Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሂድ አላህን በብቸኝነት በማምለክና ከሽርክ በመራቅ እንጂ አይገኝም !



قال تعالى "وإذ قال إبراهيم لأبيه وقومه إنني براء مما تعبدون ● إلا الذي فطرني فإنه سيهدين " الزخرف 27-26

"ኢብራሂም ለአባቱና ለህዝቦቹ ባለ ግዜ አስታውስ ። እኔ ከምትገዙት ሁሉ ንፁህ ነኝ ። ከዚያ ከፈጠረኝ በስተቀር ። እርሱ በእርግጥ ይመራኛል ።" አል ዙኽሩፍ 26,27

አላህ ሱብሃነ ወተአላ በዚህች አንቀፅ ላይ የአንድ ሰው ተውሂድ ከሽርክ በመራቅና አላህን በብቸኝነት በማምለክ እንጂ እንደማይሟላ ይናገራል ። ይህም የላኢላሃ ኢለሏህ መሰረታዊ ትርጓሜ ነው ። እንድንከተለው ከታዘዝነው ከኢብራሂም አለይሂ ሰላም ዋና መሰረታዊ መንገድ አንዱ ነው ።

፨ ተውሂድ አላህን በብቸኝነት በማምለክ እንጂ ፈፅሞ አይገኝም። ለየትኛውም ግለሰብ ከአላህ ጋር አንድንም አካል ማጋራት አይፈቀድለትም ። ስለዚህ አላህን በብቸኝነት ያለምንም ተጋሪ ማምለክ ግድ ነው ።

። ሰዎች ከአምልኮ አንፃር ሶስት አይነት ናቸው ፦

1.አላህን በብቸኝነት የሚገዛ

2.ከአላህ ሌላ ያለን ብቻ የሚገዛ

3. አላህንም ሌላንም አካል የሚገዛ

የመጀመሪያዎቹ የኢኽላስ ባለቤቶች "ሙወሂድ "ሲሆኑ ሁለተኞቹ የፈጣሪን መኖር ያስተባበሉ "ካፊር" ናቸው ሶስተኞቹ ደግሞ በአላህ ላይ የሚያጋሩ "ሙሽሪክ" ናቸው። አላህ ከሙወሂድ ባሮቹ ያድርገን