Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነብዩ ሙሃመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሰው ናቸው፡፡

ነብዩ ሙሃመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሰው ናቸው፡፡

አላህ መላእክቶችን ከኑር (ከብርሃን) ነው የፈጠራቸው፡፡ ኢብሊስ እና ዝርያዎቹ ከእሳት፡፡
አደም እና ዝርያዎቹ ከጭቃ፡፡

አደም እና ዝርያዎቹ መሰረታቸው ከጭቃ ቢሆንም እዚህም ውስጥ 4 አይነት ሁኔታ አለ፡፡ 
1) አደም ከጭቃ ያለ አባት ያለ እናት፤
2) ሃዋ ከአደም የግራ ጎን፤
3) ነብየላህ ኢሳ (አለይሂ ሰላም) የለአባት ከእናት ፤
4) የተቀሩት የሰው ልጆች ከአባት እና እናት

አርስቱ ነብዩ ሙሃመድ ﷺ ሰው ናቸው የሚል ነው፡፡ የሚከተሉት ኢስላም ውስጥ ሰርጎ ገብ የሆኑ መጤ አስተሳሰቦች አሉ፡፡ የሚከተሉትን ይመስል

1) ‹‹ረሱል ﷺ ከኑር (ብርሃን) ነው የተፈጠሩት››
2) ‹‹ኑሩር ከኑሩ (ብርሀኑን ከብርሀኑ)፤
ኸለቀው ጀሊሉ (ፈጠረው ታላቁ አላህ)››

እነዚህን ውድቅ አምነትን የሚያበላሹ አባባሎች ሸሪዐ የሚሰጣቸው መልስ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡
ነብዩ ሙሃመድ ﷺ ሙሉ ስማቸው፤ ሙሃመድ ኢብን አብደላህ ኢብን አብድል ሙጠሊብ (ሙሃመድ የአብደላህ ልጅ፤ አብደላህ የአብድል ሙጠሊብ ልጅ) ነው፡፡ እናታቸው አሚና ቢንት ወሃብ ናቸው፡፡ ነብዩ ሙሃመድ ﷺ ከወንድ እና ከሴት ነው የተገኙት፡፡

አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) በል ብሎ ሰው መሆናቸውን እንዲናገሩ እንዲህ ሲል ያዛቸዋል፡፡
قُلْ إِنَّمَا أَنَا بَشَرٌ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ
«እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደኔ የሚወረድልኝ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ፡፡››
ልብ ሊባል የሚገባው እንደናንተው ሰው ነኝ ሲሉ ከእኛ የሚለዩበት ነገር መኖሩን ማወቅም ግድ ይላል እሱም የአላህ መላክተኛ ﷺ መሆናቸው፤ መለኮታዊ ራዕይ ወደ እሳቸው እንደሚመጣላቸው ማወቅ ነው፡፡

ሌላው ነብዩ ﷺ ሰው እንደሆኑ እና እንደሚረሱ እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል ‹‹እኔ እንደናንተው ሰው ነኝ፡፡ እንደምትረሱት እረሳለሁ››

ሌላው አላህ መልክተኞችን የሚልከው ለጎሳቸው ነው፡፡ ለሰው ሰው ይልካል፡፡ ሰዎች መሪ ቁርዓን ሲመጣላቸው ምን ከማመን እንደከለከላቸው ሲናገር እንዲህ ይላል

وَمَا مَنَعَ ٱلنَّاسَ أَن يُؤْمِنُوٓا۟ إِذْ جَآءَهُمُ ٱلْهُدَىٰٓ إِلَّآ أَن قَالُوٓا۟ أَبَعَثَ ٱللَّهُ بَشَرًا رَّسُولًا
ሰዎችንም መሪ (ቁርኣን) በመጣላቸው ጊዜ ከማመን «አላህ ሰውን መልክተኛ አድርጎ ላከን?» ማለታቸው እንጂ ሌላ አልከለከላቸውም፡፡

አላህም ለሰዎች ሰውን እንደሚልክ እና ምድር ላይ የሚኼዱት መላዕክቶች ቢሆኑ መልአክን ይልክ እንደነበር እንዲህ አለ::

قُل لَّوْ كَانَ فِي الْأَرْضِ مَلَائِكَةٌ يَمْشُونَ مُطْمَئِنِّينَ لَنَزَّلْنَا عَلَيْهِم مِّنَ السَّمَاءِ مَلَكًا رَّسُولًا
«በምድር ላይ ረግተው የሚኼዱ መላእክት በነበሩ ኖሮ በእነሱ ላይ (ከጎሳቸው) የመልአክን መልክተኛ ባወረድን ነበር» በላቸው፡፡

ነብዩ ሙሃመድ ﷺ መልሰው እንዲህ አሉ ‹‹ከአደም ልጆች ሁሉ ምርጥ ማለት እኔ ነኝ ለጉራ አይደለም››፡፡ እነዚህን እና መሰል ማስረጃዎች የአላህ መላክተኛ ﷺ የአደም ልጅ ለመሆናቸው አስላቸው ከጭቃ የተፈጠረ፤ ከወንድ እና ከሴት የተፈጠሩ ለመሆናቸው እና መስመር የሳቱ የቢድዓ ሰዎች እንደሚሉት ከኑር (ብርሃን) ላለመፈጠራቸው በቂ ማስረጃ ነው፡፡

እምነታችንን እንጠብቅ፡፡ አላህ ሆይ! እውቀትን ጨምርልን፡፡