Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የኡለሞች መሞት

የኡለሞች መሞት

አብደአላህ ኢብን አምር ኢብን አል-ዓስ የአላህ መልእክተኛን( ﷺ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ ይላል፡

<<አላህ ዕውቀትን በማስወገድ መልኩ ከባሪያዎቹ(ልብ ውስጥ) የሚያስወግድ ሆኖ አያነሳም ነገር ግን (አላህ) እውቀትን የሚያነሳው የዕውቀት ባልተቤቶችን በማንሳት (በማሞት) ነው።ምንም የዕውቀት ባለቤት እስከማይከቀር ድረስ፡ሰዎችም አላዋቂዎችን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ፡ጥያቄን ይጠየቃሉ እነርሱም ያለ እውቀት ይመልሳሉ፡ራሳቸውም ይጠማሉ ሌሎችንም ያጠማሉ>> (በኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል)

ሀሰነ አል-በስሪ እንዲህ ሲሉ ይናገራሉ፡
<<አዋቂዎች(ኡለማዎች) ባይኖሩ ኖሮ ሰዎች እንደ እንሰሳ ይሆኑ ነበር>>

ሱፍያን ሰውሪ እንዲህ ይላሉ(አላህ ይዘንላቸውና)፡
<<የአሊም ምሳሌው ልክ እንደ ሀኪም(ጠቢብ) ነው፡በተመመው ቦታ ቢሆን እንጂ መድሃኒቱን አያስቀምጥም>>(አል-ሂልያህ)

አዩብ (አላህ ይዘንለትና) እንዲህ ይል ነበር፡
<<እኔ የሱና ባለቤት(አህሉ ሱና) በሆነ ሰው ሞት ሲነገረኘ ልክ የሰውነት አካሌን እንዳጣው ነው የሚሰማኝ>> (አል-ላለካይ)

በዛሬው እለት ለሞቱት ታለቁ ሼክ ዘይድ ኢብን ሃዲ አልመድኸሊ አላህ ሱብሀነ ወተዓላ ሰፊ በሆነው እዝነቱ እንዲያዝንላቸውና ፊረደውሰ አል-አዕላን እንዲያጎናፅፋቸው እንለምነዋለን።

Post a Comment

0 Comments