Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሼክ ዘይድ ኢብን ሃዲ አል-መድኸሊይ አጭር የህይወት ታሪክ

የሼክ ዘይድ ኢብን ሃዲ አል-መድኸሊይ አጭር የህይወት ታሪክ

ታላቁ እና የተከበሩት ሼክ ስማቸው እና ተቀፅላ ስማቸው አቡ ሙሀመድ ዘይድ ኢብን ሃዲ ኢብን ሙሀመድ አልመድኸሊይ ነው።ጎሳቸው በሳውዳረቢያ በደቡብ በኩል የሚገኘው ተዋቂው የመዳኪላህ ጎሳ ሰው ናቸው።ሼክ የተወለዱት በ1357 እንደ ሂጂራ(በፈረንጅ በ1938) አቆጣጠር ሩክባህ በሚሰኘው አቅራቢያ መንደር ነው፡

የሼክ አስተዳደግና የእውቀት ፍለጋ ጉዞ

ሼክ ያደጉት እናት እና አባታቸውን በመካደም አነርሱ ዘንድ ነው፡ታዲያ እናታቸው የሞቱት ለአቅመ አዳም ሳይደርሱ እርሳቸው ሰባት አመታቸው ሳሉ ነው፡እናታቸው በጥሩ ምግባርና በሃይማኖታቸው የታወቁ ነበሩ፡እንዲሁ አባታቸው የሞቱ እድሜያቸው ሰላሰ ገደማ በነበሩ ሰዓት ነው፡አባታቸው ከልጅነታቸው ጀምሮ ሼክን በዚህ የዲን እውቀት ፍለጋ ላይ አጥብቆ እንዲይዝ ያነሳሷቸው ነበር ከዛም ሼክ አህመድ ኢብኑ አህመድ አልመድኸሊይ(አላህ ይዘንላቸውና) ዘንድ የከጥ(የፅሁፍ)፡የመፃፍ፡የማንበብ፡የተውሂድ፡የተጅዊድ፡የቁራንን ትምህት ተሰብስበው(በሀለቃ) ከሚማሩት ተማሪዎች ጋር አብረው መማር ጀመሩ።ከዚያም የቁራአን ሂፍዝ በመጀመር ሱረቱል በቀራህ፡አል-ኢምራን እና ሌሎች ተጨማሪ ሱራዎችን በመሀፈዝ፡እድሜያቸው ሰባት አመት አከባቢ እያለ ወደ አቅራቢያቸው ካለው ሩኩባህ አከባቢ ካለ መድረሳ ውስጥ ከተማሩ በሁላ አ’ደጋሪር በተሰኘው አከባቢ ሰፈሩ።ከዚያም ሳሚጣህ ወደተሰኘው ከተማ በመሸጋገር ሼክ አብደላህ ኢብኑ ሙሀመድ አል-ቀርዓዋይ በቋቋሙት መድረሳ በመቀለቀል በዚህ መድረሳ ውስጥ ተውሂድ፡ብሉገል መራም፡ተጅዊድ፡ፈራኢድ ፡ሰርፍ ፡ነህው ለመማር ችለዋል።በ1368 እንደ ሂጅራ አቆጣጠር ወደ ሼክ ሀፊዝ አል-ሃከሚይ (አላህ ይዘንላቸውና) በማቅናት ከተለያዩ አከባቢ ከመጡ ተማሪዎች ጋር ለሶስት ወራት እውቀትን ቀስመዋል።ከዚያም እድሜያቸው 15 ገደማ ሳለ ወደ ሼክ አብደላህ ኢብኑ ሙሀመድ አል-ቀርዓዋይ መድረሳ በመመለስ ከፊል ተማሪዎችን በማስተማር ሀላፍትና ወሰዱ፡ከዚያም የመድረሳው ሙዲር(ዳሬክተር) በመሆን ማገልገልን ተያያቱ።

በ1375 በሁለት((ሼክ ሙሀመድ አል-ቀርዓዊይ እና ሼክ አሀመድ አል-ሀከሚይ)) ታላላቅ ሼኮች ሳሚጣህ ውስጥ በተከፈተው ተቋም ተጨማሪ እውቀትን እስከ 1379/1380 ባለው ጊዜ ውስጥ በብዙ ታላላቅ መሻኢኮች ላይ በመቅሰም እንዲሁም የተለያዩ የዲን ዘርፎችን አጠናቀቁ።

ሼክ አሁንም በዚህ አላበቁም ሪያድ ከተማው ውስጥ ወደ ሚገኘው አል-ኢማም ሱዑድ አል-ኢስላሚያህ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በመግባት የቁርዓን ሂፍዛቸውን በማጠናቀቅ ከዛው ሳይወጡ ተቋም ውስጥ ማስተማር ጀመሩ።የሚያስተምሩበት ተቋምም ዳሬክተር(ሙዲር) ነበሩ።
ከዚያም በ1382 ከርሳቸው ባልመነጨ ጥያቄ የመመረቂያ ሰርተክፌታቸውን(ሸሀዳህቸውን) ከሼክ መሁመድ ኢብኑ አህመድ አል-ሀከሚይ ወስደዋል።

እስከ 1417 ድረስ 35 አመት በፈጀ እድሜ ውስጥ ስርዓታዊ በሰፈነበት አካሄድ እውቅትን ቀሰሙ።(አላህ ይዘንላቸው)

ስለ ሼክ እንደሚነገረው ሼክን ያየና የሚያወቃቸው ለዱንያ ምንም እንደማይጨነቁ(ዛሂድ) ያውቃልም ተብሎ ይነገራል፡ሼክ ለዱንያም ካለመጨነቃቸውም ጋር ወደርሷ የሚሯሯጡበት ጊዜ አልነበራቸውም፡እድሜያቸውንም የጨረሱን እውቀትን በመቅሰም፡በማስተማር፡ፈታዋዎችን በመስጠት፡ በአጠቃላይ በዲናዊ ጉዳዮች ላይ ነው(ረሂመሁላህ)

ሼክ ዕውቀት የወሰደባቸው ታላላቅ መሻኢኮች ስም
1.ሼክ ዓሊ ኢብኑ ሙሀመድ ሃጂ አልመድኸሊይ
2.ሼክ ሃዲ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊይ
3.ሼክ አብደላህ ኢብኑ መሀመድ አል-ቀርዓዊ
4.ሼክ ሃፊዝ ኢብኑ አህመድ አል-ሀከሚይ
5.ሼክ ጃቢር ኢብኑ ሰልማን አልመድኸሊይ
6.ሼክ አህመድ ኢብኑ የህያ አል-ነጅሚ
7.ሼክ ሙሀመድ ዓጢየተ ሳሊም
8.ሼክ አብደል ዓዚዝ ኢብኑ ዓብዲላህ ኢብኑ ባዝ
9.ሼክ ሙሀመድ አማን አልጃሚይ
10.ሼክ ሙሀመድ ኢብኑ ሙሀመድ ጃቢል አልመድኸሊይ

ሌሎችም እዚህ ካልጠቀስኳቸው ኡለማዎችን እውቀትን ቀስመዋል።

እንዲሁም ሼክ አላህ በዋለላቸው ችሎታ እና ልገሳ እንድሜያቸውን የተማሩትን ትምህርት ከ50 አመት በላይ በማስተማር ብዙ ከተላያዩ ሀገሮች የሆኑ ተማሪዎችን አፍርተዋል። ወላሁ አዕለም።

أللهم اغفر له وارحمه وعافه واعف عنه,واكرم نزله ووسع مدخله,واغسله بالماء والثلج والبرد.
أللهم ارفع درجته في عليين واحشره مع الأنبياء والصديقين والصالحين.

Post a Comment

0 Comments