Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ማንን ነው የወደድነው የአንፀባራቂው ታሪክ ባለቤት ከመነሻ እስከ መድረሻ ክፍል - 2

‎<•> ማንን ነው የወደድነው  ? <•>

               ሙሐመድ ﷺ 
      የአንፀባራቂው ታሪክ ባለቤት
       ከመነሻ እስከ መድረሻ
                ክፍል - 2
                     󾁇

 ክስተት 4
ቀጣዩ ቀደር
°•••••••••••°

   አላሁ አዝዘ ወጀለ ከኣንዱ ቀደር ወደ ሌላኛው እየነዳንና እያሸጋገረን እነሆ የሙሀመድን ﷺ ማንነትና መነሻ ከሺሆች አመታት በፊት  የተደገሰውን ከርቀት እያሳየን ግብዣውን ቀጠለ።

   እመቤት ሳራ ለውዱ የአላህ አገልጋይና ተፈቃሪ መልእክተኛው ለነቢዩ ኢብራሂም ﷺ ባቀረበችለት ውድ ስጦታ ሰበብ እመት ሃጀር የበኩር ልጁን ኢስማዒልን ኣረገዘች።

                   󾀽

   እመቤታችን ሳራ እድሜዋ ገፍቷል፤ ነቢዩ ኢብራሂም ወደ ሽምግልናው ገብተዋል፤ እስከዚያን ወቅት ድረስም የመውለድ እድል አልገጠማቸውም ፍሬ ኣፍርተውም የአይን ማረፍያ ሊያገኙ አልቻሉም።

   ዘንድሮ ግን አዲስ ብስራት መጣ ። ድንቅ ስጦታዎችም ኢብራሂምና ሳራ ላይ አንዣበቡ።

   የታላቁ የነቢያት አባት ወደ ተውሂድ ጥሪ እንደቀጠለ ነው ። ሰዎችን ከባእድ አምልኮ የማስጠንቀቅ ና ልዕለ ሃያሉን ፈጣሪ አላህን በብቸኝነት እንዲያመልኩ የሚያደርጉትን ጥሪ በየደረሱበት እየገፉበት ነው።

   የዚህም ቆራጥነት ሽልማት በተለያዩ አቅጣጫዎች " ለከሊሉላህ " እየጎረፉ ነው።

~ ከግፈኛ መሪዎች ሴራና ፈተና ማምለጥ

~ በስተርጅና ደጋፊና ህይወትን ከምታጣጥም አዛኝ እውነተኛ ወዳጅ ጋር መዝለቅ

~ ቤታቸውንና ህይወታቸውን ሞቅ የምታደርግ የታረመች ጉብል በክብር ማግኘት

~ ተስፋ በደበዘዘበት የእድሜ ደረጃ ተተኪ ትውልድ፣ የበኩር ልጅ ፣ የስጋው የደሙ ክፋይ ፣ የአይን መርጊያ፣ የልብ ማረፍያ ማግኘት… … ቀጥሏል

                   󾁇

   የተከበረችዋ ሳራ ለባሏና ለአጫዋቿ  ለሃጀር በዋለችው ታላቅ ውለታ ደስተኛና እርካታ የተሰማት ብትሆንም ሰው እንደመሆንዋ እንደ እንስትነቷም የባለቤቷ ከሌላ ሴት ልጅ ማፍራት ቆንጠጥ አደረጋት ፣ ውስጧን ረበሻት።

• ይህንን ውለታ አስተውሉት
• ይህንን ፍቅር ኣስቡት
• ይህንን ትእግስት ገምቱት
• ሳራም በራስዋ አልወጠነችም
• ኢብራሂምም ﷺ ያለ ትእዛዝ አልፈፀመም

󾮜የአላህ ውሳኔ ይቀጥላል
የሙሀመድ ﷺማንነትም ይታያል
             󾁇        󾁇

   ለሣራ ትናንት አጫዋች አገልጋይዋ የነበረች፣ እንደፈለገች እንድታዝባት የተሰጣት ወጣት ዛሬ ባሏን ተካፋይ፣ ቤቷን ተጋሪ ከመሆንም ኣልፋ ሲናፈቅ የነበረውን የአብራክ ክፋይ ከሷ ቀድማ  አስደማሚውን ጉብል ልጅ ለውዱ የረዥም ግዜ ፍቅረኛዋ ዱብ ማድረጓ አስደነገጣት።

> ምን ትሁን   !
> ምን ታድርግ  !
> እንዴትስ ለአላህና ለመልእክተኛው ህግጋት ትደር   !

የደረሰባት ታውቃለች ይባል የለ  / / /
                                             • • •

   ለፈጣሪ አምላኳ ለአላህ በማደር ፣ በሱ ይሁንታ በመራመድ፣  እንደ ፈቃዱ የመጣውን በመቀበልና የባሏን መመርያዎች በመተግበር ግንባር ቀደም የሆነችው ሳራ … ፈታኝ ጉዳይ ገጠማት።

   የፍቅረኛዋን ልብ የሚሻማባት ጉድ መጣባት ፣ የምታየውን በዝምታ ማስተናገድም አቃታት፣ ማንም በወዳጁ ላይ ይቀናልና እሷ ጓጉታ ያጣችውን፣ ተስፋዋ የመነመነበትን ጉብል ልጅ ስታይ መቋቋም ከበዳት።

   በክፋት መኗኗርም ባህሪዋ ስላልነበር በሚዛናዊነት ውስጧን የረበሸው ጉዳይ የሚበርድላትን መንገድ ቀየሰች። ሃጀርና ልጇ ከአይኗ እንዲርቁላትም ኣሰበች።
               
           󾁇              󾁇 

   ራሳችንን የነቢዩ ኢብራሂም ﷺ ቅጥር ግቢ ውስጥ ኣስገብተን፣ የቤተሰቡ አካል ኣድርገን እናስበው…

° ኢብራሂም ለምን ይሆን ልጅና ሚስቱን የሚሸኘው  ?

° ሃጀር ስለምን ይሆን ከነጨቅላዋ የምትባረረው   ?

° ሳራስ ስለምን  ውለታዋን መድገም አቃታት   ?

        ምን ተደግሶ ይሆን ❗

󾮜 ሙሀመድንም ﷺ ያገኘነው ከዚሁ ምንጭ ውስጥ ነው።

 ክስተት 5
ቀጣዩ ቀደር
°•••••••••••°

   አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ነቢዩ ኢብራሂምን አለይሂ አሰላም ያሉበትን የፍልስጢንን ምድር ለቅቀው ……
_________

       ሙሐመድ ﷺ 
የአንፀባራቂው ታሪክ ባለቤት
ይቀጥላል …  …
_________
󾔧احمد سيرة  abufewzan
  28 Rabi'e al-awal 1436
 19Jan15‎
<•> ማንን ነው የወደድነው ? <•>
ሙሐመድ ﷺ
የአንፀባራቂው ታሪክ ባለቤት
ከመነሻ እስከ መድረሻ
ክፍል - 2

ክስተት 4
ቀጣዩ ቀደር
°•••••••••••°
አላሁ አዝዘ ወጀለ ከኣንዱ ቀደር ወደ ሌላኛው እየነዳንና እያሸጋገረን እነሆ የሙሀመድን ﷺ ማንነትና መነሻ ከሺሆች አመታት በፊት የተደገሰውን ከርቀት እያሳየን ግብዣውን ቀጠለ።
እመቤት ሳራ ለውዱ የአላህ አገልጋይና ተፈቃሪ መልእክተኛው ለነቢዩ ኢብራሂም ﷺ ባቀረበችለት ውድ ስጦታ ሰበብ እመት ሃጀር የበኩር ልጁን ኢስማዒልን ኣረገዘች።

እመቤታችን ሳራ እድሜዋ ገፍቷል፤ ነቢዩ ኢብራሂም ወደ ሽምግልናው ገብተዋል፤ እስከዚያን ወቅት ድረስም የመውለድ እድል አልገጠማቸውም ፍሬ ኣፍርተውም የአይን ማረፍያ ሊያገኙ አልቻሉም።
ዘንድሮ ግን አዲስ ብስራት መጣ ። ድንቅ ስጦታዎችም ኢብራሂምና ሳራ ላይ አንዣበቡ።
የታላቁ የነቢያት አባት ወደ ተውሂድ ጥሪ እንደቀጠለ ነው ። ሰዎችን ከባእድ አምልኮ የማስጠንቀቅ ና ልዕለ ሃያሉን ፈጣሪ አላህን በብቸኝነት እንዲያመልኩ የሚያደርጉትን ጥሪ በየደረሱበት እየገፉበት ነው።
የዚህም ቆራጥነት ሽልማት በተለያዩ አቅጣጫዎች " ለከሊሉላህ " እየጎረፉ ነው።
~ ከግፈኛ መሪዎች ሴራና ፈተና ማምለጥ
~ በስተርጅና ደጋፊና ህይወትን ከምታጣጥም አዛኝ እውነተኛ ወዳጅ ጋር መዝለቅ
~ ቤታቸውንና ህይወታቸውን ሞቅ የምታደርግ የታረመች ጉብል በክብር ማግኘት
~ ተስፋ በደበዘዘበት የእድሜ ደረጃ ተተኪ ትውልድ፣ የበኩር ልጅ ፣ የስጋው የደሙ ክፋይ ፣ የአይን መርጊያ፣ የልብ ማረፍያ ማግኘት… … ቀጥሏል

የተከበረችዋ ሳራ ለባሏና ለአጫዋቿ ለሃጀር በዋለችው ታላቅ ውለታ ደስተኛና እርካታ የተሰማት ብትሆንም ሰው እንደመሆንዋ እንደ እንስትነቷም የባለቤቷ ከሌላ ሴት ልጅ ማፍራት ቆንጠጥ አደረጋት ፣ ውስጧን ረበሻት።
• ይህንን ውለታ አስተውሉት
• ይህንን ፍቅር ኣስቡት
• ይህንን ትእግስት ገምቱት
• ሳራም በራስዋ አልወጠነችም
• ኢብራሂምም ﷺ ያለ ትእዛዝ አልፈፀመም
የአላህ ውሳኔ ይቀጥላል
የሙሀመድ ﷺማንነትም ይታያል

ለሣራ ትናንት አጫዋች አገልጋይዋ የነበረች፣ እንደፈለገች እንድታዝባት የተሰጣት ወጣት ዛሬ ባሏን ተካፋይ፣ ቤቷን ተጋሪ ከመሆንም ኣልፋ ሲናፈቅ የነበረውን የአብራክ ክፋይ ከሷ ቀድማ አስደማሚውን ጉብል ልጅ ለውዱ የረዥም ግዜ ፍቅረኛዋ ዱብ ማድረጓ አስደነገጣት።
> ምን ትሁን !
> ምን ታድርግ !
> እንዴትስ ለአላህና ለመልእክተኛው ህግጋት ትደር !
የደረሰባት ታውቃለች ይባል የለ / / /
• • •
ለፈጣሪ አምላኳ ለአላህ በማደር ፣ በሱ ይሁንታ በመራመድ፣ እንደ ፈቃዱ የመጣውን በመቀበልና የባሏን መመርያዎች በመተግበር ግንባር ቀደም የሆነችው ሳራ … ፈታኝ ጉዳይ ገጠማት።
የፍቅረኛዋን ልብ የሚሻማባት ጉድ መጣባት ፣ የምታየውን በዝምታ ማስተናገድም አቃታት፣ ማንም በወዳጁ ላይ ይቀናልና እሷ ጓጉታ ያጣችውን፣ ተስፋዋ የመነመነበትን ጉብል ልጅ ስታይ መቋቋም ከበዳት።
በክፋት መኗኗርም ባህሪዋ ስላልነበር በሚዛናዊነት ውስጧን የረበሸው ጉዳይ የሚበርድላትን መንገድ ቀየሰች። ሃጀርና ልጇ ከአይኗ እንዲርቁላትም ኣሰበች።

ራሳችንን የነቢዩ ኢብራሂም ﷺ ቅጥር ግቢ ውስጥ ኣስገብተን፣ የቤተሰቡ አካል ኣድርገን እናስበው…
° ኢብራሂም ለምን ይሆን ልጅና ሚስቱን የሚሸኘው ?
° ሃጀር ስለምን ይሆን ከነጨቅላዋ የምትባረረው ?
° ሳራስ ስለምን ውለታዋን መድገም አቃታት ?
ምን ተደግሶ ይሆን
ሙሀመድንም ﷺ ያገኘነው ከዚሁ ምንጭ ውስጥ ነው።
ክስተት 5
ቀጣዩ ቀደር
°•••••••••••°
አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ነቢዩ ኢብራሂምን አለይሂ አሰላም ያሉበትን የፍልስጢንን ምድር ለቅቀው ……
_________
ሙሐመድ ﷺ
የአንፀባራቂው ታሪክ ባለቤት
ይቀጥላል … …
_________
احمد سيرة abufewzan
28 Rabi'e al-awal 1436
19Jan15