Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለወንድም Hamsa hamsa የተላከ አጭር ማስታወሻ


ለወንድም Hamsa hamsa የተላከ አጭር ማስታወሻ። የመካ ሙሽሪኮች ለረሱል ጨረቃው ለሁለት ከተገመሰልህ እናምንልሀለን ብለው፣ አላህም ለሁለት ሲከፍለው ጊዜ አይ ይሄ ድግምት ነው አንቀበልም ብለው እንደሹት እንዳትሸሽ እንጂ ሙስሊም መሪዎቹ እስከሰገዱ ድረስ አረመኔ ገዳይ ቢሆኑ፣ ኢስላምንም ሙስሊሞችንም የሚጎዳ ነገርን ቢሰሩ በነሱ ላይ ማመፅ የሚከለክሉ ከ100 በላይ ሰሂህ ሀዲሶችን እናቀርብልሃለን።

አቡ ሃማድ ኢብኑ ዐብዱላህ ኢብን ሙስሊም ኢብን ያሲር ረሒመሁላህ እንዲህ አሉ
‹‹ (ታላቁ አሊም) ኢብኑ ሲሪን የታሰሩ ጊዜ የእስር ቤት ጠባቂው እንዲህ አላቸው
‘‘ የሌሊት ወቅት በመጣ ጊዜ ወደ ቤተሰቦችህ ሂድ ሲነጋም ትመልሳለህ’’
ኢብን ሲሪንም :-
‘‘ በጭራሽ! በአላህ ይሁንብኝ (ሙስሊም) መሪህ ላይ ክህደትን እንድትፈፅም አልተባበርክም’’ ››
[ምንጭ፡- ጠሪቅ በጝዳድ ሊል ኸጣብ በጝዳዲ]

ሸኽ ዑሰይሚን ረሒመሁላህ ቀጥለውም ይሄን ሃዲስ ተናገሩ
(ሙስሊም) መሪያቹን ትዕዛዙን ተቀበሉ ፤ ምንም እንኳን ጀርባቹን እየመታ ንብረታቹ ቢነጥቃቹም መስማትና መታዘዝ አለባቹ ። ሰሒህ ሙስሊም
ምኞታቹ ልክ እንደ አቡ በክር ዑመርና ኡስማን አሊይ አይነት መሪ ከሆነ እሱ አይቻልም ። በቅድሚያ እናንተ ልክ እንደ ሰሃባዎች መሆን ይጠበቅባቿል ያኔ በሰሃቦች ጊዜ እንደነበሩት ኸሊፋዎች እነሱም ይሆኑላቿል ።
ነገር ግን ወጣቶች ዛሬ ላይ እንደምናውቀው አብዛኞቻቸው ዋጂባቶችን (የግዴታ ድንጋጌዎችን) (ንቀው) ትተዋቸዋል ። እናም ሃራም የሆነውን ነገር ተዳፍረውታል ። ነገር ግን አሁንም አላህ ደግ የሆኑ ኸሊፋዎችን እንዲሰጣቸው ይመኛሉ ። ነገር ግን ይሄ ከማሰብም እራሱ የራቀ ነው ። በናንተ ላይ መስማትና መታዘዝ ነው ያለባቹ ። ይሄን ነገር የጣሰውም ካለ ጥሰቱ በርሱ ላይ ነው ። በነሱ ላይ (በመሪዎች) የሰሩት ስራ (መጥፎም ይሁን ጥሩ) ቀንበር ፣ ሸክም ነው ያለባቸው ። በኛ ላይ የሰራነው ስራ ቀንበር ሸክም ነው ያለብን።

ስለዚህም መሪዎችና ኡለማዎች ክብር ያጡ ዕለት ያኔ ዲንም ዱኒያም ሁለቱም ይታጣሉ ። መልካም መሆንን አላህን እንጠይቀዋለን ። ሸርሑ ሪያዱ ሳሊሂን (3/231-233)
አንተ አረመኔ እና ሌላም እያልክ በአደባባይ የምትዘረጥጣቸውን የሳውዲ መሪዎች ሸይኽ ኡሰይሚን እንዲህ ሲሉ ስለነሱ በጥሩ ያነሳሉ
‹‹ ይሄን (የስዑዲ) መንግስት አስመልክቶ .. እንደምታውቁት ይቺ አገር የምትተዳደረው በሸሪዐ ነው ። ዳኛው የሚፈርደው በኢስላማዊ ሸሪአ ብቻ ነው ። ፆም የተደነገገ ነው ፤ ሃጅም የተደነገገ ነው ፤ መሳጂዶች ውስጥ የሚካሄዱ ዱሩሶች (ትምሕርቶች)ም የተደነገጉ ናቸው ። ስሕተትን የፈፀመም ቢሆን ፈተና ውስጥ ነው ።
መጥፎም ነገር ቢሆን ወደ መጥፎ ነገር የሚያዳርሱ ነገራቶች ሁለቱም የታገዱ ናቸው። ወደዚች ሃገር (ስዑዲ) ብንመለከት መቃብሮች ላይ የተገነቡ ነገሮችን ወይንም መቃብር ጠዋፍ ሲደረግም አናይም። ሱፍያንም ቢሆን ሌሎች ቢደዐዎችን በአደባባይ አናይም ። እርግጥ ነው አንዳንድ ሰዎች የሱፊያ ቢደዐ የተጠናወቱ ይኖራሉ ነገር ግን ለራሳቸው (ደብቀውት) ከራሳቸው ጋር ነው ። በሌላም በኩል ሁሉም ሕዝብ ጋር (በርግጥም) ምግባረ ብልሹነት አልለ ።
ነገር ግን ይሄን ወስደን ስዑዲ አረቢያን ከሌላ ሃገራቶች ጋር ስናነፃዝጽረው በጣም ብዙ ልዩነቶችን እንመለከታለን ። (ሌላ ሃገራቶች ላይ) አልኮል ኸምር በአደባባይ ይሸጣል ። በረመዳን በእኩለ ቀን ላይ ማንም ያሻው ሰው እንዲበላና እንዲጠጣ ሬስቶራንቶች ክፍት ይሆናሉ ። ሴተኛ አዳሪዎች በአደባባይ ላይ አሉ ። ወደነዚህ ሃገራት የተጓዘ ሰው እንደውም እንደነገረኝ ከሆነ ከኤርፖርት ሳይወጣ ገና
‘‘ወንዶችም ሴቶችም አሉን የቱን ትፈልጋለክ’’ ተብሎ ይጠየቃል ።
ይህ የሚከሰተው በአደባባይ ነው ። አንድ ሰው የአንድን ሃገር መሪው ላይ ያሉ ሁነቶችን ዕውነታውን ማየት ይገባዋል ። መሪው ላይ ይቅር ሊባሉ የሚችሉ መጥፎ ምግባራትን ብቻ ነቅሶ ማውጣትና ጥሩውን ግን መዘንጋት የለበትም ። ልክ ጥሩ የሚባል ምንም ስራ የሌለው ይመስል ።
ይህ ሚዛናዊ መሆን አይደለም አላህ እንዲህ ይላል
((እናንተ ያመናችሁ ሆይ ፦ ለአላህ ቀጥተኞች፣ በትክክል መስካሪዎች ሁኑ። ሕዝቦችንም መጥላት፣ ባለመስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፤ አስተካክሉ፤ እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው። አላህንም ፍሩ። አላህ በምትሠሩት ሥራ ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው።)) [ማኢዳህ ስምንት]

ሸኽ ፈውዛን (ሃፊዘሁላህ)
‹‹ ዕርግጥ ነው መሪዎች አብረዋቸው እንዳሉ ሰዎች እነሱም ከስሕተት የፀዱ አይደለም ። እነሱን መምከርም ግዴታ ነው ። ነገር ግን በነሱ ላይ ማመፅ እና ስለነርሱ በ አደባባይ ክፉ ማውራት; ተማሪዎች (በሕዝብ) ስብስብ ፊት እነሱን መውቀስ የተከለከለና ሃሜትም (ጭምር) ነው ። ይህ ክፉ ስራ ደግሞ ሃሜት ከመሆኑም ጋር መሪዎች ላይ ይባስ የከፋ ይሆናል ። ምክንያቱም ከዚህ ሃሜት የሚገኘው ትርፍ የብጥብጥን ፍሬ ስለሚዘራ (ስለሚተክል) ነው ። መከፋፈልንም ይፈጥራል ፤ ለሚካሄደው ዳዕዋም ዕንቅፋት ይሆናል ። መደረግ ያለበት ምክሩ ዕምነት በተጣለባቸው ጎዳናዎች ለንጉሱ ለራሱ እንዲደርሰው ማድረግ ነው ። እንጂ በ አደባባይ አድርጎ የህዝብ አመፅ መቀስቀስ አይደለም ..›› [አል አጁዊባ አል ሙፊዳ]

ቤተሰቦቻችን ቢታመሙ ስለምንወዳቸው ብቻ ያለ ሞያችን ፣ ያለ እውቀታችን ለማከምና መድሀኒት ለማዘዝ እንደማንሞክረው ሁሉ በዲንናችንም ላይ ያለ ሞያችንና ያለ እውቀት ዝም ብለን ባናወራ ኖሮ ይሄ ሁላ ፈተና ባልተፈጠረ ነበር!! ለሀዲሶቹ አንተ የሰጠኸው አይነት ማብራሪያ የሰጠ አንድም ሙሀዲስ የሆነ ዐሊም ሳይኖር ሀዲሱን በራስህ አመለካከት ለማብረራራት መዳፈርህ በጣም አሳዝኖኛል! ረሱል እንዲህ ለማለት ፈልገው ነው ብሎ የመናገር ክብደቱን ብታውቅ ኖሮ እንደዚህ ባልተዳፈርክ ነበር! ሰዎችን አብሽቄ የጓደኞቼን አድናቆት አተርፋለው ስትል ፣ አላህ በእሳት እንዳያበሽቅህ ተጠንቅ! ቁርአንና ሀዲስን ሁላችንም በምንፈልገው መልኩ እንተርጉመዉ ከተባለ አህባሽ ሀዲሶቹን በራሱ አመለካከት እየተረጎመ አይደል ሀራሙን ሀላል የሚየደርገው? ታዲያ እንከተለው ሊባል ነው? ረሱልና ሰሀባዎች ሙስሊሞችን የሚጨፈጭፍ ፣ኢስላምን ለአደጋ የሚያጋልጥ ኸምር የሚጠጣና ብዙ ሀጢያቶችን የሚፈፅም መሪ ላይ ማመፅን እንዴት እነደከለከሉ እስኪ እንመልከት። ሀጃጅ ኢብኑ ዩሱፍ የሚባል ብዙ ሰሀባዎችና ታቢኢዮችን የጨፈጨፈ( የገደለ )፣ በኢስላምና በሙስሊሞች ላይ ይህ ነው የማይባል ጥፉትን ያደረሰ፣ ሀጢያት ከመዳፈሩ ብዛት ሰሀባዎችን ኸምር ሁሉ ጠጥቶ ሰክሮ ያሰግዳቸው የነበረ እጅግ በጣም ግፈኛና ወንጀልን የሚዳፈር መሪ ነበር። ታላቁን ሰሀባ አብደላህ ኢብኑ ኡመርን የገደለው ይህ ግፈኛ መሪ ነበር። የሀጃጅ በደል የበዛባቸው አንዳንድ ወጣቶች ብሶታቸውን የረሱል ኻዳሚ ለነበረው ለታላቁ ሶሀባ ለአነስ ኢብኑ ማሊክ አቅርበው ነበር ። እዚህ ጋር አስተውሉ!! ለአነስ ያቀረቡት ብሶት መሪያችን ሀጃጅ ኸምር ይጣልና የመሳሰሉት አይነት በግል ይሰራቸው የነበሩ ወንጀሎችን ብቻ አልነበረም! መሪያችን ሀጃጅ ሙስሊሞችን ይጨፈጭፋል ፣ያስጨፈጭፋል በኢስላም በሙስሊሞች ላይ ትልቅ ውድመትን እያስከተለ ነው የሚልም ጭምር ነበር። ታላቁ ሰሀባ አነስም ረሱል በእንደዚህ አይነት ፈታኝ ወቅትና መሪ እንድንታገስ ነው ያዘዙንና ታገሱ! እንዳታምፁ! ብሎ ነበር የገሰፃቸው!ይህ ታሪክ ሪያዱ ሷልሂን ላይ ሰፈሮ ይገኛል። ማስረጃ ብለህ ስለ ዑመርና ስለሙአዊያ ያቀረብከው ግን ገርሞኛል! ራሳቸውቸው ዑመርና ሙዐዊያ በሌላ ዘገባ ሰለፎችም ዑለማዎችም ጭምር ምን ለማለት እንደሆነ አብራርተውታል። ለምን ማብራሪያውንም አንድ ላይ ማቅረብ እንዳልፈለክ የታወቀ ቢሆንም ሀዲስን ቆርጦና ቀጥሎ ፣ ዶዒፍ የሆኑ ሀዲሶችን እንደ ማስረጃ ማቅረብ ከሙስሊም የሚጠበቅ አይደለምና አላህን ብንፈራ ጥሩ ይመስለኛል እላለሁ። ሙስሊም መሪ በፊት ለፊትህ ወንጀል ሲሰራ ወይም ወንጀል እሰራለሁ ብሎ ቢል እዛው ፊት ለፊቱ ምከረው ነው የተባለው እንጂ ውጪ ወተህ አሳምፅ አልተባልክም! የዑመርና የሙዐውያም ከዚህ የተለየ አይደለም። ከቻልክ ልክ ዑመርና ሙዐውያ ፊት እንደገሰፁት አይነት ሰዎች አንተም የሳውዲ ንጉስ ጋር ሄደህ ፊት ለፊቱ ምከረው ፣ አንገትህንም እቆርጥሀለው በለዉ ኢስላም ይሄን አይደለም የከለከለው! ኢስላም የከለከለው በጀርባ እየሄዱ ማመፅና ማሳመፅን ነዉ ። የሚገርመው ሙዐዊያን የረሱል ሰሀባን የሚየብጠለጥሉ ሰዎችን አትንኩዋቸው እያሉ ሙስሊሞችን ሲተቹ የነበሩ ሰዎች ለራሳቸው ጉዳይ ሙዐውያን እንደ ማስረጃ ለማቅረብ መሞከራቸው ነው ። እኔ የሚደንቀኝ እነ እከሌ የሰውዎችን ጥሩ ጎን ትተው ነውሩን ብቻ እየለቀሙ ይሳደባሉ እያላችሁ በሸሪዐ በሙስሊሞች ላይ ግዴታ የተደረገውን ተህዚርን ማለትም ማህበረሰቡን ወንጀል ሽርክና ቢድዐን ከሚያስፋፉ ሰዎች እንዲጠነቀቅ ማስታወስን ሀሜት ነው የምትሉት ነገርና ፣ እናተ ደግሞ በኢስላም በጥብቅ የተከለከለውን የመሪዎችን ስህተትና ነውርን እያወጠቹ ሙስሊሙን ለማደናገር መሞከርን ለሀቅ መታገል እንደሆነ አድርጋቹ የምታወሩት ነገር ነው!።
አንድ እዚህ ጋር አስምረህ ልታዳምጥ የሚገባው ጉዳይ ዛሬ ላይ ‘‘ በሙስሊሞች ላይ ስልጣን የያዙትና እየጨቆኑ ያሉት የስዑድ ቤተሰቦች..’ ’ ብለክ ወደ ዘር መረጣ ብትገባም ይህ እጅጉን የተኮነነ ነገር መሆኑን ነው ።
ኢብራድ ኢብን ሳሪያህ ረዲየላሁ ዐንሁ እንደዘገበው ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም አንድ ቀን እንባን የሚያስነባ ከባድ ተግሳፅ የተቀላቀለበት ኹጥባን አደረጉልን በውስጡም አንድ ሰሃባ እንዲ ሲል የጠየቀበት
‹‹አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ይሄ የመለያያ ምክር ይመስላል..››
ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ
‹‹ እኔ እገስፃቿለው አላህን እንድትፈሩና መሪዎቻቹን እንድትታዘዙ ፤ ምንም እንኳን መሪያቹ ሃበሻ (ኢትዮጵያዊም) ቢሆን እንኳን (ታዘዙ) ከናንተ መካከል ረጅም ዕድሜን የኖረ ብዙ መለያየቶችን ያያል..››
ሰዎች መጥፎ ጎናቸው ብቻ ሳይሆን ጥሩ ጎናቸውም ሊታይላቸው ይገባል እያላቹ ትዘምሩ የለ? ታዲያ ምንነው የሳውዲ መሪዎች ጥሩ ጎናቸው፣ በጎ ስራቸው አልታይ አላችሁ? ስለማይታይ ነው ወይስ እናተ ማየት ስለማትፈልጉ? ልብ ያለው ልብ ይበል!! ደሞ የሳውዲ መንግስት ከአይሁድ ጋር ተባብሮ ምናምን የምትለው ምን ማስረጃ አለህ? ፖለቲከኞች ፣ የሀሰት ሚዲያዎች የሚሰብኩህን እያመጣህ ለምንስ ሙስሊሞችን ትረብሻለህ? አላህ አረጋግጡ ብሎ የለ? ታዲያ ምነው ወንድሜ? ሙስሊሙ ባጠቃላይ ቅድሚያ ለተውሂድ የሚሉ ወንድሞና እህቶች ጥፉታቸው ምን እንደሆነ ፣ ቲቪ አፍሪካንም ሆነ ሰዎችን መቼና ምን ብለው እንደሰደቡ ፣ ጥፋት ቢገኝባቸው እንኳን ጥፉታቸው በሸሪዐ ምን ደረጃ ድረስ እደሆነ ፣ በትክክለኛ ኢስላማዊ ማስረጃ ላይ የተመረኮዘ ማረጋገጫ አቅርቡልን ብሎ በተደጋጋሚ ጊዜ ቢጠይቃችሁም እስከዛሬ ተጨባጭ የሆነ ማስረጃ ልታቀርቡለት አልቻላችሁም!! አሁንም ያለ ማስረጀ ሰው ላይ እየቀጠፉቹ ወንጀል እየተሸከማችሁ ትገኛላችሁ!! ከሀዲዎች ሙስሊሙን ያለ ማስረጃ እየከሰሱ ነው እንደሚባለው ሁሉ እናተም ወንድሞቻችሁን ያለ ማስረጃ እየከሳችሁ ነው። አሁንም ማስረጃ እንድታቀርቡልን በትህትና እንጠይቃለን ። እስከዛሬ አንድም ማስረጃ ሳይቀርብባቸው ይሄን ያክል መውቀሱስ ለምንስ ተፈለገ? ጥፉት ቢኖራቸው እንኳን ከኢስላም የሚስወጣ ነው? አላህና መልክተኞቹ ላይ ፣ ሰሀባዎችም ላይ ጭምር ለሚያላግጡ ሰዎች ጥሩ ጎንም ሊታይላቸው ይገባል እያላቹ ታወራላችሁ ፣ ታዲያ ምን ነው ተውሂድን የሚያስተምሩ የወንድምና የእህቶቻቹ ጥሩ ጎናቸው አልታይ አላተችሁ ? የሳውዲ መንግስት ዘፉኝ ምናምን የምትለው እውነት ቢሆንም እንኳን በራስህ አቋም መሰረት ልታነሳሳበት አይገባም ነበር ። ምክንያቱም ረሱል መሪዎች ወንጀል ከሰሩ ነው አታምፁባቸው ያሉት። የሀዲሱ መልእክት ይሄ ነው ፣ ሀዲሱንም እቀበላለሁ ፣ መሪዎች ወንጀል ቢሰሩ አላምፅም ፣ አላሳምፅባቸም እያልክ ነው ። አላስተዋልከው ይሆናል እንጂ መልሰህ ደግሞ የሳውዲ ንጉሰ ዘፉኝ ምናምን እያልክ በግል በሰራው ወንጀል ልታነሳሳበት እየሞከርክ ነው ። ስለዚህ በመሪዎች ዙሪያ ሀዲሱ የከለከላቸውን ሁሉ አትቀበልም እንበል ማለት ነው? ሀሰትን የሙጥኝ ያለ ሰው የፈለገውን ያህል ጥንቃቄ ቢየደርግ ፣ የፈለገውን ያህል እውቀትና ብልጠት ቢኖረውና ቢጠቀም አላህ እራሱ ያደናግርበታል ዛሬ ሌላ ነገ ደግሞ የዛን ተቃራኒ እንዲያወራ ያደርገዋል ። ተንኮሉን ፣ ባጡሉን በውስጡ ደብቆ እውነተኛ መስሎ ለመታየት ቢሞክርም አላህ ያጋልጠዋል! አላህ ይጠብቀን። ረሱል መሪ ላይ አታምፁ ብለዋልና እንታገስ ማለት መሪው የሚያጠፉውን እንወድለታለን ማለት እንዳልሆነ እንዲታወቅልኝ እፈልጋለሁ መሪው ወንጀል ካለበት ወንጀሉን እንጠላለን! ከቻልን በአካል ካልሆነ በደብዳቤ እንመክራለን ካልሆነም ዱዐ እናደርጋለን አናምፅም አናሳምፅም! ያልተስማማንበትን ነገር ወደ አላህና ወደ መልክተኛው እንመልስና ችግራችንን እንፍታ ተቀራርበን በእውቀት በማስረጃ እንወያይ። አላህ በመካከላችን ጥላቻን እንዲያነሳልን ፣ መዋድን እንዲሰጠን ሁላችንንም ይቅር እንዲለንና በቀጥተኛው መንገድ ላይ እንዲገለን እማፀነዋለሁ።

Post a Comment

0 Comments