Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

whats'app እና facebook በምንፃፃፍበት ጊዜ ልብ መባል ያለባቸው ነገሮች

የእለተ እሁድ ዙልቀዕዳ 12 -1435
( whats'app እና facebook በምንፃፃፍበት ጊዜ ልብ መባል ያለባቸው ነገሮች)
፩= ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም
صلى الله عليه وسلم

የነብዩ መሐመድ ሥም በሚነሣበት ጊዜ ሠለዋት ማውረድ ግዴታ ነው፡፡
ነቢይ ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም ሥሥታም ሠው ማለት የእኔ ሥም ተነሥቶ ሠለዋት የማያወርድ ነው ብለዋል፡፡

እንደዚሁ አላህ ሡብሀነ ወተአላ ቁርአን ላይ አላህ እና መልእክተኛው ነቢዩ ላ ሠለዋት ያወርዳሉ፡፡
እናንተ ያመናችሁ ሆይ ነብዪ ላይ ሠለዋት አዉርዱ በማለት አላህ ሡብሀነ ወተአላ አዟል፡፡

አላህ ሠለዋት ያወርዳል ማለት ያወድሣቸዋል ከፍ ያደርጋቸዋል ማለት ነው፡፡
= ሠዎች ደግሞ ነብዩ ላይ ሠለዋት ማዉረድ ማለት ለነብዩ ዱዓ ማድረግ ማለት ነው፡፡
የነብዩን ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም ሥም በምናነሣበት ጊዜ በፅሁፍም ይሁን በቃል ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም መባል አለበት፡፡

ሰሓቦች ነቢዩን እርሶ ላይ እንዴት ነው ሰለዋት የምናወርደው ብለው ጠየቋቸው ?
ነብያችን ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም
( አሏሁመ ሰሊ ዐለ ሙሐመድ ወዐለ ኣሊሙሐ.... በሉ ) ብለዋቸዋል፡፡

በዚህ የነቢዩ ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም ሐዲስ መሠረት ሠለዋት የሚባለው ወይም ደግሞ በትክክል አንድ ሠው ሠለዋት አውርዷል ማለት የሚቻለው ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም ሢል ነው ወየመ (አሏሁመ ሰሊ ወሠሊም ዐለይሂ ) ወዘተ ሲል ነው፡፡
በተረፈ ከዚህ ውጭ በአማርኛ (ሠ,አ,ወ) ተብሎ አጫጭር ፊደሎችን መፃፍ ተገቢ አይደለም፡፡
ሠለዋት ዐለ ነቢይ ሙሉ በሙሉ መፃፍ አለበት፡፡

፪ ሡብሐነሁ ወተአላ
سبحانه وتعالى
የሚለውንም በተመለከተ ከተፃፈ ሙሉ በሙሉ መፃፍ አለበት እንጂ (ሰ,ወ,አ) ተብሎ አይፃፍም፡፡
፫ ረዲየሏሁ ዐንሁ የሠሀቦች ስም በሚነሣበት ጊዜ አህለ ሱና ወል ጀመአ ሁሉም ሰሓቦች ሥም ሲነሣ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) ይባላል ዐሊይ ኢብን አቢ ጣሊብም ጭምር ማለት ነው፡፡

አንዳንዶች ዐሊይ ሲባል ከረመሏሁ ወጀሀሁ ይላሉ ይህ ቢድዓ ነው፡፡
ለዐሊይ ብቻ ተለይቶ አይባልም፡፡ ከተባለ ለሁሉም ሠሀቦች ከረመሏሁ ወጀሀሁ ከተባለ ምንም አይደለም፡፡
የትኛውም ሠሀቢይ ሥም ከተነሳ ረደሏሁ አንሁ ይባላል፡፡
ሴት ከሆነች ረዲየሏሁ ዐንሃ ይባላል፡፡
አባትም ልጅም ሙስሊም ከሆኑ ደግሞ ረዲሏሁ ዐንሁማ ይባላል፡፡
= ምሳሌ አዒሻ ረዲሏሁ ዐንሁማ ይባላል፡፡አባቷም ሙስሊም ስለሆነ ማለት ነው፡፡
= እሱ ብቻ ሙስሊም የሆነ ከሆነ ግን አባቱ ካልሠለመ ረዲሏሁ ዐንሁ ይባላል፡፡
በዚህ አንዳንድ ሠዎች ይሳሳታሉ አባቶቻቸው ሙስሊም ያልሆኑ ሠሓባዎችን ረዲሏሁ ዐንሁማ ይላሉ ይህ ትልቅ ስህተት ነው፡፡
ለምሳሌ፦ (አቡ ሁረይህ ረዲየሏሁ ዐንሁማ) ይህ ስህተትነው ትክክለኛው ( አቡ ሁረይረህ ረዲየሏሁ ዐንሁ) ነው
ረዲየሏሁ ዐንሁ በሚፃፍበት ጊዜ ሙሉ በሙሉ መፃፍ አለበት፡፡(ረ,አ) ተብሎ መፃፍ የለበትም፡፡

፬ ( አሠላሙ ዐለይኩም )
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ብለን በምንፅፍበት ጊዜም ይህ አይነት ችግር አለ ብዙ ሠዎች (as wr wb ) ብለው ይፅፋሉ፡፡ ሲመልሡም (ws wr wb ) ብለወ ይፅፋሉ
እሰላማዊ ሰላምታን በዚህመልኩ መፃፍ ተገቢ አይደለም፡፡

ከተቻለ አሠላም ዐለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ብለን ሙሉውን ሰላምታ እንፃፍ ካልቻልን ግን አሰላም ዐለይኩም ብቻ ብለን እንፃፍ
ለመጀመሪያው መልስ፥
(ወዐለይኩም አሠላም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ)
ለሁለተኛው ደግሞ (ወዐለይኩም አሠላም) ብሎ መመለሥ ዋጂብ ነው፡፡
አሏሀ በተከበረውቃሉ የሚከተለውን ብሏል
( ሠላምታ ከቀረበላቸሁ የቀረበላችሁን አይነት ሠላምታ መልሡ ወይም የተሻለ መልስ መልሱ )
አንዳንድ ሰዎች ወመግፊረቱሁ ወሪድዋኑሁ የሚሉት ነገር ተገቢ አይደለም፡፡ከረሱል ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም አልተገኘም፡፡
አሠላም ዐለይኩም ብሎ ለፃፈ ሠው ወዐለይኩም አሠላም ብለን እንመልሣለን እንጂ w w w ወይም ደ ws wr wb ተብሎ አይመለስም፡፡
= እነዚህ አራት ነጥቦች ኸይር ሥራ ናቸው፡፡ የሙስሊም መለያ እና መታወቂያ ናቸው፡፡
ሙስሊም ሠው ሲገናኙ አሠላም ዐለይከም የአላህ ስም ሲነሳ ሱብሓነሁ ወተዓላ
( ዐዘ ወጀል) ይባላል፡፡
የነብዩ ስም ሲነሳ ዐለይሂ ሥሠላቱ ወሠላም (ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም) ይባላል፡፡
የሠሓቦች ስም ሲነሳ ረዲየሏሁ ዐንሁ (ዐንሁም) አላህ ስራቸውን ይዉደድላቸዉ ይባላል፡፡

እነዚህ ሁሉ ኢባዳ ከመሆናቸው አንፃር ድካምና ጊዜ ይጠይቃሉ ጊዜያችንን መሥዋዕት አድርገን ልንፅፍ እና መልስ ልንሠጥ ይገባል፡፡
ቸኩዬ ነው እንዲህ ሆኜ ነው ወዘተ የሚሉት በቂ ምክንያት አይደለም፡፡
ኢባዳ እሥከሆነ ድረስ ልንደክምበት ይገባዋል፡፡
= ሌላው ከዚህ የተለየ በ whats.appና facebook በሌሎችም ሠዎች በሚፃፃፉበት ጊዜ የሚፈፀሙት ስህተት አለ፡፡
አሱም ፧
ቁርአንን ከዐረብኛ ውጭ በሆነ ፊደል መፃፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ ኡለማዎች ሐራም ነው ብለዋል፡፡
ቁርአንን በማንኛውም ከዐረብኛ ዉጭ ባሉ ቋንቋዎች መፃፍ አይቻልም፡፡ ትርጉሙን መፃፍ ይቻላል፡፡
እንጂ ቃሉን በአማርኛ መፃፍ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
ትርጉሙን ከሆነ ግን መፃፍ ይቻላል፡፡

አላህ ጠቃሚ እዉቀት ከመልካም ስራ ጋር
ይወፍቀን፡፡ አሚን

ወሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱሏህ
## አሕመድ ኣደም ##
ቅንብር= ቢንቱ ሙሐመድ