Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሡሉ ሠላሣ ከአጭር ማብራሪያ ጋር ክፍል 3

አላህ ይዘንልህ እና በወንድ እና በሤት ሙስሊሞች ላይ.እነዚህን ሦስት ቁም ነገሮች ማወቁ. እና በነሡም መስራቱ ግድ. እንደሚሆንባቸው እወቅ.

አንደኛ. አላህ ፈጥሮ እና ሢሣይን ለግሦ ሢያበቃ እንዲሁ (በከንቱ) አልተወንም ።ይልቁን ወደኛ መልእክተኛን ላከ ። መልዕክተኛውን የታዘዘው ጀነት ይገባል መልዕክተኛውን ያመፀ እሣት ይገባል¹

መረጃ
አላህ እንዲህ ይላል ፦ «እኛ በእናንተ ላይ መስካሪ መላዕክተኛን ላክን ወደ ፈርኦን
(ፊራኦን) መልእክተኛን እንደላክን (15) ፈርኦንም መልዕክተኛውን አመፀ ብርቱ የሆነ  አያያዝንም ያዝነው »(ሙዘሚል 15 ―16)

ሁለተኛ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ የቅርብ መላኢካም ቢሆን ፣ የተላከ ነብይ በኢባዳ እንዲጋራበት አይወድም²

መረጃ

አላህ እንዲህ ይላል ፦ «መስገጃ ቦታዎች በአጠቃላይ ለአላህ ናቸው ከአላህ ጋር
አንድንም አትገዙ »

ሦስተኛ ፦ መልእክተኛውን የታዘዘ እና በአላህ አንድነት ያመነ ሠው የቅርብ ዘመዶቹ እንኳን ቢሆኑ ከአላህ ጠላት ጋር መወዳጀት (የልብ ወዳጅ አድርጎ መያዝ) አይበቃለትም³

መረጃ
አላህ እንዲህ ይላል ፦ « በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ህዝቦች አላህ እና መልዕክተኛውን የሚከራከሩትን ሠዎች አባቶቻቸው ፣ ልጆቻቸው ፣ ወንድሞቻቸው ወይም ዘመዶቻቸው ቢሆኑም እንኳን የሚወዳጁ ሆነው አታገኛቸውም ።እነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ
እምነትን ፅፏል ከሡም በሆነ መንፈስ ደግፏቸዋል ። ከስሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሡባቸው ገነቶች በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሢሆኑ ያስገባቸዋል አላህ ከነሡ ወዷል ከእርሡም ወደዋል.። እነዚያ የአላህ ህዝቦች ናቸው ። ንቁ! የአላህ ህዝቦች ምኞታቸውን የሚያገኙ
ናቸው ። » (ሙጃደላ 22))
---------------------------------
አጭር ማብራሪያ
-----------------
¹ የዚህ ኪታብ ፀሀፊ እንዲህ አሉ «
አላህ ፈጥሮ እና ሢሣይን ለግሦ ሢያበቃ እንዲሁ (በከንቱ) አልተወንም ።ይልቁን ወደኛ መልእክተኛን ላከ ። መልዕክተኛውን የታዘዘው ጀነት ይገባል መልዕክተኛውን ያመፀ እሣት ይገባል»

ከዚህ ንግግራቸው ከአምስት በላይ ነገሮችን እንረዳለን

1,የአላህ ፈጣሪነት.እና ሢሣይ ለጋሽነት ፦ አላህ ምድርንም ፣ ሠማይንም እንዲሁም.
በውስጣቸው ያለውን ነገር በአጠቃላይ ያለ ምንም አጋዥ የፈጠረ መሆኑን.

ይህንን ከደህርዬች እና ከአንዳን ጠማማ ግለሠቦች በቀር. በአለም ላይ ያሉ ሠዎች በአጠቃላይ ያምናሉ ይህንንም አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ እንዲህ ሲል ይነግረናል

« ሠማይና ምድርን ማን ነው የፈጠረ ብትላቸው አላህ ነው ይሉሀል»

ይህ  ርእስ በአሁን.ሠአት ብዙም አሣሣቢ ካለመሆኑም ጋር (ምክንያቱም ሁሉም በአላህ ፈጣሪነት ስለተስማሙ) አንዳንድ ሠዎች (ጀመአዎች) ግን ይህንን ርእስ እንደ ትልቅ የኡማው ጉዳይ.(ችግር) አድርጎ በማሠብ አብዘሀኛው ወይም ሙሉ የዳእዋ አካሔዳቸውን ይህንን የተውሒድ ክፍል መስበክ አድርገውታል በዚህም ተግባራቸውን ወደ ተውሒድ እየተጣሩ እንደሆነ ያስባሉ ይህ አካሔድ ከሸሪአ አንፃር ልክ አይደለም አብዘሀኛውን
የዳእዋ ግዜአቸውን ሊወስድ የሚገባው ሁለተኛው የተውሒድ አይነት ነው (ኢንሻአላህ ወደ ፊት ይብራራል)

2, የሠው ልጅ ለጨዋታ እና ለዛዛታ እንዳልተፈጠረ ፦ አላህ ከእንዲህ አይነት ተግባር (የሠውን ልጅ ያለ ምንም አላማ ከመፍጠር) የፀዳ የሆነ ጌታ ነው የሠው ልጅ እንዲሁ በከንቱ እንዳልተፈጠረ የሚያመላክቱ በርካታ አናቅፆች አሉ ለአብነት ያክል፦

««የፈጠርናችሁ ለከንቱ መሆኑን እናንተም ወደ እኛ የማትመለሡ መሆናችሁን
ጠረጠራችሁን (115) የእውነቱም ንጉስ አላህ ከፍተኛነት ተገባው…»»ሙእሚን

«የሠው ልጅ. ስድ ሆኖ መተውን ይጠረጥራልን »ቂያማ

የሠው ልጅ ለአንድ ለትልቅ ጉዳይ ነው የተፈጠረው አላህ እንዲህ ሢል ይነግረናል

«« ጋኔንም ሆነ የሠውን ልጅ እኔን ሊገዙኝ ቢሆን እንጂ አልፈጠርኳቸውም»

ከዚህ አያ የተፈጠርንበትን አላማ እንረዳለን እሡም አላህን በብቸኝነት መገዛት ነው!!!

3 የአላህ መልእክተኛን መላክ ፦ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ የሠው ልጆችን ከሽርክ
የሚያስጠነቅቁ እና ወደ ተውሒድ የሚያጣሩ መልእክተኞችን ጊዜውን ባማከለ መልኩ ለሁሉም ህዝብ የቂያማ ቀን የሠው ልጆች  መልዕክቱ መድረሡን እንዳያስተባብሉ  መሥካሪ አድርጎ ልኳል. አላህ እንዲህ ሲል ይነግረናል

" መልዕክተኞች አስጠንቃቂ እና አበሣሪ ናቸው ።ሠዎች በአላህ ላይ ከመልዕክተኛ ቡሀላ መረጃ እንዳይኖራቸው""

የሠው ልጆች መልዕክቱ (ኢስላም) አልደረሠንም ብለው በአላህ ላይ መከራከርያ እንዳይኖራቸው ፍትሀዊ የሆነው አላህ ለእያንዳንዱ ህዝብ መልእክቱን የሚያደርሡ መልዕክነኞችን ላከ መጀመርያቸው ኑህ መጨረሻቸው ደግሞ ሙሀመድ ሠለላሁ አለይሒ
ወሠለም ናቸው (ኢንሸአላህ ወደ ፊት በሠፊው ይዳሠሣል)

4 መልዕክተኛን መታዘዝ ፦ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ኢስላምን ያብራሩልን ዘንዳ የላካቸውን መልዕክተኞች እንድንታዘዛቸው አበክሮ ነግሮናል
አላህ እንዲህ ይላል «ይታዘንላቹ ዘንዳ አላህ እና መልዕክተኛውን ታዘዙ»
እንዲህ ሢል ካዘዘን ቡሀላም መልዕክተኛውን ለሚታዘዙ ሠዎች ያዘጋጀላቸውን እንዲህ ሢል ይነግረናል
«አላህ እና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ከስሮቹ ወንዞች የሚፈሱባት የሆነን ገነት
ዘውታሪዎች ሢሆኑ ያስገባቸዋል ።ይህ ታላቅ እድል ነው»

5 መልዕክተኛውን ማመፅ ፦ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ መልዕክተኛን ልኮ እንድንታዘዘው ካዘዘን ቡሀላ እንዳናምፀውም ከማስጠንቀቂያ ጋር ነግሮናል

አላህ እንዲህ ይላል ፦«አላህና መልእክተኛውን የሚያምፅ ድንበሩንም የሚያልፍ እሣት.ውስጥ ዘውታሪ ሢሆን ያስገባዋል ለሡም አሣማሚ ቅጣት አለው

 ""
² የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ ፦ አላህ የቅርብ መላይካም ሆነ መልዕክተኛ በኢባዳ እንዲጋራበት አይፈልግም

ከዚህ ንግግራቸው ሁለት ነገር እንውሠድ
1 ኢባዳ ፦ ኢባዳ ማለት« ከንግግር ፣ በልብ እና በውጪው የሠውነት ክፍል የምንሠራቸው አላህ የሚወዳቸው ተግባራቶች ማለት» ነው ለምሣሌ ሠላት ፣ፆም፣ዚክር፣ዱአ፣ፍራቻ ፣የይድረሡልኝ ጥሪ የሚጠቀሡ ናቸው ።

2 ሽርክ ፦ ሽርክ ማለት ፦ ከኢባዳ አይነቶች አንዱን ከአላህ ውጪ ላለ አካል አሣልፎ መስጠት (በአላህ ፍቃድ ቁ。1&2. ቦታቸው ላይ ስንደርስ በሠፊው ይብራራል)

³በ አላህ ብቸኝነት ያመነ እና መልእክተኛውን የታዘዘ ሠው ከአላህ እና ከመልዕክተኛው ጠላት ጋር የልብ ወዳጅ መሆንን የሚከለክሉ በርካታ የቁርአን እና የሀዲስ መረጃዎች አሉ  ከላይ የዚህ ኪታብ ፀሀፊ ያሠፈሩት መረጃ እንደ ምሣሌ መውሠድ ይቻላል!!!