Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሀሰነል በስሪ ምክር ለጉዞ ተዘጋጅታችዋል?

--------}} የሀሰነል በስሪ ምክር {{--------ለጉዞ ተዘጋጅታችዋል?ሀቢብ አል አቢድ እንደዘገቡት በአንድ ወቅት ወደ በስራ ከተማ ሄድኩኝ ባየሁት ነገር ተገረምኩ ሱቆች ሁሉ ተዘግተዋል መንገዱ ላይ ማንም አይታይም ከዚያም ተጣራው:- "የበስራ ህዝቦች ሆይ እኛ የማናውቀው የግላችሁ በዓል አላችሁ እንዴ? ለምንድን ነው ሱቆች የተዘጉት መንደሩም ጭር ያለው"?አንዱ እንዲህ ሲል መለሰልኝ:- "ሀሰነል በስሪ ከተማው ላይ ሰው ተሰብስቦ ኹጥባ እያደረጉ ነው ለዛም ነው ጭር ያለው" አለኝእኔም እየሮጥኩ ኹጥባው ላይ ደረስኩሀሰነል በስሪ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ወጥተው ኹጥባ ሲያደርጉ አየኍቸው እንዲህም ይሉ ነበር" ህዝቦች ሆይ ለመዳረሻችሁ ተዘጋጁ በጣም ጥቂት የሆነ ጊዜ ቀርትዋልናለአኺራች ሁ ተዘጋጁ እዚህ ዱኒያ ላይ አትቆዩምናለፍርዱ እጅ መስጫ ጊዜ ቅርብ መሆኑን አታውቁምን?ሁላችሁም ከስራችሁ ጋር ብቻ እንደምትቀሩ አታውቁምን?የፍርዱ ቀን ላይ ስራችሁን ብቻ ይዛችሁ እንደምትቀርቡ አታውቁምን?አላህ..ወንጀል እንዳትሰሩ ከለከላችሁ ግን እናንተ ከመስራት አልተቆጠባቹምበጀሀነም እሳት ቅጣት አስፈራራቹ ግን እናንተ ምንም አልፈራችሁምጀነትን እሰጣችዋለው አላችሁ ግን እናንተ ፍላጎቶ አላደረባቹምነጭ ፀጉራቹ ሞት እንደቀረባችሁ እየነገራቹ ነው ታዲያ ምን ትጠብቃላቹባለ ነጭ ፀጉሮች ሆይ! ጥሩን ስራ መስራት ትችላላቹ ታዲያ ወደ ኍላ ምንድን ነው የሚስፈገፍጋቹ?አፉን ብቻ እና ስሜቱን ብቻ የተከተለየአኼራውን ድርሻ ትቶ የዱኒያውን ብቻ የተቀበለወንጀሎችን እና መጥፎ ድርጊቶችን ከማድረግ ያልተቆጥበአላህ ጋር ሲገኛኝ ምን ይል ይሁን?ምን ማስተባበያ ይኖረው ይሁን?መንገዳችንን እየሳትን ነው እየጠመምንም ነው ስለዚህ እናንተንም እኔንም አላህ እንዲምረን እንጠይቀው"

Post a Comment

0 Comments