Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ማን_ከማን_ያንሳል? አንደኛው ዒራቅ ላይ ሌላኛ ናይጄሪያ ላይ ሶስተኛው ደሞ የት ይሁን?

 

ማን_ከማን_ያንሳል?


አንደኛው ዒራቅ ላይ ሌላኛ ናይጄሪያ ላይ ሶስተኛው ደሞ የት ይሁን?

ከወደናይጄሪያ የሚሰማው ያስቃልም ያናዳልም ። ቅዳሜ ዕለት በናይጄሪያ የሚገኘው ፅንፈኛ የተክፊሮች ቡድን የሆነው ቦኮ ሃራም በኢንተርኔት ቪድዮ ለቋል ። ይህም ቪድዮ ላይ የቡድኑ መሪ የሆነው አቡ በክር ሸይክኹ (አቡ በክር የሚለው ስም ፈረደበት እኮ ) እንደተናገረው (እንዳስፈራራው ልበለው እንጂ) በናይጄሪያ ሃገር ላይ በሰሜን በኩል የምትገኘው ቦሮኖ ከተማ ውስጥ የምትገኘውን ጙዎዛ መንደር ላይ 'ኢስላማዊ' ደውላ (ግዛት) ማቋቋሙን እና እራሱንም አሚር (ኸሊፋ) አድርጎ መምረጡን አውጇል ። ይህች ክልል በውስጧ ከሃምሳ ሺህ ሰው በላይ እንደያዘች ይነገራል ።

ይህ ፅንፈኛ የተክፊር ቡድን ከተመሰረተ ጀምሮ ከ10ሺህ ሰው በላይ እንደገደለ ሲነገርለት ከዒራቁ የኸዋሪጆች ቡድን ዳኢሽ ጋር ጥብቅ ቁርኝት እንደነበረውና ከወር በፊት የዳኢሾቹ መሪ አቡ በክር አል በጝዳዲ ሁሉም የሱን መሰል ቡድኖች ሙባያዕ (ቃል ኪዳን) እንዲገቡለት ማሳሰቡን ተከትሎ የናይጄሪያው ቦኮ ሃራም መሪ በይዐ መግባቱን የሚያሳይ ቪድዮ ለቆ እንደነበር የሚታወስ ነው ።

ነገር ግን ባሳለፍነው ቅዳሜ በኢንተርኔት በለቀቁት ቪድዮ ላይ መሪው አቡ በክር እጁ ላይ ወረቀቱን እንደያዘ ደስታ የተቀላቀለበት ንግግሩን እንዲህ ሲል ተናግሯል.. " ጙዎዛን እንድንመራ አላህ አዞናል ። በርግጥም ናይጄሪያን ብቻ ሳይሆን ዐለምን እንድንመራ ታዘናል ። ስለዚህ ከ አሁኑ ጀመረናል.." ይላል ።

በተመሳሳይ ቪድዮ ይሀው መሪ እንዳሳወቀው በአቡጃ ፣ ዳማቱሩ ፣ ዳምቦዋ እና ሌሎችም የሃገሪቱ ክልሎች ላይ በንፁሃን ላይ የደረሰውን ጥቃት ሃላፊነቱን እንደሚወስድና ለስኬቱም አላህን እንደሚያመሰግን ገልፇል።

አዑዙ ቢላህ ( አላህ አንድን ነፍስ ያለ አግባብ ማጥፋት የአደም ልጆችን በአጠቃላይ ማጥፋት እንደሆነ መናገሩን አያውቁትምን? ለነገሩ ልብ ከተደፈነ ነገሩ አከተመ አይደል የሚባለው?)

በዚህ በያዝነው ወር ቦኮ ሃራም ጙዎዛ ክልልን መበጥበጡን ከተያያዘ ወዲህ ከ50 በላይ የሚቆጠሩ ዜጎችን መግደሉ የታወቀ ሲሆን ፤ ከወራት በፊት ደሞ በዚችው ክልል ውስጥ የሚገኙ ኤዜጝ መንደር ገብቶ ከ121 በላይ ዜጎችን ገድሏል ። የመንደሩ ሙስሊም መሪ የነበሩትን አል ሃጂ ኢድሪሳ ቲምታ የገደለ ሲሆን የርሱ ምትክ የነበረውን ልጁን አግተው ወስደዋል ።

ቦኮ ሃራም ከሚታወቅባቸው ነገሮች ውስጥ በሚለቋቸው ቪዲዮዎች ላይ አሜሪካና 'እስራዒል' ብሪቴንን አብዝቶ መኮነኑና ማስፈራራቱ (ሙስሊሞችንና ንፅሁሃኖችን ለቀቅ አድርጎ እነሱን ቢዋጋማ ምን ነበረበት?) ሲሆን ነገር ግን በሚወስዳቸው ዕርምጃዎች ላይ ተጠቂው ሙስሊሞችና ንፅሁሃን ዜጎች መሆናቸው ይታወቃል ። በቅርብ ጊዜም ከ200 በላይ ሴት ልጆችን አግቶ እንደነበር ይታወቃል ።

(( ሱብሃነ'ላህ ! በአላህ ይሁንብን ኢስላም ከዚህ ፍፁም የፀዳ ነው ። ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምም ሆኑ ኹለፋኡ ራሺዲን አንድም ቀን ሴቶች አግተው አያውቁም ። ንፁሃንን ገድለውም አያውቁም ። አጥፈተው ጠፍተውም አያውቁም ። አንገት አስቆርጠው አምጡልን ብለውም አያውቁም ))

የዛሬዎቹ ኸዋሪጆች ግን ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደተናገሩት ዋነኛ ኢላማቸው ካፊሮች ሳይሆኑ ሙስሊሞች ናቸው ። ዋነኛ ኢላማቸው የጠላት ጦር ሳይሆን ንፁሃን ናቸው ። ዋነኛ ኢላማቸው የጦር ካምፕ ሳይሆን የሕፃናት መዋያዎች ናቸው ።

ኸዋሪጆች የሚደበቁትና የዋሁን የሚያታልሉት ሙስሊሙ ተበድሏል ፣ ተጨቁኗል ፣ ፍትሕ ፣ ሸሪዐ በሚሉ ለስላሳ ቃላቶች ነው ። በርግጥም ሙስሊሙ ተበድሏል ። አዎን የሙስሊሞ ጠላት የሆኑት ሁሉም ቢጠፉልን ደስ ይለናል ። ነገር ግን አላህ በዚህ አይነት አፀያፊ መልኩ እንድንወጣው አላዘዘንም ። ረሱሉል አሚን ለሁሉም አዛኝ ነበሩ ። የዛሬዎቹ ኸዋሪጆች ግን ከልባቸው ዕዝነት የሚባል ነገር ፍፁም የለም ። ከካፊሩ የበለጠ ሙስሊሙ ላይ የበረቱ ናቸው። የትኛምው ኡለማ አይቀራቸውም ። በጠቅላላ ሕዝቡን ያከፍራሉ ።

ኢስላምን በጠላቶች ያስደርፋሉ !!

እነሱን ለማጥቃት በሚል ሰበብ ሙስሊሙ ሃገር ላይ የኢስላም ጠላይ የሆኑት እነ አማኤሪካና ፈርንሳይ ይገባሉ ። እነሱም ልክ እንደ ኸዋሪጆች ንፁሃንን ይገድላሉ ። መሳጂዶችን የጦር ቀጠና ያደርጋሉ ። ሙስሊሙን እርስ በእርስ ያባላሉ ። በመጨረሻም የሙስሊሞችን ንብረት (ነዳጅ እና ሌሎችንም) ዘርፈው ይወጣሉ ። እዛ ላሉ ሙስሊሞች የሚተርፋቸው ወታደሮቹና ጋዜጠኞቹ ይዘው የሚመጡት የምዕራባውያን ክፉ ባሕል እና በነሱ ሰበብ የሚገቡት ሚሽነሪዎች ኩፍር ነው ።

_________________

አላህ የኢስላም ጠላቶችንያጥፋልን ከተንኮላቸውምይጠብቀን

አላህ ኡለማዎቻችንን ይጠብቅልን

ከኸዋሪጆች አይነት ኢስላምን ስም ከሚያስጠፋ ፅንፈኝነት ይጠብቀን

አሚን አላሁመ አሚን