Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዘካ

ዘካ

ዘካት የተወሰኑ መመዘኛዎች ሲሟሉ ለተለያዩ የሕብረተሰቡ አባላት በንብረትነት ከያዙት (ንብረት) የሚከፈል ግዴታ ነው፡፡ ዘካት ከእስላም አበይት መስፈርቶችና ከታላላቅ መዋቅሮቹ አንዱ ሲሆን ቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ብዙ ቦታ ላይ ከሶላት ተጣምሮ ተወስቷል፡፡ በግዴታነቱ ላይ ሙስሊሞች ሙሉ በሙሉ በፍጹምነት የተስማሙበት ሲሆን ግዴታነቱን እያወቀ ያስተባበለ ሰው ከኢስላም ጎራ የወጣ ከሐዲ (ካፊር) ነው፡፡ ዘካትን የከለከለ ወይም ያጥላላውና ያንቋሸሸው ሰው ለአላህ ቅጣትና ቁጣ ከተጋለጡት በደለኞቹ ይቆጠራል፡፡ ለዚህ ማስረጃ የሚከተሉትን እንመልከት፡- አላህ (ሱወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፤ ዘካትንም ስጡ፤…›› ‹‹አላህን፣ ሃይማኖትና ለርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ሆነው ሊግገዙት፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ፣ ዘካትንም ሊሰጡ እንጅ ያልታዘዙ ሲሆኑ (ተለያዩ)፡፡ ይህም የቀጥተኛይቱ (ሃይማኖት) ድንጋጌ ነው፡፡ >> ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ መሰረት ዘካት ከአምስቱ የኢሰላም አበይት አዕማድ አንዱ መሆኑን የአላህ መልክተኛ (ሰዐወ) ማግለጻቸው ተረጋግጧል፡፡ ሙዓዝ ብኑ ጀበል የተባሉትን ባልደረባ ነቢዩ (ሰዐወ) መልክተኛቸው በማድረግ ወደ የመን ስለመላካቸው ታሪክ ቡኻሪ ሲዘግቢ ከሀብታሞቻቸው ተወስዶ ለድሆቻቸው የሚከፈል የተወሰነ ክፍያ አላህ የደነገገባቸው መሆኑን እንዲያስተምሩ ነብዩ ማዘዛቸውን አውስተዋል፡፡ የዘካትን አስፍላጊነት በማስተባበል ክፍያውን የከለከሉ ሰዎች ከሐዲ (ካፊር) መሆናቸዉን ከሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ እንረዳለን፡- ‹‹ቢጸጸቱም፣ሶላትንም ቢሰግዱ፣ ዘካንም ቢሰጡ፣የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው፤‹‹ ከአንቀጹ እደምንረዳው ሶላት የማይሰግድና ዘካት የማይከፍል ሰው የእምነት ወንድማችን ሳይሆን ከከሃዲዎት የሚቆጠር ነው፡፡ ከዚሁ በመነሳት ሶላትንና ዘካን ለያይተው ዘካን የከለከሉ ሰዎችን አቡበከር ተዋግተዋቸዋል፡፡ በዚህ አቋማቸው ላይ ሁሉም ያላንዳች ልዩነት ተስማምተውበታል፡፡ ብዙ ጥበቦችን ያቀፈ፣ታላላቅ ግቦችን ያለመ ከፍተኛ የጋራ ጥቅሞችን ያካተተና ቁርኣንና ሐዲስ ይህ ግዴታ ተፈጻሚ እንዲሆን ያዘዙባቸውን አንቀጾች በማጥናትና በማስተዋል በግልጽ የሚታይ ጥበባዊ ድንጋኔ ነው፡፡ ከነዚህ አንቀጾች መካከል በ‹‹አል-ተውባህ›› ምዕራፍ ውስጥ የሰፈረውንና የዘካት ባለመብቶችን የሚዘረዝረው አንቀጽና ምጽዋት እንዲሰጥና ለበጎ አድራጎት ገንዘብ እንዲለገስ በአጠቃላይ መልኩ የሚያዙና የሚገፋፉ ነቢያዊ ሐዲሶች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ መካከል የሚተሉትን እናገኛለን፡፡ 1.ከኃጢአትና ከክፉ ሥራ የአማኙን መንፈስ ማጥራትና በሕሊና ላይ የሚያስከትሉትነ ተጽእኖዎች ማስወገድ፤ ከንፉግነትና ከቆንቋናነት መጥፎ ባህሪና ከሚያስከትሉት አፍራሽ ውጤቶች አማኝን ማጽዳት፡፡ ሃያሉ አላህ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ከገንዘቦቻቸው ስትሆን በርሷ የምታጠራቸውና የምታፋፋቸው የሆነችነ ምጽዋት ያዝ፤…›› 2. ድሃ ሙስሊምን በመርዳት ችግሮቹን በማቃለል ማገዝና አላህ ብቻ እንጂ የማንን እጅ ተዋራጅ ሆኖ እንዳያይና እንዳይለምን ማስቻሉ፣ 3. ዕዳ ያለበት መስሊም በሰው እዳ ጫና እንዳይጨነቅ ዕዳውን በመሸፈን ከወደቀበት የሰዎች እዳ ነፃ ማውጣቱ፤ 4. እምነት ሥር ያልሰደደባቸውንና የእስላም የእምነት ጽኑ እውነታ ማሸጋገሩ፣ 5. በአላህ መንገድ የሚታገሉ ተጋዳዮችን ለማደራጀት፣ የእስላምን ትምህርት ለማሰራጨት አስፈላጊውን መሰናዶ ለማከናወን፣ ክህደትና መጥፎ ነገሮችን በማስወግድ በሰዎች መካከል ፍትህን አንግሶ ተፈታታኝ ሁኔታዎችን በማጥፋት የአላህ ኃይማኖት እንዲሰፍን ለማድረግ ማስቻሉ፤ 6. ከቤቱ ወጥቶ በእንግድነት ላይ እያለ ወደ ሀገሩ መመለሻ ገንዘብና አስፈላጊ ነገሮች ማገኘት ያልቻለ ሙስሊም መንገደኛ ወደ አገሩ ለማስመለስ ከዘካት የሚበቃውን ያህል የሚሰጠው መሆኑ፤ 7. የአላህ ትዕዛዝ ማክበርና ለፍጡራኑ በተግባር በመፈጸም ቃሉን መስማት የሚያስገኘው በረከት፤ የዘካ ከፋዩን ንብረት ታዳጊ ምርታማ ማድረጉና ከክፋትና ከጥፋት መከላከያና መጠበቂያው መሆኑ፤ እነዚህ ከመጠቁ የዘካት ጥበባትና ከላቁ ክቡር ዓላማዎች፡ በከፊል ለመጥቀስ ብቻ ሲሆን፣ የአላህን ሸሪዓ ምስጢሮችና ጥበቦቹን ሙሉ በሙሉ የሚያካትት ዕውቀት የአላህ ብቻ እንደመሆኑ ዘካት ሌሎች አያሌ ጥበቦችና ምስጢሮችን አቅፎአል፡፡ ዘካት የሚከፈላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች በተመለከተው የቁርኣን አንቀጽ የተዘረዘሩ ናቸው፡- ‹‹ግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት) ለድሆች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሰሩ ሠራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱት፣ ጫንቃዎችንም ነፃ በማውጣት፡ በባለ ዕዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሰሩ፣ ለመንገደኛም ብቻ ነው፣ ከአላህ የተደነገገች ግዴታ ናት፣ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡

Post a Comment

0 Comments