Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፡- በሀገራችን ወደ አላህ ከሚጣሩ ወንድሞቻችን አንዳንዶቹ በሙሐደራዎች ወይም......


ጥያቄ፡- በሀገራችን ወደ አላህ ከሚጣሩ ወንድሞቻችን አንዳንዶቹ በሙሐደራዎች ወይም በኹጥባዎች ላይ ለምሳሌ ኢስቲዋእ (የአላህን ከላይ መሆን) ኢስቲጋሳህ (ከአላህ ሌላ ካለ እርዳታ መጠየቅ)፣ በመሳሰሉ ጉዳዮች ላይ ላለማውራት ከሱፍዮች ጋር ተስማምተዋል፡፡ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከአይሁድ ጋር ያደረጉትን ስምምነት እንደማስረጃ ተጠቅመዋል፡፡ ሸይኽ ሆይ! ይሄ የመረጃ አጠቃቀም ጤነኛ ነው? ምንድን ነው በዚህ ላይ የምትሉት?
መልስ፡- በጭራሽ! ይሄ የመረጃ አጠቃቀም ጤነኛ አይደለም፡፡ ምክኒያቱም ይሄ የምትጠቅሰው ነገር አላህ በቁርኣኑ ((እንድትለሳለስላቸው እንዲለሳለሱልህም ወደዱ)) ሲል የገለፀው ነው፡፡ በዲን ላይ በዚህ መልኩ መለሳለስ (ሙዳሀና) አይፈቀድም፡፡ መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከአይሁድ ጋር የተስማሙት አንዱ በሌላው ላይ ድንበር እንዳያልፍ ነው፡፡ እንጂ በዲናቸው እንድንወድ አይደለም፡፡ በፍፁም!! መልእክተኛው ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዲናቸውን ሊወዱላቸውም ፈፅሞ አይታሰብም፡፡ እናም ይሄ የጠቀስከው ነገር ያሉበትን ባጢል መውደድ ማለት ነው፡፡ በዚህ መልኩ መስማማት ደግሞ በተጨባጭ ሙዳሀናህ ነው፡፡ በዲን ሂሳብ የሚደረግ መለሳለስ፡፡ ሙዳሀና ደግሞ ሐራም ነው፡፡ በአላህ ዲን ጉዳይ ማንንም ሊያስደስት መለሳለሱ ለማንም አይፈቀድም፡፡ ይልቅ ምንም ይሁን ምን ሐቅን ግልፅ ማድረግ ግድ ይለዋል፡፡ ነገር ግን አስቀድመው በተቃውሞ በመጀመር ፋንታ ትክክለኛ በሆነ ማብራሪያ መጀመራቸው የተሻለ ሆኖ ከታያቸው፣ ለምሳሌ እንዳላችሁት ስለ ኢስቲዋእ ሲናገር የኢስቲዋእን መልእክት ቢያብራራ፣ እውነታውንም ግልፅ ቢያደርግ፣ ሰዎች እስከሚረጋጉና ሐቁንም እስከሚያውቁ ድረስ፣ ከነበሩበት ባጢል ወደሐቅ መሸጋገር ይቀላቸው ዘንድ “እንዲህ እያሉ የሚፈስሩት አሉ” ሳይል ቢያስተምር፣ በዚህም ላይ ቢስማሙ ችግር ላይኖረው ይችላል፡፡
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ፡ (ሊቃአቱ አልባቢልመፍቱሕ፡ 156)
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ፡፡ “ወደ መልካም ያመላከተ ልክ እንደ ሰሪው ነው (አጅሩን የሚያገኘው)” ይላሉ ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡