Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፍሬሹም ሲኒየሩም ሙስሊም ተማሪ ሆይ ንቃ !!

ፍሬሹም ሲኒየሩም ሙስሊም ተማሪ ሆይ ንቃ !!

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች
የካምፓስ ተማሪ ከፊት በር ገብቶ ትምሕርቱን አጠናቆ ከኋላ በር ሲወጣ የተማረበትን ፊልድ ዲግሪ ብቻ አይደለም ይዞ መውጣት ያለበት ነገር ግን በዒልም ዳብሮ በተውሂድ ታንፆ በሱና ፈክቶ ሴቷም ሸሪዓዊ የሴት ልጅ ህግጛቶችና ደንቦችን ተምራ አልፎ ተርፎ ከወደፊት ትዳሯ አንስቶ እስከልጅ አስትዳደግ ተርቢያ ጠንቅቃ ተረድታ ወደ ቤቷ መመልስ ይኖርባታል።

____________
ነገር ግን ዛሬ ዛሬ ይሄን የተማሪ ራዕይ ከወዲው የሚቀጩ ፤ በስኳር ብዕራቸው ውስጥ እሾህን ያዘሉ ያን ንፁህ የረሱልን እና የሰለፎችን እስልምና ዳር አስይዘው በራሳቸው ፍልስፍና የታጀቡ መፅሃፍት የተከበረው የአላህ ቤት መደርደሪያዎች ላይ ተደርድረው ተማሪ አንብቦ እንዲጠም እየተደረገ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው።
_____

ከታች ምስላቸው የሚታዩት ሰይድ ቁጥብ እና አቡል አዕላ አል መውዱዲ መፅሃፍት ለአብነት ያክል ተጠቃሽ ነው ፤ እነዚህ መፅሃፍት በጀማዓቱል ኢኽ ዋኑል ሙስሊሚን ማሕበራት በተለያዩ ሚሽነሪዎቻቸው አማኻኝነት በእንግሊዘኛ ተተርጉመው በየዩኒቨርሲቲው የሙስሊም ተማሪ ጀምዓ እጅ እንዲገቡ ተደርጓል እየተደረገም ነው ፤ በመዲናችን አዲስ አበባም እንዲሁ እነዚህን መፃህፍት ወደ አማርኛ በመተርጎም ስራ ላይ ተጠምደው እናገኛቸዋለን !!
_________
ንቃ !!!
‹‹ በፍየል ዘመን በግ መሆን አያዋጣም ›› !!!