Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሡሉ ሠላሣ ከአጭር ማብራሪያ ጋር ክፍል 2

‎ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻢ ¹

የአለማቱ ጌታ ለሆነው ለአላህ ምስጋና ይገባው የአላህ ሠላት እና ሠላም የነብያት
መደምደሚያ በሆኑት በሙሀመድ ላይ ይውረድ

በመቀጠል የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ ይላል
አላህ ይዘንልህ² እና በእኛ ላይ ልናውቃቸው የሚገቡ አራት ቁም ነገሮችን እወቅ

አንደኛው፦ እውቀት ፦ አላህን ፣መልእክተኛውን እና ዲነል ኢስላምን በመረጃ ማወቅ ³

ሁለተኛው ፦ ባወቀው ነገር መስራት ⁴

ሦስተኛ ፦ ወደ አወቀው እና ወደ ተገበረው ነገር ጥሪ (ዳእዋ) ማድረግ ⑤

አራተኛው ፦ ዳዕዋ በሚያደርግበት ግዜ ለሚደርስበት መከራና ችግር ትዕግስት ማድረግ ⑥

መረጃ ፦ አላህ እንዲህ ይላል ""በጊዜያት እምላለው ፣ሠው ሁሉ በኪሣራ ውስጥ ነው ያለው ፣እነዚያ ያመኑት: መልካምን የሠሩ: በእውነትም አደራ የተባባሉ: በትዕግስትም አደራ የተባባሉ ሢቀሩ ""(ሡረቱል አስር)⑦

ኢማሙ ሻፊዕይ አላህ ይዘንላቸው እና እቺን ሡራ አስመልክተው እንዲህ አሉ « አላህ ከእዚች ሡራ በቀር ሌላ ምዕራፍ ባያወርድ ኖሮ ይህች ሡራ ትበቃቸው ነበር »
ቡኻርይ አላህ ይዘንላቸው እና በመፀሀፋቸው ላይ ይህንን ምእራፍ አሠፈሩ. ""ምዕራፍ ፦
እውቀት ከስራም ከንግግርም በፊት ነው ፦ መረጃ. ፦ አላህ እንዲህ ይላል ""እወቅ እነሆ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም " ሡረቱል ሙሀመድ
________
አጭር ማብራርያ
_____________
¹( ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ )

በንግግሩ መጀመርያ ላይ ይህንን ቃል ያስገባው (( ( ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ ))) የሚለውን ሁለት ነገሮችን አስቦ ነው

1 በረካ ፦ አላህ ይህንን የእውቀት ማዕድ በረካ ያደርገው ዘንዳ ፣እስቲቃማ ይሠጠን ዘንዳ ታስቦ ነው

2 የነብዩን ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እና የነብያቶችን ሡና ከመከተል አንፃር ነው
ትርጉም ፦

★ቢስሚላህ ( ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ .)) አላህ  የሚለው "ተአሉህ " ከሚለው ቃል የተያዘ ሢሆን የሚዋረዱለት ፣ የሚተናነሡለት በጥቅሉ የሚያመልኩት የሚል ትርጓሜ የያዘው  ከአላህ ስሞች መካከል አንዱ ነው በዚህ ስም በልቅ ከአላህ ውጪ ያለን አካል  መሠየም (መጥራት) አይበቃም! 

★አርረህማን(( ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ )) አርረህማን የሚለው አላህ ስም እና ባህሪዎች መካከል አንዱ ነው በዚህ በልቅ መሠየሙ (መጠራቱ) አይበቃም ትርጉሙም ሁሉን ያካበበ እዝነተ ሠፊ
ማለት ነው (ይህ የእዝነት አይነት አላህ ለሙስሊሙም ለካፊሩም የሚያዝነው የእዝነት
አይነት ነው)
★ አርረሒም(( ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ))ይህም እንደመጀመርያዎቹ ከአላህ ስሞች መካከል የሚቆጠር ነው
ይህም ለሙዕሚኖች ብቻ የሚያዝንበቶ የእዝነት ስሙ ነው
² የዚህ ኪታብ ፀሀፊ አላህ ይዘንልህ አሉ. ይህንን ኪታብ በሚቀራ ሠው ላይ እዝነትን
አወረዱ ትርጉሙም ((አላህ የምትፈልገውን ነገር ይስጥህ ከምትፈራው ነገር ይጠብቅህ))
ማለት ነው
³ የኪታቡ ፀሀፊ አራት ነገሮችን ማወቅ እንዳለብን ከነገሩን ቡሀላ አንደኛ እውቀት አሉ
እሡም
★ አላህን ማወቅ ፦ አላህን ማወቅ ማለት የደነገገውን አምኖ መቀበል ፣ ረሡል ሠለላሁ
አለይሒ ወሠለም ይዘው የመጡትን ነገር መቀበል ማለት ሢሆን አንድ ባርያ ቁርአን ውስጥ
የተጠቀሡትን ፣ በሀዲስ የሠጡትን ፣ በአጠቃላ ምድር ላይ የሚከሰቱትን ነገሮች
በመመልከት ጌታውን (አላህን) ያውቃል አላህ እንዲህ ይላል (በምድር ላይ ለአረጋጋጮች
ተአምር አለ ፣ወደ ነፍሦቻችሁ አትመለከቱምን?))

★ መልዕክተኛውን ማወቅ ፦ ነብዩን ማወቅ ሢባል አራት ነገሮችን ያቅፋል
1 የተናገሩትን እውነት ማለት
2 ያዘዙትን መታዘዝ
3 የከለከሉትን መከልከል
4 እሣቸውን ማስፈረድ (የፈረዱትን ነገር መውደድ)
አላህ እንዲህ ይላል ( በአንዳች ነገር በተለያያቹ ግዜ ወደ አላህ እና ወደ መልእክተኛው መልሡት)

★ ዲነል ኢስላምን ማወቅ ፦ኢስላም የሠው ልጆች ከተፈጠሩበት ሠአት አንስቶ እስከ ይህች አለም የመኖር ጊዜዋ እስከሚያበቃበት (እስከ ቂያማ) ድረስ የሚቀር እምነት ነው ዲነል ኢስላምን ማወቅ ማለት ቁርአን እና ሀዲስ ያዘዙትን መታዘዝ የከለከሉትን መከልከል ማለት ነው

⁴ ባወቀው ነገር መስራት ፦ ባወቀው ነገር መስራት የአንድ እውቀት ፍሬው ነው! አንድ ሠው ያለ እውቀት የሚሠራ ከሆነ ከነሣራዎች ጋር ይመሣሠላል አውቆ የማይሠራበት ከሆነ ደግሞ ከየሁዳዎች ጋር ይመሣሠላል

⑤ ወደ አወቀው እና ወደ ተገበረው ነገር መጣራት ፦ ይህ ማለት ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ይዘው ወደመጡት ሸሪአ መጣራት ማለት ሢሆን አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ሦስት እርከኖችን አድርጎለታል አላህ እንዲህ ይላል ""ወደ ጌታህ መንገድ በጥበብ ፣ በለዘብታ
ቃል ፣ በዛች መልካም በሆነች ቃል እየተከራከርክ ተጣራ ""
ሦስቱ እርከኖች
1 ጥበብ ለሚያስፈልገው ሠው በጥበብ
2 ምክር ለሚያስፈልገው ሠው በምክር
3 ክርክር ለሚፈልግ ሠው ደግሞ መልካም በሆነችው በመከራከር.
ይህንን ዳዕዋ የሚያደርገው ሠው ዳእዋ ስለሚያደርገው ነገር.እና ዳእዋ ስለሚያደርግለት
ሠው የጠለቀ እውቀት ሊኖረው ይገባል እንዲህ ካልሆነ
1 ባለማወቅ አላህና መልዕክተኛው ላይ ሊዋሽ (ሊሣሣት) ይችላል
2 ዳእዋ የሚያደርግላቸውን ሠዎች ልክ (ደእውቀት መጠን) ካላወቀ ያለ አቅማቸው
ያሸክማቸውና ሊያጠማቸው ይችላል
አላህ እንዲህ ይላል ፦ ይህች እኔ እና እኔን የተከተሉ ሠዎች በዕውቀት ላይ ሆነን ወደ
አላህ የምንጣራባት መንገዴ ናት በላቸው "
⑥ ዳእዋ በሚያደርግበት ግዜ በሚደርስበት ችግር ትእግስት ማድረግ ፦ ትዕግስት ማለት
አላህን በመታዘዝ ላይ መቆየት ፣አላህን ባለማመፅ ላይ መቆየት ፣ በአላህ ውሣኔ ቅር
አለመሠኘት ማለት ነው ሁልግዜ ወደ አላህ መንገድ በመጣራት ላይ መቆየት ምንም
አይነት ችግር እና መከራ ቢደርሶበት ማለት ነው ።ምንግዜም ቢሆን ወደ ሀቅ የሚጣራ
ሠው የሠው እና የሸይጣን ጂኒዎች አዛ እንደሚያደርጉት እሙን ነው ወደ አላህ የሚጣራ
ሠው ይህንን አውቆ ትዕግስት ማድረጉ የግድ ነው ይህን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል
((እንደዚሁ ለነብይ ሁሉ ከአመፀኞች የሆኑ ጠላትን አድርገናል ።መሪና ረዳትም በጌታህ
በቃ)) የዚህ አያ ሒጣቡ (ንግግሩ) ለነብዩ ቢሆንም የሣቸውን ስራ እየሠራ ያለ ሁሉ
ይመለከተዋል!!
⑦ አላህ በግዜያት እምላለው አለ ፦ አላህ የሚምልባቸውም ነገሮች የሚምልላቸውም
ነገሮች ከባባድ ነገሮች ናቸው
★ የማለበት ነገር ፦ አላህ በፈለገው ነገር መማል ይችላል የተለያዩ የቁርአን አናቅፆች
ላይ በተለያዩ ነገሮች ይምላል ለምሣሌ (በቀን ፣በለሊት ፣በፀሀይ ፣በጨረቃ ፣በራሡ) እና
በተለያዩ ትልቅ በሆኑ ነገሮች ይምላል እዚህ ጋር በጊዜ ማለ ከዚህ የምንረዳው በኢስላም
ውስጥ የጊዜን ትልቅነት ነው ። ይህም ሢሆን ለሠው ልጅ ግን በእናቱም ፣ በአባቱም
፣በሼሆችም ፣ በቁርአንም በአጠቃላይ ከአላህ ውጪ ባለ ነገር መማል አልተፈቀደለትም
ከማለም ትንሹን ሽርክ ፈፅሟል ይባላል ።
★ የማለለት ነገር ፦ የሠው ልጆችን ከኪሣራ ሊያወጣ የሚችል ለሆነ ወሣኝ ጉዳይ
እሡም
አላህን ማወቅ ፣ባወቀው ነገር መሥራት ወደ አወቀው ነገር መጣራት እና ትዕግስት
ማድረግ ናቸው

share ማድረጎን እንዳይረሡ‎
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻢ ¹

share ማድረጎን እንዳይረሡ