Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰማሃቱ ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ) እንዲህ አሉ :

ሰማሃቱ ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ኢብኑ ባዝ (ረሒመሁላህ) እንዲህ አሉ :-
‹‹ አቂዳ ከምንመገበው ምግብ ፣ መጠጥ ፣ ጤና ፣ እንደውም ከምንተነፍሰው አየርም በላይ ለኛ እጅጉን አስፈላጊ ነው ። ምክንያቱም እነዚህን ነገራቶች አጥተን የከፋ የተባለ ነገር ቢደርስብን ሕይወታችንን ብናጣ ነው ። ይህን ዓለም ለቀን ወደ የሚቀጥለው እንሸጋገራለን ። ነገር ግን አቂዳችን የተበላሸ ከሆነ ይሄን ዓለም (ዱኒያ) ብቻ አይደለም የምናጣው ነገር ግን አኺራችንንም ነው ። እጅግ የከፋ ትልቅ ኪሳራ ነው ››
[( "القوادح في العقيدة ووسائل السلامة منه " ) ከሚለው ደርሳቸው የተወሰደ]
_________
የሱና ኡለማዎቻችን ሙስሊም የሆኑ መሪዎችን ስለማያከፍሩ ይሰደባሉ !!?
ሱብሃነላህ ወላሂ ቢላሂ ልንገርህ አንተ ሰው !!
እናትህ ከምታስብልህ ከምታዝንልህ ከምትራራልህ በላይ የሱና ኡለማዎች ላንተ ያስቡልካል!! ቀንና ሌት ጭንቀታቸው ምኞታቸው ጥበታቸው አንተ ተውሒድህን ጨብጠህ አቂዳን አውቀህ ተንቀልቃይ ከሆነችው የጀሃነም እሳት እንድትጠበቅ ነው!!
ግን አንተ መች ገባህ?
ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዳሉት ወደ እሳት የሚጣሩ ዱዐቶችን ጆሮህን ልብህን አቅልህን ሰጥተህ የሱና ኡለማዎች ግን ያንተን የፖለቲካ ድንፋታ ስለማያወሩልህ ትሰድባቸዋለህ??

ያ አላህ!
አንተው ሁነን አንተው አስተካክለን

Post a Comment

0 Comments