Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ውዷ ሙስሊም እሕቴ!


እኔንጃ ምን ልልሽ እንደምችል አላውቅም ….
ውዷ ሙስሊም እሕቴ! አንቺ ላይ ሳየውማ ውስጤ ይብከነከናል ።

ገና በዱኒያ ላይ እያለን የአላህን ቅጣት ‘‘ላኢላሃ ኢለላህ’’ ያስተሳሰራቹ እሕታቹ ላይ ስታዩት ምን ይሰማቿል ?

የት እንዳነበብኩት የማላስታውሰው ነገር ግን አዕምሮዬ ላይ ታትሞ የቀረ ከታማኝ መረጃ ላይ እንዳገኘሁት ግን የማስታውሰው የሸኽ ኢብኑ ባዝን (ረሒመሁላህ) ንግግር ትዝ ባለኝ ቁጥር ውስጤ በፍርሃት ይርዳል ።
ቃል በቃል ባይሆንም የሸኹን ንግግር ጥሬ ሃሳቡን ላስቀምጥላቹ
‘‘አዎን ሴት ልጅን አላህ ሲቆጣባት ሰውነቷን አውራዋን ይገልጥባታል ። እናታችን ሐዋ እና አደም አለይሂሙ ሰላም አላህ የተቆጣባቸው ጊዜ ቅድሚያ የቀጣቸው የሰውነታቸውን አውራ ሽፋን በማንሳት ነው። ’’
የሸኹ ንግግር እዚህ ጋር አበቃ
_______________
(ሸይጧን) በማታለልም አዋረዳቸው፤ ከዛፊቱም በቀመሱ ጊዜ እፍረተ ገላቸው ለሁለቱም ተገለጠችላቸው፤ ከገነት ቅጠልም በላያቸው ላይ ይደርቱ ጀመር ፤ ጌታቸውም ከዚቻችሁ ዛፍ አልከለከልኋችሁምን? ሰይጣንም ለናንተ ግልጽ ጠላት ነው አላልኩዋችሁምን? ሲል ጠራቸው።
________________ አል አዕራፍ
የ አላህ ቅጣት ወላሂ ከባድ ነው! ። ይሄን ስፅፍ ውስጤም ተረብሿል! ግን እሕቴ ለአላህ ብለሽ ምክሬን ተቀበዪኝ ። የአላህ ቅጣት ከባድ ነው ። ከአላህ ተጣልተሽ ወዴት ይሸሻል ? ዛሬ ሱሪ ፣ ስኪኒ ፣ እግር የሚያሳይ ቀሚስ ፣ የሰውነትሽን ቅርፅ አጉልቶ የሚያሳይ ጉርድ ፣ ደረትሽን ግልፅ የሚያደርግ ቦዲ ፣ በምላጭና በክር የነቀልሽው ቅንድብ ፣ የተቀባሽው የከለር ቻፕስቲክ ፣ የለበሽው ስስ ሒጃብ ፣ የተጫመትሽው አረማመድሽን እንዲያጎላ የተሰራ ሒል (ባለታኮ) ጫማ ፣ ከሒጃብሽና ከጅልባብሽ ሰርቀሽ ያወጣሻት ፀጉር ፣ ፌሩ ፣ ፓውደሩ ፣ ሽቶው…. ብትዋቢባቸው ሰው አደነቀሽ አላህ ግን ተቆጣብሽ ። እስኪ ንገሪኝ የቱ ይብሳል የፍጡር አድናቅዎት ቢቀር ወይንስ የየፈጣሪ ቁጣ ቢቀር ? የማይወዳደሩ ናቸው!! ። አላህን አመስግኚው ቢላሂ አላህን አመስግኚው ። አሁንም በሕይወት አለሽ ። አሁንም መቶበት ትችያለሽ ። ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ‘‘ጀሃነም አብዝተው የሚማገዱት ሴቶች ናቸው’’ ብለዋል ። አንዷ አንቺ ላለመሆንሽ ዋስትናሽ ምንድን ነው? አሁኑኑ ቶብቺ አላህን ለስከዛሬውም ወንጀል ስርየትን ለምኚው ።
ከላይ ከፃፍኩልሽ የአላህ ቃል ቀጥሎ አደምና ሃዋ አላህን ምን ብለው ለመኑት ?
(( ጌታችን ሆይ፦ ነፍሶቻችንን በደልን፤ ለኛ ባትምር ባታዝንልም በእርግጥ ከከሳሪዎቹ እንሆናለን አሉ።))
እስኪ ልክ እንደ እናትሽ ሐዋ አንቺም ይህን ቃል ከልብሽ ደጋግሚው.. ደጋግሚው አላህ መሃሪ ነው ። ደግመሽ ወደነበርሽበት እንደማትመለሺ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ ድረሺ ።
አላህ ጌታችን አላህ ወረድ ብሎ እንዲህ ይላል
{{ የአዳም ልጆች ሆይ፦ ኀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ ጌጥንም በእርግጥ በናንተ ላይ አወረድን፤ አላህን የመፍራትም ልብስ፣ ይህ የተሻለ ነው፤ይህ ከአላህ ታምራቶች ነው፤ ይገሠጹ ዘንድ (አወረደላቸው)። }}

ቀጠለና …
{{የአዳም ልጆች ሆይ፦ #ሰይጣን_አባትና_እናታችሁን_ዕፍረተ_ገላቸውን_ሊያሳያቸው ልብሶቻቸውን ከነሱ #የገፈፋቸው ሲሆን ከገነት እንዳወጣቸው ሁሉ #እናንተን_አይሞክራችሁ፤ እነሆ እርሱ ከነሰራዊቱ ከማታዩዋቸው ስፍራ ያዩዋችኋልና፤ እኛ ሰይጣናትን ለነዚያ ለማያምኑት ወዳጆች አድርገናል}}

ዛሬ የለውጥ ቀን ነው የአላህን ቁጣ ከመሸመት ወደ የአላህን ውዴታ ማግኘት የምንሸጋገርበት ቀን ይሁን ። ቃል ግቢ ፣ ከገባሽም በቃልሽ ፅኚ! ። አላህ ከፈቀደልን ጀነት እንገናኝ ይሆናል ። ኢንሻ አላህ

ለኔም ዱዐ አድርጊልኝ ።
የኢስላም ወንድምሽ አቡ ዓኢሻ
••••••
@sisters only page ሙስሊም እሕቶች ብቻ ፔጅ
ከታች ያለውን ሊንክ ተጭነው ላይክ ማድረግ ይችላሉ
https://m.facebook.com/profile.php?id=503368746467445&ref=bookmark