንነት ላይ ይሁዶችም ሆኑ ነሳራዎች ያደረጉት የታሪክ ሽሚያና ቅልበሳ ቦታ የሌለው ነው።
                       󾁇󾁀󾁇

ክስተት 5
ቀጣዩ ቀደር
°•••••••••••°

   አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ነቢዩ ኢብራሂምን አለይሂ ሰላም ያሉበትን የፍልስጢንን ምድር ለቅቀው ……
 
_________

         ሙሐመድ ﷺ
የአንፀባራቂው ታሪክ ባለቤት
     ከመነሻ እስከ መድረሻ
            ክፍል _4
ይቀጥላል ……
_________
󾔧 احمد سيرة  abufewzan
22Jan15
1 Rabi'e al-thani 1436

~`~‎
°° ማንን ነው የወደድነው°°

احمد سيرة abufewzan
22Jan15
1 Rabi'e al-thani 1436
~`~