Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አጭር ታሪክ

አጭር ታሪክ
1. ከአሕመድ ልጆች አንዱን ጠላት በሌሊት ገደለው
2. አሕመድ ወደ ጠላት አቅጣጫ ጥይት መተኮስ ያዘ
3. ጠላቱ የአሕመድን ቤት አውድሞ የቀሩትን ልጆቹን ጨረሳቸው
4. ጧት ላይ ፡-አሕመድ “ድል አደረግኩኝ” ብሎ ማክበር ያዘ፡፡
ከሸይኽ ሐመድ አልዐቲቅ የትዊተር ገፅ የተተረጎመ፡፡
(ሁልጊዜ ሐማስ የሚሰራው እንዲህ አይነት የምርቃና ስራ ነው፡፡ ለነገሩ ስሙ እራሱ ወደዚያው የቀረበ ነው፡፡ ጥቂት ሚሳኢሎችን ወደ “እስራኢል” ይተኩሳል፡፡ ሚሳኢሎቹ ይሄ ነው የሚባል ጉዳት “እስራኤል” ላይ ሳያደርሱ ባየር ላይ እንዲከሽፉ ይደረጋሉ፡፡ ከዚያ ሐማስ እንደ ጀግና ተደብቆ ያቅራራል፡፡ የሚያልቁት ህፃናት ናቸው፡፡ ኢስላም ይሄን ያክል ሂሳብ እንኳን የማይችል የጀዝባ ሀይማኖት ነው እንዴ?! ዐማር እንዲህ ሆነ ሱመያ እንዲህ ሆነች እያልን ከንፈራችንን ከመምጠጥ ታሪካቸውን በተግባር በወሰድን፡፡ አንድ የ “እስራኤል” ወታደር ይጠልፍና መቶ ሁለት መቶ ሴትና ህፃናት ያስጨርሳል፡፡ “እስራኤል” “ገደለችብኝ” ብሎ ጥቂት ሚሳኢሎችን በከንቱ ያስወነጭፍና ህዝብ ያስጨፈጭፋል፡፡ ወትሮስ ታዲያ ነፍሰ-በላ አይሁዳውያን ሊያዝኑልን ነው? ከዐለም ዝምታ ይበልጥ የሚገርመው የጀዝባው ሐማስ ቂላቂል ስራ ነው፡፡ ቀላል ሂሳብ እኮ ነው የሆነ አካል ልጅህን ገደለብህ፡፡ ልትበቀል ብትሞክር ምንም ሳትጎዳው ቀሪ ቤተሰብህን እንደሚጨርስብህ ካወቅክ ምን ታደርጋለህ? እሺ እንደ ሐማስ እበቀላለሁ ብለህ ቤተሰብህን አስጨረስክ እስኪ በዝምታ ከሚመለከትህ ጎረቤት ጭካኔና ካንተ ሞኝነት የቱ ይከፋል?)