Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዘመናዊ ኸዋሪጆች! ኧረ የዘንድሮ ኸዋሪጆች ደግሞ ፈጣጣ ናቸውሳ? በሺርክ አያከፍሩም ሰልፍ የተቃወመን ግን ያከፍራሉ!!

ዘመናዊ ኸዋሪጆች!
ኧረ የዘንድሮ ኸዋሪጆች ደግሞ ፈጣጣ ናቸውሳ? በሺርክ አያከፍሩም ሰልፍ የተቃወመን ግን ያከፍራሉ!! ኸዋሪጅ የተለየ አፈጣጠር የለውም፣ ተክፊር ቀንድና ጂራት የለውም፡፡ ከኸዋሪጅ አንዱ መገለጫ መስሊሞችን ማክፈር ነው፡፡ የድሮዎቹ ኸዋሪጆች በአብዛሃኛው ታላላቅ ወንጀል የሚፈፅሙ ሙስሊሞችን ነበር የሚያከፍሩት፡፡ እንደ ኢኽዋን ያሉ በርካታ የዛሬ ኸዋሪጆች ግን ጥመታቸውን ስላልተጋራሃቸው ብቻ ያከፍሩሃል፡፡ አለቀ፡፡ ጥመታቸውን ኢስላማዊ ስም ያወጡለታል፤ “ለኢስላም መታገል፣ ለዲን መቆርቆር፣ ከመጥፎ መከልከል” በማለት፡፡ ተንኮላቸው ግልፅ ነው ለጥመታቸው ኢስላማዊ ስያሜ የሚያወጡለት የሚቃወማቸው ሲመጣ ኢስላምን እንደተቃወመ አድርጎ ለማቅረብ ነው፡፡ ይህን ባጢላቸውን ስትቃወም “ጂሃድ ተቃወሙ፣ ከጠላት ጎን ቆሙ፣ ..” በማለት ድምፃቻን ከፍ አድርገው ይጮኃሉ፡፡ እኛ ማንም ስላከፈረን አንደነግጥም፡፡ ኢስላም ማንም ሲፈልግ የሚነጥቀን ሲያሻው የሚሰጠን የግል ንበረት አይደለምና!! ይሄ በባጢል ማክፈራችሁ ግን እራሳችሁን ነው የሚጎዳው! ((እናንተ ሰዎች ሆይ! ድንበር ማለፋችሁ በራሳችሁ ላይ ነው)) (ዩኑስ፡ 23) በተውሒድና በተውሒድ ዱዓቶች ላይ የምታሴሩት ደባም እራሳችሁን እንጂ ማንንም አይጎዳም!! ((ክፉ ተንኮል በባለቤቱ ላይ እንጂ በሌላ ላይ አይሰፍርም!!)) (ፋጢር፡ 43) እነዚህ ከኋላ የሚገፏችሁ እስስቶች ሲዘፍኑ ካጨበጨባችሁላቸው ማክፈራችሁ አደጋ እንሚያመጣባችሁ አይነግሯችሁም፡- ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- “ወንድሙን አንተ ካፊር ያለ በርግጥም ከሁለት አንዳቸው ፈፅመውታል፡፡ እንዳለው ከሆነ (የተባለው ከፍሯል፡፡) ያለበለዚያ ወደራሱ (ወደ ተናጋሪው) ይመለሳል፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት) “ሙእሚንን መራገም ልክ እንደመግደል ነው!! አንድን ሙእሚን በኩፍር የወነጀለ ልክ እንደገደለው ነው!!” (ቡኻሪ የዘገቡት) እንደዋዛ የምትለቁት ቃል መዘዝ እንዳያመጣባችሁ ብትጠነቀቁ መልካም ነው፡፡ የሚገርም እኮ ነው፡፡ “ዘገርም ነገር አለ” የገረመው! ጭራሽ ይህን ቅጥ አንባሩ የጠፋው ሰልፋቸውን ስላልደገፍን ባደባባይ ማክፈር ያዙ እኮ?! “አይ ጃሂሎቹ ናቸው ተዋቸው” ይባል ይሆናል፡፡ በቲቪ ሰው እናስተምራለን የሚሉትንስ ምን እንበላቸው? ስትኮፈሱበት የኖራችሁበት እውቀት ጣራው ይሄው ሆነ? ቻግኒ ላይ ከቲጃኒያ ጋር ሲታረቁ የነበሩት እነማን ናቸው? ቲጃኒያ በሺርክ የተወረረ የሱፍያ ጠሪቃ አይደለም እንዴ? እስኪ ዐቂዳው ከአሕባሽ እንዴት እንደሚሻል ንገሩን? እናስ እነሱን ያላከፈራችሁትን ሰልፉን የማይደግፉት ግን ካፊሮች ሆኑ? ወላሂ አስተዋይ ለሆነ ሰው አይን ያወጣችሁ ስሜት ተከታዮች እንደሆናችሁ ይሄ ብቻ በቂው ነው፡፡ ((ነገሩ አይኖች አይታወሩም፡፡ ነገር ግን በደረቶች ውስጥ ያሉት ልቦች ናቸው የሚታወሩት!!)) ሰሐባ የሚያወግዙ ሺዐዎችን አያከፍሩም፣ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስለደጃል መምጣት የተናገሩት “ትክክል አይደለም” የሚለውን መውዱዲን አያከፍሩም፣ የሮማውንና የግብፁን ፓፓሳት ሲሞቱ “አላህ ይማራቸው” ያሉትን ቀርዳዊንና ሙርሲን አያከፍሩም፣ ኡማውን በጅምላ የሚያከፍረውን፣ ሰሐቦችን የሚያንቋሽሸውን፣ በቁርኣን ክብር እንዳሻው የሚረማመደውን ሰይድ ቁጥብን አያከፍሩም፣ ሌሎችም ፀጉር የሚያቆም፣ አካል የሚያሸማቅቅ አስደንጋጭ ጥፋቶችን የሚፈፅሙ የኢኽዋን ተራሮችን አያከፍሩም፡፡ እንዳውም ክንንፍ ይሉላቸዋል፡፡ ሰልፍን የሚቃወሙትን ግን ያከፍራሉ፡፡ ለመሆኑ ሰሐባን ከማንቋሸሽ፣ ኡማውን በጅምላ ከማክፈር፣ ነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከማስተባበል፣ በቁርኣን ከመቀለድ ይልቅ፣ ለሺርክ ከመሟገት በላይ ሰልፋችሁን መቃወሙ የከፋ ወንጀል ነው ማለት ነው? ((ምን ነካቸው እነኚህ ሰዎች ወሬን ለመረዳት እንኳን አይቀርቡምሳ?!!)) ከሰለፎች አንዱ የሆነ ጠሞ አጥማሚን ሲመለከት “ለሱ አላዝንም የማዝነው ላጠመማቸው ነው” ያለው ምንኛ ድንቅ አባባል ነው፡፡ ወላሂ እኔም ለናንተ አላዝንም የማዝነው በጭፍን ለሚከተላችሁ እናንተ አማን ቦታ ሆናችሁ እሳት ውስጥ ለምትማግዱት ነው፡፡ እሺ ይሁን “ሰልፍን መቃወም ኡዝር የሌለው ኩፍር ነው” እንበል፡፡ ምነውሳ ታዲያ እነ ኢድሪስ ሙሐመድና ሐሰን ታጁ ሰልፉን ሲቃወሙ አላከፈራችኋቸውም? የምን ባንድ እራስ ሁለት ምላስ መሆን ነው?
በቅርቡ ሰልፉ ላይ ያለንን ሀሳብ ስንገልፅ እነንቶኔ “ዐቂዳ አረጋችሁት እኮ” እያሉን ነበር፡፡ ዛሬስ ዐቂዳ ያደረገው ማን እንደሆነ ለማን ይሰወር ይሆን? ሰልፍ ስላልደገፉ ብቻ ሰዎችን የሚያከፍረው እየታየ ነው፡፡ “ሰልፉን የማትደግፉ ዞር በሉልኝ” እያሉ ፖስት አድርገዋል፡፡ በሰለፍያ ስም የሚነግዱ አንዳንድ በቀቀኖችም አብረው ሲያስተጋቡ አይተናል፡፡ በሰልፍ ጉዳይ “ሀጅር” ያደርጋሉ፡፡ ለሙብተዲዖች ምቹ አልጋ ናቸው፡፡ ለሰለፍዮች ሲሆን ግን ግስላ ናቸው፡፡ ትላንት “ሰሐቦችም በዐቂዳ ጉዳይ ተለያይተዋል” እያሉ የተውሒድን ጉዳይ ሲያቃልሉ እንዳልነበር ዛሬ ግን ሰልፍ መለያየት የማይቻልበት ያለበለዚያ የሚከፈርበት ትልቅ አጀንዳ ሆነ፡፡ ለመሆኑ ሰልፍ ስንተኛው የኢማን ማእዘን ነው? እስኪ የጣሃን ድስኩር፣ የሙሐመድ አወልን መንዙማ ስሙና ከአሕባሾች አቂዳ በምን እንደሚለይ አስረዱን? እሱስ ካፊር ነው? በቻናሎቻችሁ ስታቀርቡት፣ በየመድረኩ ስታደምቁበት የነበረው ጥፋቱ ሰልፍን ከመቃወም የቀለለ ሆኖ ነው እናንተ ዘንድ? ምናልባት እንደ ጥፋት ከቆጠራችሁት? “ሙሐመዱ ሰማን ገፍታሪው ቀደር” የሚል ሰው፤ “በናንተ የሸሸ ምንጊዜም አያፍር” እያለ ሺርክ የሚያሰራጭ ሰው፤ “አላህ የትም የለም” እያለ የአሕባሽን ጥመት በግልፅ የሚያስተጋባ ሰው ዐቂዳው ጤነኛ “ሆኖ” አብረውት ይሰራሉ፡፡ ሴቶች እርቃን የሚሰቃዩበትን፣ መሳጂድ የሚዘጋበትን፣ ደም የሚፈስበትን ሰልፍ የተቃወመ ግን ይቅርታም አይገባውም፣ ከጠላት ጋር ተባባሪ ነው፣…፡፡ ህሊና ያለህ አስተውል!! እንዲህ አይነት ፍረደ ገምድሎች ናቸው “ለዲንህ እናውቅልሃለን” ብለው የሚጋልቡህ፡፡ ንቃ “ሙእሚን ካንድ ጉድጓድ ሁለት ጊዜ አይነደፍም!!” ይላሉ መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡
በጣም የሚገርመው ደግሞ የሚያከፍሩት እነሱ ሆነው ሳለ እኛን ተክፊሮች ማለታቸው ነው፡፡ ለመሆኑ የተክፊር ትርጉሙ ተቀየረ እንዴ? “የሌባ አይነ-ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ!!” አሉ፡፡
“ለተውሒድ ተቆርቁረን ነው ሰልፍ የምንወጣው” ይሉናል፡፡ ድንቄም ተውሒድ!! የሚሊኒየሙን እርቅ ከማን ጋር ነው ያደረጋችሁት? የኛ የተውሒድ አርበኞች? ከቲጃኒያ ሱፍዮችስ ጋር መሞዳሞዱ ተውሒድ ነበር? ከነሙሐመድ አወል ከነጣሃ ጋር የነበራችሁስ ቅርበት ተውሒድ ኖሯቸው ነው? በየመውሊዱ ሲልከሰከሱ የነበሩት መሻኢኾቻችሁስ ተውሒድ ሊያስተምሩ ነበር ሲዘምቱ የነበረው? “ኢትዮጵያ ውስጥ የዐቂዳ ችግር የለም” የሚል ሰው ነው ለተውሒድ ዋጋ የሚሰጠው? ሀገራችን ውስጥ የዐቂዳ ችግር ከሌለለ እንግዲያው የናንተ ተውሒድ ምን አይነት ነው? ልዩነታችን የቀለም ልዩነት አይነት ቀላል ልዩነት ነው እያለ “ነጭ ቲሸርት ጥቁር ቲሸርት” እያለ የሚያሾፈው ነው ተውሒድ የገባው? ዳዒ ከጠሩ በኋላ “ተውሒድ ግን እንዳታስተምሩ” የሚሉት ናቸው ለተውሒድ ተቆርቋሪዎቹ? “ምን ነካችሁ እንዴት ነው የምትፈርዱት?”
የቅጥፈታቸው ቅጥፈት “ሙስሊሞች ላይ በደረሰው ነገር ተደስታችኋል” ማለታቸው ነው፡፡ ኢንሻአላህ አላህ ፊት እንተሳሰባለን!! ለመሆኑ ውሸት ሐራም መሆኑ ተዘነጋ እንዴ?! ረሒመላሁ ኢብኑ ሺሃብ አዝዙህሪ “ ‘አላህ ውሸትን ፈቀደ’ የሚል ተጣሪ ከሰማይ ቢጣራ ወላሂ! አልዋሽም!!” ይላል፡፡ ዛሬ የውሸት መጋዘን የሆኑት ኢኽዋንና በቀቀኖቹን ቢያይ ምን ይል ነበር?!! በሀሳብ ስለተለያየህ ብቻ “ሰዎችን ያሰበረግጋል” ብለው ያሰቡትን ሁሉ ያለምንም ጥንቃቄ እንዳሻቸው ይለጥፋሉ፡፡ ጌታችን አላህ ግን እንዲህ ይላል፡- ((እነዚያ አማኞች ወንዶችንና አማኝ ሴቶችን ባለሰሩት (እየወነጅሉ) የሚያስቸግሩ ሰዎች በርግጥም ቅጥፈትንና ግልፅ የሆነ ወንጀልን ተሸክመዋል)) (አልአሕዛብ፡ 57) እነሱ ተደብቀው እየቀሰቀሱ የሚያስደበድቡት አዛኝ ሆነው እኛ “ህዝብ እያስወጣችሁ አታስጎዱ” የምንለው ሆን የማናዝነው? ካስደበደቡ በኋላ የአዞ እንባ ማንባቱ ነው እዝነቱ? ዐጂብ!
ወላሂ ዘግናኝ ነው!!! እስኪ የትኛዋ ሙስሊማ ነች ዛሬ እርቃኗን አቁመው ሲሳለቁባት የቆዩ አረመኔዎች እንዲጫወቱባት ዳግም ወደ ሰልፍ እግሯን የምታነሳው? ለመሆኑ የትኛውን መብትሽን ልታስከብሪ ነበር የወጣሽው? የዲንን ህግጋት ሳያከግሩ ለዲን መቆርቆር አለ እንዴ? እሺ ይሁን እሷ ደጋሚ ምላሶች ተብትበውባት፣ ጥፋቷን እንደ ልማት እየቆጠረች ዳግም ወደ ተኩላዎቹ “እወጣለሁ” ብትል እስኪ ማነው ኒቃብ የለበሰች ሚስቱን፣ እህቱን ወይም ልጁን ልብሷን አስወልቀው ሲዘባበቱባት እንደቆዩ እያወቀ ዳግም ወደ ሰልፍ እንድትሄድ የሚለቃት? ሴቶችን ቀስቅሶ የአረመኔ መጫዋቻ ያደረጋቸው፣ ኒቃብ የለበሱ እህቶችን ልብሳቸውን እያስወለቁ በታይትና በጡት መያዣ አስቁመው እንዲሳለቁባቸው ያደረገው ማነው? በውድቅት ሌሊት አባረው ለአደጋ እንዲጋለጡ ያደረጋቸው ነው ለሴቶቻችን የሚያዝነው?! ስንት ያልሰማነው ያላወቅነው የደረሰ ነገርስ ይኖራል? እውነት አንድ ሰው እህቱ ወይም ልጁ እንደዚህ ብትደረግ ዳግም ስትወጣ ዝም ይላል? ደዩስነት እስከዚህ ደርሷል ማለት ነው?!! ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይ ራጂዑን!! ይሄን የጀዝባ “ጂሃድ” ስላልደገፍን ነው ከመንግስት ጋር እንደምናብር፣ የሙስሊሙ ግፍ እንደሚያስደስተን የሚነዛው?! አላሁልሙስተዓን!! አብሺሩ የምትዋሹት ሁሉ እየተመዘገበ ነው!!” እንዳውም ህዝባችንን ውጭ የመሸጉ ፖለቲከኞች መጠቀሚያ ያደረጋችሁት እናንተ እንጂ እኛ አይደለንም፡፡ ወደዚህ ሰልፍ እየተጣሩ ካሉት ውስጥ፡- ትላንት የፈረንሳዩን ፀረ-ሒጃብ ህግ እንደግፋለን ሲሉ የነበሩ ሸፍጠኞች፣ ሀገራቸው ለመግባት ተስፋ የቆረጡ ገልቱዎች፣ እዚህ ሰልፉን ሲያራግቡ ቆይተው ሸሽተው የወጡ ብልጣብልጦች፣ ማህበራዊ ድረ-ገፆች ላይ ኢዕቲካፍ ያደረጉ ፈሪዎች ናቸው፡፡ “ሞት እንደሁ አይቀርም” እያሉ ሰው ከመማገድ ጀግና ከሆኑ ወደ ሀገር ገብተው ለምን አብረው አይሰለፉም? ከዳር አድፍጣችሁ የምትማግዱ ቀስቃሾች ሆይ! እውነት ትግላችሁ ለተውሒድ ከሆነ፣ እውነት አላማችሁ ጀነት ከሆነ የምን ዳር ሆኖ ማጨብጨብ ነው? ነው እናንተ ጀነት አትፈልጉም? አብዛሃኞቹ ቀስቃሾች ፍልሚያው ውስጥ የሉም፡፡ እውነት የምትጮሁት ለዲን ከሆነ ለምን አትቀላቀሉም? የኛ ታጋዮች ትግላችሁ የበለጠ ሙስሊሙን እያዋረደው፣ ይበልጥ ብዙ እያስከፈለው ነው፡፡ ትግላችሁ ያተረፈው አንድ ኸይር የለም፡፡ ትግላችሁ መሳጂድ ነው ያስነጠቀው፤ ሙስሊሞችን ነው ያስጨፈጨፈው፤ ህዝብ ነው ያሳደደው፤ ሴቶቻችንን በማጋለጥ ክብራችንን ነው ያዋረደው!! ይሄ ሁሉ ሆኖም አትማሩም!! ከቁርኣን አትማሩ! ከሐዲሥ አትማሩ! ከሰለፎች ትውፊት አትማሩ! ከምታዩትና ከሚደርሰው ነገር አትማሩ! ወላሂ እንስሳ እንኳን ደጋግመህ ስትመልሳት ይገባታል፡፡ እንዳውም “ትግል ነው ብዙ ነገር ሊደርስ ይችላል፡፡ አቅም የለንም ብለን ዝም ልንል ነው ወይ?” ይሉናል፡፡ ውጭ ያሉትን ብልጣብልጦች ትቻለሁ፡፡ እዚህ ያላችሁ የዋሃን ሆይ! የሚደርሰው ካላሳሰባችሁ፣ እውነት ስራችሁ ጀግንነት ከሆነ መስጂድ ዙሪያ የቁራ ጩኸት ከማሰማት ለምን ቤተ-መንግስት አትሄዱም? አራት ኪሎ ጠፋባችሁ? የምን ፈራ ተባ ማለት ነው? እናስ ሴቶችን የማንም መጫወቻ እያደረግክ ነው ድል የምታሳካው?! አንቺስ እህቴ አታስተውይም ሰብስቦ የሚያግትሽ ፖሊስ ለማውራት የምትሸማቀቂበት፣ ስታስቢ የምትሳቀቂበት ክፋት እየፈፀመብሽ እንደሆነ እያየሽ ነው የምትወጪው?! እውነት ለዲን መታገል እንዲህ ነው?
“ቅድሚያ ለተውሒድ ብላችሁ ስታጨበጨቡ የነበራችሁ በሙሉ ሙስሊሙ ለተውሒድ ሲል ሲገረፍ፣ ሲገደል… ኒቃብ ጂልባብ ሲቃጠል የት ገባችሁ” ብለው ፅፈዋል፡፡ ሰዎቹ ጤናም የላቸው?! የት እንሁንላችሁ? ሰልፋችሁን ስለተቃወምን እየተሳደባችሁ አይደል? እናስ እናንተ ስለሰራችሁት በምናዝንበት ሰልፍ ውስጥ እንድንገባ ያምራችኋል? ደግሞም አትርሱ!! የተዋረዳችሁት በፈቃዳችሁ ነው!! ወራዳ ማለት ከማይቋቋመው ፈተና ውስጥ በፍቃዱ የሚዘፈቅ ነው፡፡ የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡- “ሙእሚን እራሱን ሊያዋርድ አይገባውም፡፡” “እንዴት እራሱን ያዋርዳል” ተብለው ሲጠየቁ “ለማይቋቋመው ፈተና እራሱን ማጋፈጡ ነው” አሉ፡፡ (አሰሒሐህ፡ 613) ሴቶቻችን ላይ የተፈፀመው ይሄ እራሱ ነው፡፡ ሰዎቹ ግን ሐዲሥ አይመልሳቸውም!! እንዳውም ህሊና ቢኖራችሁ ያስደበደባቸው፣ ያስገደላቸው፣ ሴቶቹንም ያዋረዳቸው ለሰልፍ የቀሰቀሳቸው ገልቱ ነው!! አስተዋይ የሆነ ሰው ይህን ሐዲሥ ይመልከት፡- ጃቢር ረዲየላሁ ዐንሁ እንዲህ ይላል፡- “በአንድ ወቅት መንገድ ወጣንና አንዱን ሰው ድንጋይ እራሱን ፈነከተው፡፡ ከዚያም ጁኑብ ሆነና ጓደኞቹን “ተየሙም ማድረግ የምችልበት ፍቃድ” ታገኙልኛላችሁ” ሲል ጠየቀ፡፡ “አይ ውሃ መጠቀም እየቻልክ (ለተየሙም) ፈቃድ አናገኝልህም” አሉት፡፡ በውሃ ታጠበና (ቁስሉ አገርሽቶበት) ሞተ፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘንድ በመጣን ጊዜ ጉዳዩ ሲነገራቸው፡- “ #ገደሉት_አላህይግደላቸውና ! ካላወቁ አይጠይቁም ነበር? የአለማወቅ መድሃኒቱ መጠየቅ ነው?!” አሉ፡፡ አልባኒ “ሰሒሕ” ብለውታል፡፡ አስተውሉ የተሳሳተ ፈትዋ ሰጥተውት ስለሞተ ነው “ #ገደሉት_አላህ ይግደላቸውና” ያሏቸው፡፡ እናንተ ግን ሞት ካለበት፣ ውርደት ካለበት ቦታ ሰው እየማገዳቸሁ ነው ኋላ የምታለቅሱት፡፡ “ጋዜጠኞች የት አሉ? ተቃዋሚዎች ለምን ዝም ይላሉ?” እያሉ ቢያላዝኑት ምን ፋይዳ አለው? የነቢላሉልሐበሺን፣ የነዐማርን ታሪክ እያስታወሱ ከንፈር መምጠጡ ካልተማርንበት ምን ዋጋ አለው? ለመሆኑ ሰሐቦች ከኛ የበለጠ ስቃይና እንግልት አልደረሰባቸውም እንዴ? እስኪ ኸባብ ኢብኑልአረት ረዲየላሁ ዐንሁ ምን እንደሚል እዩት፡- ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከከዕባ ጥላ ስር ኩታቸውን ደገፍ ብለው ሳለ አገኘናቸው፡፡ በርግጥም ከሙሽሪኮቹ ስቃይ እየደረሰብን ነው፡፡ “አላህን እርዳታን አትጠይቅልንምን? አላህን አትለምንልንም?” አልናቸው፡፡ “ከናተ በፊት የነበሩ ህዝቦች ዘንድ ጉድጓድ ይቆፈርለትና ውስጥ እንዲገባ ተደርጎ በመጋዝ ከአናቱ ጀምሮ ለሁለት ይከፈላል፡፡ ይሄ ሁሉ መሆኑ ግን ከዲኑ አይመልሰውም፡፡ በርግጥም አላህ ይህን (ዲን) ይሞላል ተጓዥ ከሰንዐ እስከ ሐድረመውት ሲጓዝ አላህን እንጂ ወይም ለበጎቹ ተኩላን እንጂ ሌላ ጉዳይ እስከማይፈራ ድረስ፡፡ ነገር ግን እናንተ#ትቸኩላላችሁ !!” (ቡኻሪ የዘገቡት) ይሄ ሁሉ ሲሆን ግን ሰብር እንጂ ሰልፍ አላደረጉም!! መካ ላይ ሰሐቦች ሲገደሉ ሲሰቃዩ፣ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እትብታቸው በተቀበረበት ሀገር ሲደፈሩ፣ ሲንገላቱ አቅማቸው በፈቀደ እንዲያስተምሩ ከሙሽሪኮቹ የሚደርሰውን ግፍ ግን እንዲታገሱ ነበር የታዘዙት፡፡ ቀደምት ነብያትና ተከታዮቻቸውም ጋር በተያያዘ ተመሳሳይ ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል፡- ((ከበፊትህም መልእክተኞች በእርግጥ ተስተባብለዋል፡፡ በተስተባበሉበት ነገርና በተሰቃዩበት ላይ እርዳታችን እስከመጣላቸው ድረስ #ታገሱ፡፡ የአላህንም ንግግሮች ለዋጭ የለም፡፡ ከመልእክተኞቹም ወሬ (የምትረጋጋበት) በእርግጥ መጣልህ)) (አልአንዓም፡ 34) ((ከናንተም በዚያ እኔ በርሱ በተላኩበት ያመኑ ጭፍሮችና ያላመኑ ጭፍሮችም ቢኖሩ#በመካከላችን_አላህ_እስከሚፈርድ_ታገሱ ፡፡ እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው፡፡)) (አልአዕራፍ፡ 87) (( #እናንተ_ሰዎች_ሆይ !#እውነቱ_ከጌታችሁ_በእርግጥ_መጣላችሁ (በርሱ) የተመራም ሰው የሚመራው ለራሱ ነው፡፡ የተሳሳተም ሰው የሚሳሳተው (ጉዳቱ) በራሱ ላይ ነው፡፡ እኔም በናንተ ላይ ተጠባባቂ አይደለሁም በላቸው፡፡ ወዳንተ የሚወረደውን ነገር ተከተል፡፡ አላህም (በነሱ ላይ) #እስከሚፈርድ_ድረስ_ታገስ፡፡ እርሱም ከፈራጆች ሁሉ በላጭ ነው፡፡)) (ዩኑስ፡ 108-109) ሙሳ ዐለይሂሰላም እና ተከታዮቻቸው በፊርዐውን ሲሰቃዩ ሰብር እንጂ ሰልፍ አላደረጉም!! እናንተ ግን “ሰብር እናድርግ” ማለትን እጅን አጣጥፎ መቀመጥ አልፎም ፍርሃት አድርጋችሁታል፡፡ እንዲህ አይነት የተገለበጠ ግንዛቤ ይዞ ድል አይታለምም!! አላህ ግን ሰብር በራሱ የእርዳታ ሰበብ እንደሆነ ነበር የነገረን፡፡ ((እናንተ ያመናችሁ ሆይ! #በሰብርና በሰላት ታገዙ አላህ #ከታጋሾች ጋር ነው፡፡)) (አልበቀራህ፡ 153) ((በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ በእርግጥ ትፈተናላችሁ፤ ከነዚያም ካጋሩት ብዙ ክፋትን ትሰማላችሁ፡፡ #ብትታገሱና አላህን ብትፈሩ ይህ ከጥብቅ ነገሮች ነው!!)) (አሊ ዒምራን፡ 186) በኑ ኢስራኢሎችን ፊርዐውን ሲጨፈጭፋቸው፣ ሲያሰቃያቸው ሙሳ ዐለይሂሰላም ምንድን ነው ያሏቸው? ((በአላህ ታገዙ፣ #ታገሱም፣ ምድር ለአላህ ናትና፤ ከባሮቹ ለሚሻው ያወርሳታል መልካም ፍፃሜዋም አላህን ለሚፈሩት ናት፡፡)) አዎ የተባለው ተፈፀመ፡፡ ፊርዐውንና ግበረ አበሮቹ ጠፉ፡፡ ትላንት ሲዋረዱ የነበሩት የበላይ ሆኑ፡፡ የበላይ የሆኑት ግን በሰብር እንጂ በሰልፍ አልነበረም፡፡ አብረን እናንብብ ((እነዚያንም ደካሞች የነበሩትን ህዝቦች ያችን በውስጧ በረከት ያደረግንባትን ምድር ምስራቆቿንም ምዕራቦቿንም አወረስናቸው፡፡ የጌታህም መልካሚቱ ቃል በእስራኢል ልጆች ላይ #በመታገሳቸውተፈፀመች፡፡..)) (ሱረቱል አልአዕራፍ ከ124-137 ያለውን ረጋ ብለው ይመልከቱ)) ይሄው ለሚያስተውል ሰው ሰብር ምንም ነገር ሳይሆን ትልቅ ነገር ነው፡፡ “አልታገስም” ያለ፣ የትእግስትን ዋጋ ያቃለለ እራሱንም ይጎዳል ገፈቱ ለሌሎቹም ይተርፋል፡፡ ኢስላምን ለሚያጠቁ ሀይሎችም ጥሩ ምክኒያት ይሆናቸዋል፡፡ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “#የሚደንቀው_በሰንካላ_አእምሯቸው_በብልሹ_እይታቸው_ተመረኩዘው_ሸሪዐን_ለመርዳት_የሚሞክሩ_ሰዎች_ሁኔታ_ነው ፡፡#የሚሰሩት_ስራ_አፈንጋጭ_የኢስላም_ጠላቶች_በኢስላም_ላይ_እንዲረማመዱ_አድርጓል ፡፡” (መጅሙዑልፈታዋ፡ 9/253) ሱብሐነላህ! ወላሂ ይሄ ንግግር በደንብ አድርጎ እናንተን ይገልፃል!! ነገር ግን ልብ ከታወረ አይን አያይም!! ወላሂ እኔ እንዳውም ኢስላምና ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰውን እየተመለከቱ ሙጭጭ የሚሉ ሰዎችን ሳይ ስማቸውን ቀይረው የገቡ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ እየጠረጠርኩ ነው፡፡ በተጨባጭ የኛው መርቃኞችም መኖራቸው የማይካድ ከመሆኑ ጋር!!!
አላህ እውነቱን ያሳየን፡፡ ሐቅን በመከተልም በመግለፅም ላይ የሰዎችን ወቀሳ ከማይፈሩት ያድርገን፡፡ ወሰለላሁ ዐላነብይና ሙሐመዲን ወዐላ ኣሊሂ ወሰሕቢሂ ወሰለም፡፡