Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢብነል ቀይም (ረሂመሁላህ) ሚፍታሁ ዳሩ ሰዓዳ የተሰኘ ኪታባቸው ላይ የንጉሶችን እና መሪዎችን ተግባር የህዝቦች ስራ ውጤት እንደሆነ እንዲህም ሲሉ ያስቀምጣሉ


ኢብነል ቀይም (ረሂመሁላህ) ሚፍታሁ ዳሩ ሰዓዳ የተሰኘ ኪታባቸው ላይ የንጉሶችን እና መሪዎችን ተግባር የህዝቦች ስራ ውጤት እንደሆነ እንዲህም ሲሉ ያስቀምጣሉ

‹‹አስተውል፤ አስተንትን ከፍ ባለው ጌታ ጥበብ፤ የባርያዎችን የሚመሩዋቸው ንጉሶች እና መሪዎች እንደባርያዎች ተግባር፤ ዝርያ (አምሳያ) ያደረገ፡፡ ቢጤን ለቢጤው፤ ጥሩን ለጥሩ መጥፎን ለመጥፎ፡፡››
እንዲያውም የባርያዎች ተግባር የመሪዎቻቸው መገለጫ እስኪመስል ድረስ፡፡ የነሱ (የባርያዎች) ተግባር የመሪዎቻቸው ነፀብራቅ እስኪመስል ድረስ፤ ንጉሶች ማለት እራስን በመስታወት እንደማየት እስኪመስል ድረስ፡፡ ቢጤን ለቢጤ ይህ ሁሉ የባርያዎች ተግባር ነው፤ እጆቻቸው ያስቀደሙት ውጤት ነው፡፡

ባርያዎች ቀጥ ካሉ (አምልኳቸውን ለአላህ ያጠሩ፤ ሱናን የተገበሩ) ከሆኑ መሪዎቻቸው እና ንጉሶቻቸውም ጥሩ እና የተቀኑ ይሆናሉ፡፡ ባርያዎች ጥሩ ከመሆን የተወገዱ ግዜ ንጉሶቻቸውም ጥሩ ከመሆን ይወገዳሉ፡፡
ባርያዎች በሚበድሉ ግዜ (እራሳቸውንም ይሁን ሌሎችን) ንጉሶቻቸው እና መሪዎቻቸው ይበድሏቸዋል፡፡
ባርያዎች ዘንድ ሴራ እና ማጭበርበር ካለ መሪዎቻቸው ባህሪያቸው እንደዛው ይሆናል፡፡ ባርያዎች በመካከላቸው ያለን የአላህ መብት ሲከለክሉ እና ስስታም ሲሆኑ ንጉሶቻቸው እና መሪዎቻቸው እነሱ (ባርያዎች) ላይ ያላቸውን መብት ይይዙባቸዋል፤ ባርያዎችን አስመልክቶ (ንጉሶች) ስስታም ይሆኑባቸዋል፡፡

እስቲ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መንገድ ልብ ብለህ ተገንዘብ እና ለውጥ ከየት እንደሚመጣ ተመልከት
ذَٰلِكَ بِأَنَّ ٱللَّهَ لَمْ يَكُ مُغَيِّرًا نِّعْمَةً أَنْعَمَهَا عَلَىٰ قَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا۟ مَا بِأَنفُسِهِمْ ۙ وَأَنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٌ
ይህ (ቅጣት) አላህ በሕዝቦች ላይ የለገሰውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን ነገር እስከሚለውጡ ድረስ የማይለውጥ በመኾኑ ምክንያት ነው፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡
إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا۟ مَا بِأَنفُسِهِمْ ۗ وَإِذَآ أَرَادَ ٱللَّهُ بِقَوْمٍ سُوٓءًا فَلَا مَرَدَّ لَهُۥ ۚ وَمَا لَهُم مِّن دُونِهِۦ مِن وَالٍ
አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን (ኹኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም፡፡ አላህም በሰዎች ላይ ክፉን በሻ ጊዜ ለእርሱ መመለስ የለውም፡፡ ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም ተከላካይ የላቸውም፡፡
........
እናም ለዛ ነው የመጀመሪያዎቹ ምርጥ ትውልዶች (ምርጡ 3 ክፍለ ዘመን እና 3 ትውልድ) መሪዎቻቸው እንደነሱ (ምርጥ) ነበሩ፡፡ (ከዛ በኋላ) የተበላሹ ባርያዎች ሲሆኑ መሪዎቻቸው የተበላሹ ሆኑ፡፡
የአላህ ጥበብ ትከለክላለች (ኢብነል ቀይም ስለ እራሳቸው ዘመን እያወሩ 8ኛው መቶ ሂጅራ) የአላህ ጥበብ ትከለክላለች አደለም አቡበክር እና ኡመርን፤ ሙዓዊያ እና ኡመር አብድል አዚዝን በእኛ ላይ መሾም (የአላህ ጥበብ) ትከለክላለች፡፡ ይልቁንስ መሪዎች የእኛ ተፈጥሮ (ባህሪ ነፀብራቅ) ነው ያላቸው፤ ከእኛ በፊት የነበሩትም እንደዛው፡፡

ከሸይኽ ሙሃመድ ሰዒድ ረስላን (ሀፊዘሁላህ) ትምህርት የተወሰደ፡፡
ዛሬ አለማችን ላይ ሽርክ ተንሰራፍቶ፤ ቢድዓ ነግሶ፤ ተውሂዱ ሽርክ ሽርኩ ተውሂድ፤ ሱናው ቢድዓ ቢድዓው ሱና እስኪመስል ደርሶ፤ ወንጀል እንደ ቀላል ታይቶ፤ ሃጅ ወጅቦባቸው ስንቶች ሳይተገብሩት፤ ዘካ ስንቶች ሳያወጡ፤ የወላጆች ሃቅ ተጓድሎ አረ ስንቱ አላህ በብዙ ወንጀሎች ታምፆ ጥሩ መሪን መከጀል የዋህነት ነው፡፡ አላህ እራሳቸውን ቀይረው ጥሩ መሪ ከሚያገኙት ያድርገን፡፡