Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

((ሙዛኽራ)) በሙስሊም መሪ ላይ ማመፅ

((ሙዛኽራ)) በሙስሊም መሪ ላይ ማመፅ
☞ ይህንን ርዕስ ለማንሣት ያነሣሣኝ ነገር ከአንዳንድ ወንድሞች በሙስሊም አመራር ላይ ማመፅ እንደሚቻል የሚያትቱ ፅሁፎች መበራከታቸው ነው
ወደ ርዕሡ ስገባ
☞ የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም የሙስሊም አመራሮችን መታዘዝ እንዳለብን በርካታ መልዕክትችን በሠሀቦቻቸው አማካኝነት አድርሠውናል

☞ ሠዎች በመሪዎቻቸው ደላቸውም ፣ ተቸገሩም ፣ ተደሠቱም ፣ አዘኑም፣ ቢመቷቸውም ፣ ገንዘባቸውን ቢወስዱም አላህን እስካላሳመፁዋቸው ድረስ አልሠማም ((አልታዘዝም)) ማለት እንደሌለባቸው የአላህ መልእክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም እንዲህ ሢሉ በግልፅ ቋንቋ ነግረውናል
★ የአላህ መልእክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም « ሲደላህም፣ ሲቸገርህም በነሸጥክበትም ፣ በደበረህም ወቅት፣ ገንዘብህንም ቢበሉ ፣ ጀርባህንም ቢመቱህ ወንጀል እስካል ሆነ ድረስ ስማቸው ታዘዛቸው» ይላሉ
☞ በተጨማሪም ምንም ያክል በደለኛ ቢሆኑም በእነሡ እጅን ማንሣት እንደሌለብን በድጋሚ እንዲህ ሢሉ ይነግሩናል
« ምርጥ መሪዎቻቹ የምትወዷቸው እና የሚወዷቹ ፣ የሚለምኑላችሁ እና አላህን የምትለምኑላቸው ናቸው፣ መጥፎ መሪዎቻቹ ደግሞ የምትጠሏቸው የሚጠሏቹ ፣ የምትረግሟቸው የሚረግሟቹ ናቸው» ሢሉ ሡሀቦች በሠይፍ እንጋደላቸው እንዴ ብለው ሢጠይቁ « ሠላትን እስካቋቋሙ ድረስ አትጋደሏቸው ከመሪዎቻቹ የምትጠሉትን ነገር ባያቹ ግዜ ስራውን ብቻ ጥሉ ከሡ ትዕዛዝ ውጪ እንዳትሆኑ» ሢሉ አዘውናል
☞ የሙስሊም አመራሮች ላይ ማመፅ ቅጣቱ እጅጉኑ የገዘፈ ነው ።
★ ከሙስሊም መሪዎች ትእዛዝ ውጪ ሆኖ እና ጀመአውን ተለይቶ የሞተ ሠው የጃሒልያ አሟሟት እንደሞተ ነው
☞ የቀደምት ሠለፎች ከመሪዎቻቸው ጋር የነበራቸው ስነ ምግባር ይህን ይመስል ነበር
★ ኢማሙ ሣቡንይ አላህ ይዘንላቸው እና ይላሉ « ሡሀቦች ለኡመራእ ዱአ ማድረግን እንደ ጥሩ መገጠም አድርገው ይቆጥሩ ነበር»
★ ኢማሙ በር በሀሪይ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል « አንድ ሠው በሙስሊም መሪ ላይ ዱአ ሢያደርግበት ካየህ እሡ የስሜቱ ተከታይ መሆኑ እወቅ በአንፃሩ ለመሪ ዱአ ሢያደርግለት ያየህው ሠው የሡና ባልተቤት ነው»
★ ፋደይል ኢብኑ ኢያድ አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል « ለኔ አንድ ተቀባይነት ያላት ዱአ ብትኖረኝ ለመሪ አደርገው ነበር
ጥሩ ነገር እንዲያገኙ እንድንለምንላቸው ታዘናል ድንበር ቢያልፉም ቢበድሉንም በነሡ ላይ እንድንለምንባቸው አልታዘዝንም መበደላቸው እና ድንበር ማለፋቸው ለነፍሣቸው እና ለሙስሊሞች ነው መስተካከላቸውም እንደዛው»

★ አነስ ኢብኑ ማሊክ አላህ ስራውን ይውደድለት እና እንዲህ ይላል « ታላላቅ ሡሀቦች ኡመራኦቻችንን ከመስደብ ፣ ከማታለል ፣ ከመጥላት ከለከሉን አላህን ፍሩ ታገሡ ነገሩ ቅርብ ነው»
አላህ አለም ላይ ያሉ የሙስሊም መሪዎቻችን መልካም ሠው ያድርግልን እድሜያቸውንም ያርዝምልን የሡና እና የተውሒድን ባንዲራ ከፍ አድርገው የሚያውለበልቡ ያድርግልን አሚን

Post a Comment

0 Comments