Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የዓመቱ ትርፍ እና ከሳራ

አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ"አሏህ እንደሚያየን እንወቅ ነስፊያችንንም እንተሳሰብ"ዓመት አልፎ ሌላ ሲተካ አስተዋይ ሰው ብዙ ነገሮችን ይታዘባል:: እዚህ ጋር ቆም ብሎ ማስተንተንና ባለፉት ጊዜያት ምን ሰራሁ? ማለት፣አሏህን ሁሌም ለመታዘዝ ቃል መግባት፣ ከዚህ በፊት     ላጠፋናቸው ጥፋቶችም ምህረትን መጠየቅና ለቀጣይም ጌታችንን የሚያስደስት አዲስ እቅድ ማውጣት ይጠበቅብናል 
ዱንያ፥ ውስን ቀናት ነች የምንኖረውም አጭር ጊዜ ነው የምንሰራው  ስራ በሙሉም አሏህ ዘንድ እንጠየቅበታለን አሏህም የሚከተለውን ብሏል[يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَلْتَنْظُرْ نَفْسٌ مَا قَدَّمَتْ لِغَدٍ وَاتَّقُوا اللَّهَ إِنَّا للَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ](እናንተ ምእምናን ሆይ፥ አሏህን ፍሩ እያንዳንዷ  ነፍስም ለነገ ህይወቷ  ምን እንዳዘጋጀች እራሷን ትጠይቅ:: አሏህን ፍሩ እርሱ የምትሰሩትን በሙሉ ጠንቅቆ ያውቃል) ሱረቱል ሐሽር 18ለዚህም ነው የአሏህ መልእክተኛ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ሁሌም እራሳችንን  እንድንገመግም የመከሩንاتق الله حيثما كنت وأتبع السيئة الحسنة تمحها وخالق الناس بخلق حسن) رواه الترمذي)"የትም ብትሆን አሏህን ፍራ! ወንጀል ላይም ከወደቅክ -ቶሎ  ብለህ በመታቀብ- መልካምን ነገር አስከትለህ ስራ ከሰዎችም ጋር በመልካም ስነምግባር ተኗኗር " ኢማም አቲርሚዚይ ዘግበውታል 
በዚህ ረገድ ከሰሓባዎች አሏህ መልካም ስራቸን ይውደድላቸውና እጅግ በጣም መካሪ የሆኑ ክስተቶች ተዘግበዋል ለምሳሌም፥ አቡበክር አሲዲቅ እጅግ በጣም አሏህን እና ቅጣቱን ከመፍራታቸው የመጣ የሚከተለውን ይሉ ነበር"ምነው እኔእንስሳትየሚመገቡት ዛፍ ወይም ቅጠል በሆንኩኝ!እያሉ እራሳቸውን ይገመግሙና ነፍሲያቸውን ያስፈራሩ እንደነበር ሲጠቀስ፥ ዑመር ኢብኑል ኸጧብ ደግሞ የሚከተለውን ይሉ ነበር { አሏህ  ፊት ከመተሳሰባችሁ በፊት እራሳችሁን ተሳሰቡ እርሱ ፊት ከመመዘናችሁም በፊት እራሳችሁን መዝኑ ለትልቁ ጉባኤም ተዘጋጁ}ሐሰን አል-በስሪይም የሚከተለውን ይሉ ነበር { አንተ የሰው ልጅ ሆይ፥ አንተ  ማለት እኮ የእለታት ድምር -ወይም ስብስብ- ነህ ቀን ባለፈ ቁጥር እራስህን - ከፊልህን -ታጣልህ }
እነሆ ዓመት በሄድ ቁጥር የሰራናቸውን መልካምም ይሁን መጥፎ ስራዎችን ይዞ ይሄዳል ጌታችን ዘንድም ለእኛ ወይም እኛ ላይ ይመሰክራል!አሏህ እድሜና ጤና እስከሰጠን ድረስ ለአኼራህ የሚሆነን ስንቅ እንሰንቅ እርሱ ፊት ለመንጠየቃቸው ጥያቄዎም ትክክለኛ  መልስ እናዘጋጅ የመልካም ስራ አጋጣሚዎችን ፈጥነንእንጠቀማቸው ሞት በድንገት ሳይመጣና ምንው ትንሽ ጊዜ በተሰጠኝ ብለን የማይቻልን ነገር ከመመኝታችን በፊት( وَاتَّقُوا يَوْمًا تُرْجَعُونَ فِيهِ إِلَى اللَّهِ ثُمَّ تُوَفَّى كُلُّ نَفْسٍ مَا كَسَبَتْ وَهُمْ لَا يُظْلَمُونَ ){ ወደ አሏህ የምትመለሱበትና ከዛም እያንዳንዷ ነፍስ የሰራዋን ዋጋ የምታገኝበትን ቀን ፍሩ በእለቱም ማንም የሰራውን ስራ በመካድ ወይም ያልሰራውን ሰርተሃል በመባል አይበደልም } ሱረቱል በቀረህ 281:::::::::: ጌታይ ሆይ፥ ምንም ወንጀሌ ቢበዛ፣ ምህረትህ ከዛ የላቀ  እንደሆነ  አውቃለሁ:::::::::: የአንተን ምህረት ተስፋ የሚያደርጉት ደጋጎች ብቻ ከሆነ፣ ለሀጢያተኞችስ ማን ኣላቸው?!:::::::::: ባዘዝከው መሰረት ተናንሼ እለምንሃለሁ፣ አሳፍረህ ከመለስከኝ ካንተ ይልቅ መሃሪና እሩህሩሁ ማን ይሁን?!:::::::::: ከምህረትህና ይቅር ባይነትህ ውጪ አንተ ዘንድ ምንም የለኝም፣ እንደው ሙስሊም መሆኔ እንጂ!


/// አሕመድ ኣደም///